አቶ ደመቀ መኮንን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃላፊነታቸው በተጨማሪ ደርበው እየሰሩ ላሉበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጣፌ መታጨታቸው ተሰማ። ክልሉና በውጭ አገር ያሉ የክልሉ ተወላጆች በዜናው ደስተኛ አይደሉም።
የአብዲሌ ወንበር ላይ ከተቀመጡ ጀምሮ እጅግ በሚገርም ሁኔታ በመላው አገሪቱ ተቀባይነት ያገኙት ሙስጣፌ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት የታጩት ገዢው ፓርቲ ብልጽግና በምርጫው ካሸነፈ አዲስ በሚዋቀረው ካቢኔ የሚካተቱ እንዲሆን ታስቦ ነው።
በሚመሩት ክልል ሁሉም ብሄረሰቦች እኩል ሆነው የሚስተናገዱበትን፣ ቋንቋውን ከቻሉ በሃላፊነት የሚመደቡበትንና ልዩነት የሌለበትን አሰራር በማስፈን ሰላም ያወረዱት ሙስጣፌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሆን መታጨታቸውን አስመልክቶ የክልሉን ተወላጅ ዲያስፖራ አባላትን አናገረን ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የሜኖሶታ ነዋሪ የሆኑ የሶማሌ ተወላጅ ” ዜናውን ሰምተናል፤ ደስተኛ አይደለንም” ብለዋል። በሙስጣፌ ሹመት ሳይሆን ክልሉ ላይ የጀመሩትን ተግባር እንዲያጠናክሩ ከመመኘት አንጻር ባሉበት እንዲቀጥሉ ምኞታቸው እንደሆነም አስታውቀዋል። ክልሉ አካባቢም ተመሳሳይ እምነት እንዳለ ለማወቅ ችለናል።
በሌላ ዜና የሜኖሶታ ነዋሪ የሶማሌ ተወላጆች አሁን አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ የያዝቸውን አቋም እንዲላዘብ እየሰሩ መሆናቸው ታውቋል። ሰፊ የሶማሌና የኦሮሞ ማህበረሰብ ባለበት ሚኖሶታ የሶማሌ ድምጽና ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ በአካባቢው ያሉትን ሴናተር ማሳመናቸውም ታውቋል። ትናት ወደ ሜኖሶታ ያቀናው የክልሉ ሉዑል ቡድን ከባለስልታኑ ጋር እንዲገናኝ መመቻቸቱንም ጠቁመውናል።
ሙስጣፊ በትህነግና በትህነግ ደጋፊዎች ዘንድ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቀጥለው የሚጠሉ፣ በመላው አገሪቱ ደግሞ ተቀባይነትን ያገኙ የለውጡ ቱርፋት የሆኑ አዲስ መሪ መሆናቸው ይታወቃል።
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report
- ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችምዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ የጠቀችውን ብድር ለመፍቀድ ያቀረቡት ዋና ቅድመ ሁኔታ የብርን የመግዛት አቅም… Read more: ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችም
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀችOctober 27, 2021 የጉምሩክ ኮሚሽን ኮንትሮባንዲስቶች፣… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ