በምሥራቅ ሸዋ ዞን ተሽከርካሪ የዘረፉ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። በዞኑ በአዳሚ ቱሉ ጅዱ ኮምቦልቻ እና ሊበን ወረዳዎች የተሽከርካሪ ዘረፋ ወንጀል የፈጸሙ 12 ግለቦች በቁጥጥር መዋላቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ ንብረትነቱ የሰላም ውኃ ማምረቻ ፋብሪካ የሆኑ አንድ ኤፍ ኤስ አር እና አንድ አይሱዙ እንዲሁም አንድ ሲኖ ትራክ በድምሩ ሦስት ተሽከርካሪዎችን ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጨለማን ተገን በማድረግ መዝረፋቸውን ገልጸዋል።
ዘራፊዎቹ የሐሰት ሰሌዳ ቁጥር በተለጠፈባቸው ሁለት ቪትስ ተሽከርካሪዎች እና በጦር መሳሪያ በመታገዝ የተሽከርካሪ ዝርፊያውን መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
ዘራፊዎቹ በተለይም የኤፍ ኤስ አር አሽከርካሪውን ዛፍ ላይ አስረው የዘረፏቸውን ተሽከርካሪዎች ይዘው መሰወራቸውን ኮማንደር አስቻለው ተናግረዋል። በዛፍ ላይ ታስሮ ያደረው አሽከርካሪ ለአካባቢው ኅብረተሰብ ባሰማው ጩኽት ፖሊስ ደርሶ ሕይወቱን ማትረፉን ገልፀዋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በዛፍ ላይ ታስሮ ያደረን አሽከርካሪ መነሻ በማድረግ የምርመራ አባላትን በቡድን በማደራጀት ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪ ዘራፊዎቹ የዘረፋ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀሙባቸው ከነበሩ ተሽከርካሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አመልክተዋል።
ፖሊስ ሌት ተቀን ባደረገው ክትትል የተዘረፉ ተሽከርካሪዎች ከተሸጡባቸው ድሬ ደዋ፣ አዲስ አበባ እና ሞጆ ከተሞች መያዛቸውን የገለጹት ኮማንደር አስቻለው፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ማስታወቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ዜናው ኢቢሲ ነው
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕወሓት የፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ለማሳተም ዝግጅት እያደረገ… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ