የመጀመሪያው ምርጫ ለ450 የፓርላማ መቀመጫ ነው፤ ለ64ቱ ጷጉሜ

በነጪው ሰኞ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በ450 የፓርላማ መቀመጫ ለማሸነፍ የሚደረገው ምርጫ መንግስት ለመመስረት በቂ መሆኑ ተመለከተ። ምርጫ ቦርድ ይፋ እንዳደረገው የትግራይ ክልልን 38 ወንበር ሳያካትት 64 የፓርላማ ተመራጮች ፉክክር ሰኞ አይከናወንም። ጷጉሜ አንድ ግን ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬ እለት ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው ለ64ቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ለማሸነፍ የሚደረገው ፉክክር የተጓተተው ለጸጥታ በሚል በተለዩት ስፍራዎች ምክንያት ነው።

የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ በጥቅሉ 547 መሆኑ ይታወቃል። ሰኔ 14 በሚካሄደው ምርጫ ቀደም ሲል ለውድድር ቀርበው የነበሩት 509 የፓርላማ መቀመጫዎች ቢሆኑም በታሰበው መሰረት የተጠቀሰው አሃዝ ሙሉሉ በሙሉ ምርጫ በመርጫ እንደማይሸፈን የቦርዱ መረጃ ያመለክታል። በዚሁ መሰረት ለ450 መቀመጫ የሚካሄደው ፉክክር በተደጋጋሚ እንደተገለጸው ሰኞ ይካሄዳል።  

ሰኔ 14 ሙሉ ለመሉ ምርጫ የማይካሄድበት የሶማሌ ክልል በ23 የፓርላማ መቀመጫዎች ፤ ደቡብ ክልል በ16 መቀመጫዎች፣ የአማራ ክልል መራጮች ለ10 የፓርላማ መቀመጫዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ሰባት መቀመጫዎች፣በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አራት የፓርላማ መቀመጫዎች ሰኔ 14 ለምርጫ አይቀርቡም። 

በሐረሪ ክልል ሁለት፣ በአፋር ክልልም ሁለት የፓርላማ መቀመጫዎች ብድምሩ 64 መቀመጫዎች ለምርጫ አይቀርቡም።

ዳታውን የተመለከቱ እንዳሉት ዋና በሚባሉት ክልሎችም ሆነ በፌደራል ደረጃ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል መቀመጫ ለውድድር ክፍት በመሆኑ ከጷግሜ በፊትም ለንገላለግልና ወደ ናፈቅነው ሳምንት መመለስ የምንችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ጠቁመዋል። 

በሌላ የምርጫ ዜና ቦሩ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲከናወን መወሰኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በእለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምጻቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር አዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሰረት ለመንግስታዊ እና ለማንኛውም መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።

በዚህም መሰረት፣
– ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል ( ከሃረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) መንግስታዊ ተቋማት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ስራ ዝግ እንዲያደርጉ
– ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በክልሎች (ከሃረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) እና በፌዴራል የሚገኙ ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ
– የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የእለት ተእለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት..) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።
– የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም ዜጎች ድምጽ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና እቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምጽ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰኔ 08 ቀን 2013 ዓ.ም

Leave a Reply