በፌዴራል የጋራ ገቢዎች ቀመር መሠረት ባለፉት 11 ወራት ከ20.7 ቢሊዮን ብር በላይ የክልሎች ድርሻ መሆኑን በመለየት ማስተላለፍ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገለጹ።
ይህ የበጀት ክፍፍል ከአለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ 11 ወራት አንፃር ሲታይ የ16.6 ቢሊዮን ብር ወይም 400.14% ዕድገት አለው።ይህ ገንዘብ የክልሎችን የልማት ወጭ በመሸፈን ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው ገልጸዋል።
ለክልሎች የተላለፈው የገቢው ምንጭ ከኤክሳይዝ፣ ከተርን ኦቨር፣ ከተጨማሪ እሴት እና ከንግድ ስራ ገቢ ግብር ታክሶች ብቻ የተሰበሰበ ነው ተብሏል።የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፌዴሬሽን ም/ቤት መሻሻል በመቻሉ፣ የተቋሙ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ በመምጣቱ እና ተቋሙ በተቀመጠው የማከፋፈያ ቀመር መሰረት ክፍፍሉን በአግባቡና በትክክል መስራት በመቻሉ የጋራ ገቢው ድርሻ ማደጉ ተገልጿል።
ክፍፍሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ታላቁና ፍትሃዊ ነው የተባለ መሆኑንን ለማሳየት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገላጭ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል። በሰንጠረዥ አስደግፎ የቀረበው ማስረጃ ሃሜታንና የጎንዮሽ ወሬዎችን ያስቀራል ተብሏል።
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ