በመጨረሻው ከበባና በድርድር ተስፋ መካከል ላለው ትህነግ አዲስ የሚዲያ ዘመቻ ተጀመረለት፤ የማርቲን ፕላውት ለቅሶ

“ቢቢሲን ጨምሮ፣ ሮይተርስ፣ ዘ ጋርዲያን፣ ዘ ቴሌግራፍ፣ ሜይል ኤንድ ጋርዲያን፣ ዘ ኢንዲፔንደንትና ሌሎች በርካታ መገናኛ ብዙኃን (ድረ-ገፆችን ጨምሮ) የውሸት ዜና በማሰራጨት ዘመቻ ተጠምደው ከርመዋል፤ አሁንም በአልሞት ባይ ተጋዳይነታቸው ቀጥለዋል። የእነዚህ ‹‹መገናኛ ብዙኃን›› የሐሰት ፕሮፓጋንዳና ውንጀላ ጠቅለል ያለ ምክንያት ‹‹ፀረ-ኢትዮጵያዊነት›› ነው።ይህ ኢትዮጵያን የመጥላት አባዜ እንግሊዝ ከከሃዲው የህ.ወ.ሓ.ት ጁንታ ጋር ካላት ወዳጅነትና ኢትዮጵያን ከማዳከም የዘመናት ሴራዋ የሚመነጭ ነው” ይላሉ አንተነህ ቸሬ በርካታ መረጃ ጠቅሰው ባሰራጩት ጽሁፍ።

ባለፈው ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባዘጋጀው የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ቢለኔ ስዩም ባልተለመደ ፊትና ስሜት የውጭው ዓለም ሚዲያዎችን የሚገባቸውን ነግረዋቸዋል። በዚያን ዕለት መግለጫቸው ” በቅርቡ ጦርነቱ ይጠቃለላል። ይህን አረጋግጥላችኋለሁ” ብለው ነበር ፣ የውጭ ሚዲያዎች አዲስ ዜና ማሰማት የጀመሩትም ይህንኑ የቢሌኔን ጥቅስ ከሰሙ በሁዋላ ነበር። ሚዲያዎቹ ብቻ ሳይሆኑ በበርካታ አዲስ ማዕረጎች ብቅ ያሉት የቀድሞው ኤታማዦር ሹም ጻድቃን ገብረትንሳይ እንዴት አሁን አሉበት ደረጃ እንደደረሱ፣ የደረሰባቸው ምትና ከአራት አቅጣጫ የደረሰባቸው ድብደባ ለማሰብና ዳግም ለመደራጀት እንኳን ጊዜ የሚሰጥ እንዳልሆነ ሲናገሩ ” ከባዶ ትግሉን እንጀምራለን ኑ ወደ በረሃ ግቡ” የሚል ጥሪ ነበር ያስተላለፉት።

በተደጋጋሚ ቀሪውን የትህነግ ሃይል ወደ ሱዳን ለማስወጣት የተደረገ ተደጋጋሚ ሙከራ መክሸፉን፣ በተደጋጋሚ የሞከሩ መመታታቸውንና የተረፉትም ወደ ዋሻቸው ማምለጣቸውን ፣ ወደ ሱዳን ለመውጣት መሞከር እንደማይቻል፣ ቢሞከርም እንደማይሳካ የመከላከያ ሃላፊዎች በተደጋጋሚ አስታውቀዋል። የርዳታ ስራውን ተገን አድርገው የተረፈውን የትህነግ ሃይል ነበስ እንዲዘራ የሚንቀሳቀሱትን መከላከያ እየለየ በፍተሻ እየያዘ ስላስቸገራቸው አዲስ መንገድ የተፈለገ ይመስላል።

ምርጫውን ከማካሄድ ጎን ለጎን መንግስት ጨዋታውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጠናቀቅ በያዘው እቅድ መሰረት ” ወደ ሽፍታነት ተቀይሮ እህልና ከብት እየቀማ ይበላል” የሚባለውን የትህነግ ቀሪ ሃይል ለመደምሰስ አሉበት ወደተባሉበት ስፍራ ቀለበቱን እያጠበበ እይከበባቸው እንደሚገኝ መረጃዎች አሉ። ይህ ቀሪ ሃይል አለ የሚባልበት ሁለት ስፍራዎች ተለይተው ከየአቅጣጫው ተከበው ዘመቻው የሚጀመርበት ጊዜ በሚጠበቅበት ሰዓት ነው ማርቲን ፕላውት ማልቀስ የጀመረው።

ረሃብን ለፖለቲካ መተቀምን የተካነበት ትህነግ አሁን ያለውን ቀውስ እጅግ አድርጎ የሚፈልገውና ወዳጆቹ ይህንኑ ቀውስ ለፖለቲካ ማስፈራሪያ እንዲጠቀሙበት በዋናነት የእንግሊዝ ሚዲያዎች ከበረሃ የሚከወነውን በማጮኽ ዓለም የተሳሳተ ሚዛን እንዲይዝ አስችለዋል። ዛሬም ማርቲን ፕላውት ኢትዮጵያ 42 ቶን የመርዝ መሳሪያ መቀለ ማራገፏን ኢንዲፔንደንት የተጠቀሰበትን መረጃ እያሰራቸ ይገኛል።

The chemical weapons arrived in Mekelle from Addis Abeba on flight ET3160 ETAUQ on June 5, B789 departing from Addis Abeba at 08:22. The plane is reported to have delivered a phosphorus chemical. The carrying capacity of the plane is 51 tons.

የኪሚካል ጦር መሳሪአ መቀሌ የገባው ከአዲስ አበባ በበረራ ቁጥር ET3160 ETAUQ በጁን 5 እንደሆነ የሚገልጸው የኢንዲፔንደንት ውስጥ አዋቂ ነገረን ወሬ ፖስፐርስ የሚባል ኪሚካል መጫኑን ይጠቁማል። ይህ የሆነው ኢትዮጵያ በማተቃለያው ዘመቻ የኬሚካል መሳሪያ ለመጠቀም ተዘጋጅታለች የሚል ዜና ለማራባትና ጫናውን ከዘመቻው በፊት ለማፍጠን እንደሆነ ይታመናል።

የሃሰት ዜና እንዴት እንደሚፈጠርና እነደሚሰራ ስልጠና ሲሰጥ በገሃድ የታየው ማርቲን ፕላውት፣ ኢትዮጵያ በያዘችው የመጨረሻ ጥቃት ድሮን እንደምትጠቀምና ጥቃቱ ከባድ እንደሚሆን ወትውቷል። ለህጻናት መብት እንከራከራለን የሚሉት ሚዲያዎች አንዳችም ተኩስ በሌለባት መቀለ ህሳናት ለአንድ ዓመት ከሶስት ወራት በቤት ውስጥ ታሸገው መኖራቸውን አያወግዙም። አሁን ትምህርት በይፋ ሲጀመር ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ከሄዱና ነገሮች ወደ ቀደሞ እንቅስቃሴያቸው ከተመለሱ የዓለም ህብረትሰብ ጫናውን ይቀንሳል በሚል ህጻናቱን ለፖለቲካ ጥቅም በቤት እንዲቆዩ ማድረግ ለትህነግ ደጋፊዎች ጽድቅ ነው።

የውጭ ሚዲያዎች ብቻ ሳይሆኑ የአገር ውስጥ የጀርመንና የቪኦኤ ሪፖርተሮች ሕጻናቱ ምን እንደሚሰማቸው ጠይቀው ቢያንስ ለህጻናቱ ሲሉ እውነት እንዳይዘግቡ ጉዳዩን የፖለቲካ መተቀሚያ አድረገው ሲዘግቡት መስማት እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ነጻ መሆናቸውን የገለጹ ተናግረዋል።

ማሪቲን ፕላውት ኢንዲፐንደንት የሚባለውን የአገሩን ሚዲያ ተጠቅሶ ሪፖርት የተደረገውን ዜና በግል የድረ ገጽ አምዱ ላይ አስፍሯል። ሰውየው “ለመጨረሻው ዘመቻ የማጥቃት ዘመቻ የኬሚካልና ከባድ መሳሪያዎች ወደ ትግራይ ተልከዋል ” ይላል ሊንኩን እዚህ ላይ ተጭነው ያንብቡ።

ማርቲን ፕላውት – በመግቢያ የተጠቀሱት ጸሃፊ ይህን ብለው ነበር

ይህኛው ‹‹ነጭ ህ.ወ.ሓ.ት›› ደግሞ የጋራ ብልፅግና አገራት የጥናት ተቋም (Institute of Commonwealth Studies) ባልደረባ፤ የቢቢሲ አፍሪካ የቀድሞ አርታኢ እንዲሁም ‹‹Understanding Eritrea››፣ ‹‹Fighting Britain››፣ ‹‹Understanding South Africa››፣ ‹‹War in the Horn››፣ ‹‹Who Rules South Africa›› የተባሉና የሌሎች መጽሐፍት ጸሐፊ ነው ይባላል። በብዙ አገራት የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ በመፈትፈትና ግጭት በመቸርቸርም ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኤርትራው ፕሬዚዳንትና ከዐማራ ክልል መሪዎች ጋር በጋራ ሆነው ትግራይን እንደወረሩ፣ የህ.ወ.ሓ.ት ኃይል የፌዴራል መንግሥቱን የጦር ጀቶች መትቶ እንደጣለ፣ የሕግ ማስከበር ዘመቻው እንዳልተጠናቀቀ … የሚገልፁ በርካታ የሐሰት መረጃዎችንና ማደናገሪያዎችን ሲፈበረክ ቆይቷል።

ከዚያም አልፎ የትግራይ ሕዝብ የሽምቅ ውጊያ እንዲደረግና የተራዘመ ጦርነት ውስጥ ገብቶ ለራሱም፣ ለፌዴራል መንግሥትም በአጠቃላይ ለመላው ኢትዮጵያ ተጨማሪ ችግር እንዲሆን የጅል ምክር መክሯል።

መቀሌ ከተማ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር መዋሏ በተሰማበት ወቅትም ልክ የህ.ወ.ሓ.ት ሰዎች ሲሉት እንደነበረው ‹‹ገና ምን ተነክቶ! ውጊያው ገና ነው …›› በማለት የከሃዲውን ውርደት ለማመን ሲቸገር ተስተውሏል።

ቀደም ሲል ከሻዕቢያ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበረው ቢነገርም ራሱን ‹‹የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አድርጎ›› ከሾመ በኋላ ከኤርትራ መሪዎች ጋር ተቀያይሟል።

 ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ማውረዷ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተጥሎባት የነበረው ማዕቀብ መነሳቱ ምቾት አልሰጠውም።

በአካባቢው ሰላም ከተፈጠረ የሚናገረው እንደሚያጣ ስጋት የገባው ፕላውት፤ ለማዕቀቡ መነሳትና ከኢትዮጵያ ጋር ለተፈጠረው ሰላም ዋናው ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መሆናቸውም ‹‹የዐቢይ ወታደሮችና ታማኞች›› እያለ ለሚጽፋቸው ብጥስጣሽ መልዕክቶቹ መንስኤ ናቸው። ‹‹ኤርትራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በማበር ህ.ወ.ሓ.ትን እየወጋች ነው›› የሚለው ተደጋጋሚ ለቅሶው የዚህ በቀል መነሻ ሳይሆን አይቀርም። • ጌታቸው ረዳ የማያውቃቸው የጄ. ይልማ መርዳሳ ንሥሮች
  …. SU-27 ሆዬ 100KM ላይ ኢላማውን አረጋግጦ ሚሳይልና ቦምቦቹን አራግፎለት ተመልሷል። በዚህ ቅፅበት የጌቾ ሰዎች ፍንዳታ እና እሳትን እንጂ SU-27 መምጣቱንም ማወቅ አይችሉም። ጌቾ ፍንዳታውን በተመለከተ መረጃ ሳይደርሰው/ በማይሰማበት ቅፅበት ጄቱ ሚሳይሉን ካስወነጨፈበት የ 100KM ርቀት አፍንጫውን ወደ ደብረ ዘይት መልሶ ከድምፅ ሁለት እጥፍ በላይ ተወንጭፎ ወደ ጦር ሰፈሩ ለማረፍContinue Reading
 • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
  የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
 • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
  “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
 • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
  አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading
 • የሽብርተኛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሠራዊታችንን የድል ግስጋሴ አይገታውም !
  ሽብርተኛው ከሚታወቅባቸው ስልቶቹ መሀል አንዱ ቅጥፈቱ ነው ፡፡ ጉልበት ሲያንሰው ምላሱ ይረዝማል ፤ ያልሆነውን ሆንኩ ፣ ያላደረገውንም አደረኩ…ይላል ፡፡ ይህ ደግሞ ጥርሱን የነቀለበት እና ተወልዶ ያረጀበት ባህሪው ነው ፡፡ አንድም ቀን ከአፉ እውነት ተገኝታ የማታውቀው ይህ ሽብርተኛ ፣ ሽንፈቱን የሚሸፍነው የሠራዊታችንን ስም በማጠልሸት ነው ፡፡ ደጋፊዎቹ ኪሳራውን እንዳያወቁ ፣ ሰላማዊውContinue Reading

Leave a Reply