ኢዜማ መንግስት ሊመሰርት እንደሚችል አስታወቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በቀጣዩ ምርጫ 50+1 ድምፅ የማግኘት ዕድል እንዳለው ገልጾ መንግስት መሆን እንደሚችል ገመተ። በማብራሪያቸው ላይ ደግሞ ስፍራዎችን ጠቅሰው ” ጫና ባይኖርብን ኖሮ” ሲሉ ግምታቸውን ተታልተዋል።

ፓርቲው ለክልል ምክር ቤቶችና ለህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት 1540 እጩዎችን ያቀረበ ሲሆን ይህም መንግስት መመስረት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት የፓርቲው የአዲስ አበባ ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪና የህዝብ ግንኑነት ክፍል ምክትል ሃላፊው አቶ መሳይ ግርማ በተለይም ለብሰራት ሬዲዮ በሰጡት መረጃ ነው።

ኢዜማ ባቀረባቸወቅ እጩዎች፣ ባዘጋጃቸው የፖሊሲ ሰነዶች እንዲሁም በሚያራምደው የዜግነት ፖለቲካ አማካኝነት በአዲስ አበባ፣ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ፣በአማራ እና በጋምቤላ ክልሎች አሸንፎ ስልጣን እንደሚረከብ አቶ መሳይ ተናግረዋል።

ኢዜማ ከነዚህ የምርጫ ክልሎች ውጪ በሌሎች ማለትም በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በኦሮምያ እና በሃረር ክልሎች ጫና ባይኖርብን ኖሮ የማሸነፍ እድሉ ነበረን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመጪው ምርጫ 50+1 እንደሚያሸንፍ አቶ መሳይ ለብስራት በዝርዝር ያስረዱት ለብስራት ራዲዮ ነው። አቶ ብስራት ባሉት ላይ የብልጽግና አመራር በጽሁፍ ለላክንላቸው ጥያቄ ” ማሸነፋቸው ሲታወጅ በጨዋ አስረክበን አብረን እንሰራለን” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

የኢዜማ መሪ ዶክተር ብርሃኑ ጂኖሳይድን አስመልክቶ ለአማራ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ተንተርሶ የባልደራስ የውጭ አገር ምክትል ሊቀመንበርና የ360 ተንታኝ፣ የቀድሞው የትግራይ ክልል ነጻ አውጪ ግንባር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኤርሚያስ ለገሰ፣ “በትህነግ ግፍ ተፈጽሞብኝ መቀመጫዬ ተበለሽቷል” በማለት ክስ ሲያሰማ የነበረው ሃብታሙ አያሌው በምርጫ እንዳይሳካላቸው ሲቀሰቅሱ መሰንበታቸው የሚታወስ ነው።

Leave a Reply