ግራ ያጋባው የነጮቹ ፍላጎትና የትግራይ ቀውስ! ኢትዮጵያ በሰብአዊ ድጋፍ ስም መሳሪያ ሲገባ በተደጋጋሚ ይዛለች!!

ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለዕርዳታ ተደራሽነት እንቅፋት እንደሆነች፣ ይህም ችጋርን ለጦር መሳሪያነት ማዋል ተደርጎ እንደሚወሰድ፣ በዚህም ሳቢያ ባለስልጣኖቿን ” ትጠየቃላችሁ” የሚል ማስፈራሪያ እየተሰነዘረ ነው። ኢትዮጵያ በበኩሏ ከሁለት ቀበሌ ወይም ወረዳዎች በስተቀር ሁሉንም የትግራይ ክልሎች እርዳታ የሚሰጡትና የሚያከፋፍሉት የውጭ የርእዳታ ድርጅቶች መሆናቸው እየታወቀ እንዴት በዚህ ደረጃ እውቀሳለሁ ባይ ናት። ነገሩን ግራ የሚያጋባ የሚያደርገውም ይኸው ጉዳ ነው።

“በሰብአዊ ድጋፍ ስም የጦር መሳሪያ አሾልኮ ለማስገባት ተሞክሯል” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን አገራቸው በነጮቹ ወቀሳ ማዘኗንና ሃሳቡ ተቀባይ እንዳልሆነ ትናንት ባሰራጩት የቪዲዮ መልዕክት ገልጸዋል። እንዲህ ያለው አካሄድ ፍጹም ተቀባይነት እንደሌለውም አክለው አስታውቀዋል።

በትግራይ የችጋር አደጋ መኖሩን ቁጥር በመጠቀስ የተለያዩ አገራትና እዛው ትግራይ ሆነው እርዳታ በማከፋፈል ስራ ላይ የተሰማሩት እየተናገሩ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ሁሉንም በሩን ለሰብአዊ እርዳታ መክፈቱን፣ አንዳችም ዓይነት ገደብ አለመኖሩን፣ ሽፍቶች ዝርፊያ እንዳያካሂዱ የእጀባ ድጋፍ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ከሚናገረው በላይ የአብዛኞች ጥያቄ የሆነው መንግስት ከትህነግ ጋር እንዲደራደር የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ከማድረጉ በላይ ያልተቀበለውና ያልተገበረው ጉዳይ አለመኖሩ ነው።

የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ እየለቀቁ በመሆኑ ሌላ ምክንያት ሊቀርብ እንደማይችል ቢገመትም የነጮቹ ጥያቄ መቆሚያው የት እንደሆነ በርካቶችን ግራ እያጋባ ያለውም ለዚህ ነው። አቶ ደመቀ ለጂ7 አገር ተሰብሳቢዎች በሚመስል መልኩ ባስተላለፉት መልዕት፣ በትግራይ ክልል በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ የተሰማሩ አንዳንድ ወገኖች የጦር መሣሪያ አሾልከው ለመስገባት መሞከራቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አድርገዋል። ይሁን እንጂ ይህ በነጮቹ እይታ አግባብ የሚባልና የሚደገፍ ይመስላል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ” ኢትዮጵያ ላይ ተከፈተባት” ያሉት የተቀነባበረ ዘመቻ፣ እሳቸው እንዳሉት ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎ ምክንያት ፈልጎ አገሪቱን የማጥፋት ሴራ ስለመሆኑ ምልክቶች መኖራቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን በተደጋጋሚ እያነሱ ነው። አቶ ደመቀ በዝርዝር ይፋ አያድርጉት እንጂ ከሱዳን በኩል እርዳታ ለማስገባት በሚል መሳሪያ፣ መድሃኒትና የመገናኛ መሳሪያዎች ሲገቡ በተደጋጋሚ መያዙን የመከላከያ ሃላፊዎች አመልክተዋል።

ሚኒስትሩ የተወሰኑ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት የሆኑ ግለሰቦችና አጋሮች ሰብአዊ ስጋቶችን እንደሰበብ በመጠቀም “የአገሪቱን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነትን የሚጻረር ተግባርን እያከናወኑ ነው” በጥቅል ይናገሩ እንጂ በትግራይ እርዳታ ስራ ላይ የተሰማሩ ለሸማቂው የትህነግ ሃይል በቂ ድጋፍ እያደረጉ ነው። ይህን ድርጊት ነው አቶ ደመቀ “በሰብአዊ ድጋፍ ስም የጦር መሳሪያዎችን ለሽብርተኛ ቡድን አሾልከው ለማስገባት መሞከራቸውን የሚያመለክቱ አሳማኝ ማስረጃዎች” አሉን ሲሉ ነጮቹ እንዲያጤኑት የገለጹት።

ትግራይ ደርሰው የመጡ እንደሚሉት እንደሚወራው ባይሆንም በትግራይ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ይሁን እንጂ ሚዲያዎችና አንዳንድ አገሮች ችግሩን የሚገልጹበት አግባብ ከችግሩ ባለፈ መንግስትን በመወንጀል መሆኑን አይደግፉም። እንደውም ለዚህ ሁሉ ቀውስ ዋና ምንጭ የሆነውን ትህነግን ዘንግተውታል።

ሰሞኑንን ተምህርት መጀመሩን አስመልክቶ የጀርመን ድምጹ ሚሊዮን ከመቀለ ያስተላለፈው ዝግጅት ” እንዴት ትምህርት ይጀመራል” የሚል ይዘት ያለውና ዓላማው አለመማርን ማበረታትና የአድማው አንዱ አካል አድርጎ የማሳየት ይመስላል። ቢያንስ ለትግራይ ሕጻናት ትምህርት ቤት ውሎ መመለስ እንደ አንድ መላካም አጋጣሚ መውሰድና ሚዲያው ሊያበረታታው የሚገባ ጉዳይ ሆኖ ሳለ፣ ገና ለገና የዓለም ዓቀፍ ህብረተሰብ ትግራይ ተረጋጋች ብሎ ያስባል በሚል እንዲህ ያለ ቅስቀሳ መደረጉ በራሱ የሲራው ተባባሪዎች ብዛታቸውን አመላካች እንደሆነ ማስረጃ ንነው።

ወዳጅ አገሮችን ጥቀሰው እየተኬደበት ያለው አካሄድና መንግስት እየሰራ ያለውን ተግባር ማተልሸት ልክ እንዳልሆነ ባስገነዘቡበት መልዕክታቸው አቶ ድመቀ ” እንዲህ ያለው አካሄድ ለትግራይ ህዝብ አይጠቅምም” ብለዋል። ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተባብሮ መስራትና ማገዝ ችግሩን ለማስወገድ ዋነኛ መፍትሄ መሆኑንን ሚኒስትሩ አበክረው አስገንዝበዋል።

ማን ምን እንዳቀረበ በዝርዝር ባስገነዘቡበት ንግግራቸው አቶ ደመቀ በድጋሚ ኢትዮጵያ ለማንናውም ዓይነት ትብብር ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ላይ በዘመቻ ሉዓላዊነቷን በሚጥስ መልኩ ማጠልሸት ችግሩን ለመቅረፍ የሚፈይደው አንዳችም ነገር እንደሌለ አስታውቀዋል። እጅ ጥምዘዛው ተቀባይነት እንደሌለው በድጋሚ አረጋግጠዋል። የጂ 7 አገሮች ስብሰባ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ቻይና በግልጽ ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት ከወትሮው በተለየ አክርራ ገልጻለች። ቻይና ይን መግለጫ ያወጣችው ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋር ምክክር ከተደረገ በሁዋላ ነው።


Leave a Reply