ከ15 ወራት በላይ ስጋት ሆኖ የዘለቀው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ 36 የጤና ባለሙያዎችን ህይወት እንደነጠቀ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።በቫይረሱ 3 ሺህ 329 የጤና ባለሙያዎች ተይዘው እንደነበር እና ከነዚህም ውስጥ 36ቱ ህይወታቸው ማለፉን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለሁ አባይነህ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስከ ሰኔ ሶስት ባለው ጊዜ በቫይረሱ ምክንያት 4 ሺህ 226 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት የጤና ሚኒስቴር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሐገራዊ የወረርሽኙን ስርጭት የሚያመላክተቱ ጥናቶች የሚቀርቡበት መድረክ ላይ ነው።
ወረርሽኙ ከባድ ጫና በሀገር ላይ ፈጥሯል ያሉት አቶ አባይነህ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎች በቫይረሱ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የሞት መጠን መቀነስ እንዳስቻለም ጠቁመዋል።ምክትል ዳይክተሩ ወረርሽኙ ሲጀምር ምንም አይነት የመርመሪያ መሳሪያ ያልነበረ ሲሆን አሁን ላይ 82 የመንግስትንና የግል የላብራቶሪ ተቋማት የኮቪድ ምርመራ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ተናግረዋል።
የምርመራ ኪትም በሀገር ውስጥ እየተመረተ እንዳለ እና ይህም በውጭ ምንዛሬ እጥረት ይስተጓጎል የነበረውን የግዥ ሒደት ማስቀረት እንዳስቻለ ተነግሯል።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እያገዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።በቀጣይም በወረርሽኙ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ጥንቃቄዎች ሊደረጉ ይገባል ተብሏል።
ኢቢሲ ዜና
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement,… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council