ስድስተኛው አገራዊው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈለጊው ዝግጅት መደረጉ ተጠቆመ ፣”ምርጫውን ለማደናቀፍ፣ የግድቡን ሙሌት ለማስተጓጎል የሚንቀሳቀሱ አሉ፤ ከእይታችን ውጭ ግን አይደሉም” ትብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሕዝብ ወትቶ ያለ ስጋት እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል። የፓርቲዎች ሕብረት ምርጫው በሰላማዊ መነግድ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።
የፌዴራል፣ የክልል የደህንነትና የፀጥታ መዋቅሮች በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ያስታወቁት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው። የፌዴራል፣ የክልል የደህንነትና የፀጥታ አካላት ግብረኅይል ወቅታዊ የሀገሪቷን ደህንነት የሚገመግም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ውይይት እያደረጉ መሆኑም ታውቋል።
በዚሁ ወቅት የብሔራዊ ደህንነት እና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩ የምርጫ እና ድህረ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት እንደተደረገ መናገራቸውን የኢቢሲ ዘግባ አመልክቷል። ምርጫውንና ለማደናቀፍና የግድቡን ሙሌት ለማስተጓጎል የሚሰሩ የውጭ እና የውስጥ ጠላቶች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ተመስገን ሁሉም አይነት እንቅስቃሴ ከደህንነቱ መስሪያ ቤት ክትትል የሚያመልጥ እንዳልሆነ አመልከዋል። ይህንኑ አተናክሮ በአስተማማኝ ለመከወን የፌዴራል፣ የክልል የፀጥታና ደህንነት አካላት የጋራ ግብረ ሀይልም የሀገሪቷን ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተመሳሳይ የምርጫ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫና አረንጓዴ ዐሻራ እውን እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። “ኢትዮጵያውያን በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ድምፃችንን እንሰጣለን፤ ይህ ምርጫ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሚሆን ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።
መላው ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር ወደ ምርጫው በሚሄዱበት ወቅት ቀኑን የዜግነት ግዴታቸውን በመወጣት የትውልድ ማኅተም ለመተው እንዲጠቀሙበትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “በመጪው ሰኞ ውጡና ድምጽ ስጡ፣ እንዲሁም አረንጓዴ ዐሻራችሁን አስቀምጡ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ቀኑን ታሪካዊ የዴሞክራሲ ቀን እንዲያደርግትም መልዕክት አስተላልፈዋል።
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ