የመከላከያ ሰራዊት ላይ ትህነግ ክህደት ከፈጸመ በሁዋላ፤ ትግራይ የገባው የኤርትራ ሰራዊት በቅርቡ ጠቅልሎ ይወጣል

እንግሊዛዊው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በትግራይ ክልል የ1977 ዓይነቱ ረሃብ እንደሚከሰት እያስጠነቀቁ እያስፈራሩ ነው። እርዳታ እንዳይዳረስ እንቅፋት ሆነዋል ሲል ኢትዮጵያን ኤርትራን አምርረው ሲከሱ ጫካ ያለው ያህል አመራሮችን ሲገድልና ሲያፍን፣ እርዳታ ሲዘርፍና ሲያቃጥል ለአንዴ እንኳን ስሙን አያነሱትም።ሊንዳ ቶማስም ” ምን እንደምንጠብቅ አይገባኝም” ሲሉ የማርክ ሎውኮክን ድምጽ ደግመውላቸውል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በግፍ በትህነግ ከታረደና ከተጨፈጨፈ በሁዋላ ድንበሩ ባዶ በመሆኑ ያለ ከልካይ ” ራሴን ለመከላከል” በሚል ወደ ትግራይ የገሰገሰው የኤርትራ ሰራዊት፣ በገለልተኛ ሃይሎች በጥልቅ ምርመራ ያልተረጋገጡትን ጨመሮ በርካታ በህግ ያልተደገፉ ጥፋቶችን ከመስራቱ ባሻገር ለእርዳታ ማጓጓዙ እንቅፋት በመሆኑ ስፋራውን ለቆ እንዲወጣ ሲወተውቱ ለነበሩት ዛሬ በግልጽ መልስ ተሰጥቷል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ዛሬ መደበኛ ባልሆነ የጸጥታው ምክር ቤት መድረክ ላይ ዛሬ እንዳሉት የኤርትራ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ከትግራይ ለቀው ይወጣሉ ማለታቸውን፤ የቀሩት ጥቂት ቴክኒካል የአፈጻጸም ሁኔታዎች እንደሆኑ ሮይተርስ እሳቸውን ጥቅሶ ጽፏል።

የኤርትራ መንግስት ” ሮኬት ተተኩሶብኝ በግብዣ ወደ ጦርነት ገባሁ” ሲል መጀመሪያ ላይ ቢናገርም፣ ከትግራይ ጠቅልሎ ለመውጣት ግን ዋስትና እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ መናገሩ ያታወሳል። አሜሪካ በቅርቡ ለሰየመችው የምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛም ይህንኑ መነጋራቸው በውቅቱ ተስምቶ ነበር። እንደውም ኤርትራ በኈለቱ ድንበር መካከል ሰላም አስከባሪ እንዲመደብ ጠይቃ ሁሉ ነበር።

አምብሳደር ታዬ ” ቴክኒካል ጉዳዮች” ሲሉ በዝርዝር ምን እንዳሉ ሮይተርስ አላብራራም።  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ ” ግጭቱ ቆሞ የኤርትራ ወታደሮች ይውጡ” ሲል በተደጋጋሚ መወትወቱ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ጻድቃ በቅርቡ ” የኤርትራ ሰራዊት ከወጣ በሁዋላ ሌላው ቀላል ነው” መናገራቸው የተመሳሰለ አሳብ ሆኖ ተገኝቷል።

ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ወታደራዊ አቋም የሚያውቁ እንደሚሉት ዛሬ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ከጉዳቱ አገግሞ፣ አዳዲስ አባላት አካቶና በአዲስ ተመሳሳይ ዓላማ ዳግም የተደራጀ በመሆኑ የኤርትራ ሰራዊት ድጋፍ አያስፈልገውም። መከላከያ አሁን ባለው አቅም ሙሉ በሙሉ ቴክኖሎጂ የሚጠቀምና የትህነግ ከሃጂ ሃይል ዘርፎ የታጠቀውን መሳሪይ ሙሉ በሙሉ የተረከበ በመሆኑ ስጋት የለም።

በትግራይ ይከሰታል የተባለውን ረሃብ መንግስት የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግና የትህነግ ሃይሎችን ለመርዳት ታስቦ የሚራገብ መሆኑን በመጥቀስ እንደማይቀበለው በዳታ መረጃ አስደግፎ ይፋ አድርጓል።

በትግራይ ከሚሰሩት የውጭ አገር እርዳታ ተቋማት 95 በመቶ ሰራተኞቻቸው የትግራይ ተወላጆች በመሆናቸውና አብዛኞቹ ከትህነግ ጋር ግንኙነት ስላላቸው ” መኪና ነጠቁን” በሚል መኪና እንደሚሰጡዋቸው፣ “እህል ወሰዱበን” እያሉ እንደሚያስረክቧቸውና፣ የእርዳታ እህል ከትግራይ እየተጋዘ አማራ ክልል ገብቶ እየተሸጠ መሆኑን እርዳታ ሰጪዎቹ እያወቁ ዝም ማለታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑንን ሪፖርት ማቅረቡ ተሰምቷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በጸጥታው ምክር ቤት ቀርበው “ግጭቱ እንዲቆም ተደርጎ የኤርትራ ወታደሮች ካልወጡ የ1977 አይነቱ የከፋ ረሃብ ተመልሶ ቢከሰት ማንም መደነቅ የለበትም” ማለታቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ ቢዘግብም አምባሳደር ታዬ ቃል በቃል ምን ምላሽ እንደሰጡ አላሰፈረም። ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብ ተከስቷል የሚለውን ዘገባ ግነት እንደሆነ፤ በተለይ በትግራይ ክልል ውስጥ ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ከሌሎች የረድኤት ድርጅቶች ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን በረጃና ማስረጃ መግለጹ አይዘነጋም።

Leave a Reply