ካርቱም ላይ ከግብጽ ጋር የነበረው ምክክር ካለቀ በሁዋላ የሱዳን የፀጥታና የመከላከያ ምክር ቤት በቅርቡ በድንበር አካባቢ የኢትዮጵያን ወታደራዊ የመከላከያ ሃይሏን አተናክራለች በሚል በምስራቅ ሱዳን ድንበር ያሰማራውን ሃይል ለማጠናከር መወሰኑ ተሰማ። ተጨማሪ ሃይልም ወደ ስፍራው እንደሚልክ ይፋ ሆኗል።
የሱዳን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ማክሰኞ ዕለት ከጋዳሬፍ ግዛት ጋር በሚዋሰነው በአማራ ክልል ተጨማሪ የኢትዮጵያ ጦር ተጨማሪ ወታደሮችን ማሰማሩን ለሱዳን ትሪቢዩን አስታወቁ ፡፡
የሱዳንን ወታደራዊ ባለስልጣናት ጠቅሶ ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው ውሳኔው የተወሰነው ባለፈው ሐሙስ በሉዓላዊው ምክር ቤት ኃላፊ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን በተመራው የፀጥታና የመከላከያ ም / ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ውይይት ከተደረገበት በሁዋላ ነው።
እንደምንክንያት የቀረበው የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች በሱዳን አርሶ አደሮች ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውና የተወሰኑትን ካገቱ በኋላ መሬታቸውን ጥለው እንዲወጡ አስገድደዋል በሚል የአንድ ወገን መረጃ በመጥቀስ ነው ሱዳን ትሪቡን ያስታወቀው።
ሱዳን የአማራ ሚሊሻ የሚለውን ጉዳይ ደጋግማ ብታነሳም ዋናው ጉዳይ ግን ግብጽ ለሰጠቻት የቤት ስራ መነሻ ምክንያት ለመፍጠር እንደሆነ ይታወቃል። በሱዳን ያለው አለመረጋጋት መርገብ እንዳለበት ከወትሮው በተለየ ሊሰራ እንደሚገባ በተመድ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ትግራይን አስመልክቶ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ተወካዮችና ሌሎች ዓለም ዓቀፍ አካላት ጋር በተካሄደ የጠርጴዛ ዙሪያ ውይይት አንስተዋል።
ሱዳን የያዘችውን አቋም የማይደግፉ ባለስልጣናትና የወታደራዊ መኮንኖች መኖራቸው በሚሰማበት፣ የውስጥ አለመግባባቱና ትርምሱ በገነነበት፣ አመጽ በየቀኑ በሚስተናገድባት፣ የዳርፉር ጉዳይ እያገረሸ በሄደበትና የሱዳን ወደብ ከተማ አካባቢ በአስቸኳይ አዋጅ ስር ባለበት በአሁኑ ወቅት ቶማስ ሊንዳ ሱዳን ልትታገዝ እንደሚገባ አጽንዖት መስጠታቸው አካሄዱን ግልጽ እንደሚያደርገው ባለሙያዎች ወዲያው ነው የተቹት።
በሲኤኔን ጋዜጠኛ መሪነት በተካሄደው ኢትዮጵያን የመደብደብ ስብሰባ ሊንዳ ልክ እንደ ሱዳን ሁሉ የአማራን ስም በመጠቀስ ሲናገሩ ፊታቸው ላይ ከሚታየው ንዴት በላይ ድምጻቸውና ጥሪያቸው አንዳች ልዩ ጫና የመፍጠር ስሜት እንዳላቸው በሚያሳብቅ መልኩ ነበር።
ሊንዳ ብቻ ሳይሆኑ ሳማታን ፓወርም በተመሳሳይ ሱዳን ስለሟን እንድታስጠብቅ ልትረዳ ይገባል በሚል አንስተዋል። ሱዳን ወታደሮቿን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ለማንቀሳቀስ መወሰኗን በይፋ ማስታወቋን ተከትሎ ከኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ በድንበር አካባቢ ኢትዮጵያ በቂ ዝግጅት እንዳላትና የህዳሴው ግድብ ዙሪያ ምን ቀልድ እንደሌለ ማስታወቋ፣ አካባቢው ላይ ለሚሞከር ማናቸውም ጥቃት ሙሉ ዝግጅት መኖሩን መግለጿና ሙከራ ለሚያደርጉ ማስጠንቀቂያ መስጠቷ አይዘነጋም። ሱዳን ሰልጥኖ ወደ ቢኒሻንጉል ሊዘልቅ የነበረ ሃይልም በቅርቡ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ያታወሳል።
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country.… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ
- መንግስት ክትግስት በኋላ የሚከሰት ሕግ ማስከበር ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን አስታውሶ ጦርነት ናፋቂዎች አደብ እንዲገዙ አሳሰበ“ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ሁላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይኖርብናል። ከትዕግሥት በኋላ… Read more: መንግስት ክትግስት በኋላ የሚከሰት ሕግ ማስከበር ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን አስታውሶ ጦርነት ናፋቂዎች አደብ እንዲገዙ አሳሰበ
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ