በምሥራቅ ሸዋ ዞን ተሽከርካሪ የዘረፉ 12 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። በዞኑ በአዳሚ ቱሉ ጅዱ ኮምቦልቻ እና ሊበን ወረዳዎች የተሽከርካሪ ዘረፋ ወንጀል የፈጸሙ 12 ግለቦች በቁጥጥር መዋላቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ ንብረትነቱ የሰላም ውኃ ማምረቻ ፋብሪካ የሆኑ አንድ ኤፍ ኤስ አር እና አንድ አይሱዙ እንዲሁም አንድ ሲኖ ትራክ በድምሩ ሦስት ተሽከርካሪዎችን ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጨለማን ተገን በማድረግ መዝረፋቸውን ገልጸዋል።
ዘራፊዎቹ የሐሰት ሰሌዳ ቁጥር በተለጠፈባቸው ሁለት ቪትስ ተሽከርካሪዎች እና በጦር መሳሪያ በመታገዝ የተሽከርካሪ ዝርፊያውን መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
ዘራፊዎቹ በተለይም የኤፍ ኤስ አር አሽከርካሪውን ዛፍ ላይ አስረው የዘረፏቸውን ተሽከርካሪዎች ይዘው መሰወራቸውን ኮማንደር አስቻለው ተናግረዋል። በዛፍ ላይ ታስሮ ያደረው አሽከርካሪ ለአካባቢው ኅብረተሰብ ባሰማው ጩኽት ፖሊስ ደርሶ ሕይወቱን ማትረፉን ገልፀዋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በዛፍ ላይ ታስሮ ያደረን አሽከርካሪ መነሻ በማድረግ የምርመራ አባላትን በቡድን በማደራጀት ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪ ዘራፊዎቹ የዘረፋ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀሙባቸው ከነበሩ ተሽከርካሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አመልክተዋል።
ፖሊስ ሌት ተቀን ባደረገው ክትትል የተዘረፉ ተሽከርካሪዎች ከተሸጡባቸው ድሬ ደዋ፣ አዲስ አበባ እና ሞጆ ከተሞች መያዛቸውን የገለጹት ኮማንደር አስቻለው፣ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ማስታወቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ዜናው ኢቢሲ ነው
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ