ኢትዮጵያ የአርብ ሊግ የያዘውን የተንሸዋረረ አቋም ” ወግድ” አለች፤ “ግድቡ የሃይልና የምግብ ዋስትና ህልውና ነው”

የአረብ ሊግ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው መንግስት አስታወቀ። የአረብ ሊግ የህዳሴው ግድብን በተመለከተ በኳታር ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ነው ያስታወቀ።

የአረብ ሊግ በግብጽና በሱዳንን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ላይ ሳይመሰረት በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙሪያ ገንቢ ሚና መጫወት ሲገባው፣ ሚዛናዊነት የጎደለው፣ ለአንድ ወገን ያደለ ውሳኔ መሆኑንን ጠቅሶ ውሳኔውን ተቀባይነት እንደሌለው መንግስት ይፋ አድርጓል። ግድቡን የህልውና ሲል ደጋግሞ ገልጾታል።

ውሳኔው በቀጠናው የአባይን ወንዝ በትብብርና በዘላቂነት ለመጠቅም የተዘረጋውን መንገድ ይላከበረ መሆኑን መንግስት በመግለጫው ገልጿል። የአርብ ሊግ አባል ሀገራት የአባይ ወንዝን አጠቃቀምና የኢትዮጵያን ነባር አቋም በሚገባ እንደማያወቁ፣ ሊያውቁ ግን ይገባቸዋልም እንደነበር አመልክቷል።

የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎቿን ከድህነት የምታወጣበት የሀይል አቅርቦትና የምግብ ዋስትና የምታረጋግጥበት ፕሮጅክት በመሆኑ የህልውናዋ ጉዳይ እንደሆነ ሊታወቅ እንደሚገባ በጥብቅ ያስታወቀው ነው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህ የህልውና ጉዳይ ሊከበር እንደሚገባ አሳስቧል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የውሃ አጠቃቀም ህግ በማክበር የተፈጥሮ መብቷን እየተጠቀመች መሆኗ ሊታወቅ ይገባል ሲል መግለጫው ማስገንዘቢያ ይሰጣል። “አባይ የጋራ ሀብት እንጂ የተናጠል የግብጽ እና የሱዳን ብቻ አይደለም” በማለትም የሊጉ አገራት የያዙትን የተንሸዋረረ አቋም በሰፊው በማየት እንዲያስተካከሉት መክሯል።

የተፋሰሱ ሀገራት በትብብርና በውይይት መስራት የውሃ ደህንነትን ለማረጋገት ብቸኛው መንገድ እንደሆን የኢትዮጵያ ጽኑ እምነት እንዳላት መንግስት ይፋ አድርጓል። ሌሎች የአባይ ባለቤት የሆኑ የተፋሰሱን ሀገራት ወደ ጎን በመተው የአረብ ሊግ ሚዛናዊነት የጎደለውና ለሁለቱ ሀገራት ብቻ ያደላ አወዛጋቢ አቋም መያዙን መንግስት ሲኮንን በምክንያት መሆኑን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ የሁለቱን ሀገራት ስጋት ግመት ውስጥ ያስገባ፣ የታችኞቹን የተፋሰስ ሀገራትን በጋራና በትብብር መንፈስ እንጠቀም መርህን ተግባራዊ እንደምታደረግና ይህም መረህ ቀድሞውንም ቢሆን የነበረና ዛሬም የሚቀጥለበት እንደሆነ ተመክቷል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚደረገውን ድርድር በሚገባ ሳያጤኑ የአረብ ሊግ አባል ሀገራት የሳለፉትን ውሳኔ ዳግም ያጤኑታል የሚል እምነት እንዳላትም በመግለጫው ተካቷል።የህዳሴውን ግድብ አሞላልን በተመለከተ ሊጉ የያዘውን አቋም የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበለው አጠንክሮ ገልጿል።ከዚህ ይልቅ እንደ አንድ የቀጠናው ድርጅት ሶስቱ ሀገራትን በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ መፍተሔ በማምጣት የተዛባና ምክንያታዊ ያልሆነ አቋሙን የአረብ ሊግ እንዲያስተካክል መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

የንግሊዘኛውን መግለጫ ሙሉ ቃለ ኢዚህ ላይ ያንብቡ

Leave a Reply