ትህነግ”ዘመቻ አሉላ አውጇል” ሼትል “ለመተማመኛ ትህነግ በሰሞኑ ዘመቻ ምን እንደሆነ ፊልም ይቀርባል” ኃላፊ

ኢትዮ12 ዜና – “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ነኝ” ከሚለው ቡድን ጋር ያላቸው ግንኙነት በይፋ አይታወቅም። ከመድበኛ የመምህርነት ስራቸው በላይ ስለ ትህነግ ውሎና በትህነግ ጉዳይ አብዝተው ቲዊት ያደርጋሉ። ዛሬ “ጌታቸው ረዳ በስልክ ነገረኝ” ብለው በቲውተር ገጻቸው በተከታታይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ” ዘመቻ አሉላ ቀን አምስት ሰዓት አካባቢ ተጀምሯል” ብለዋል። በኖርዌይ በርገን ዩኒቨርስቲ መምህር ፕሮፌሰር ሻትል። እሳቸው ይህን ማለታቸውን ተከትሎ ያነጋገርናቸው እንዳሉን ከሆነ ትህነግ ላለፉት ሶስት ቀናቶች ክፉኛ ተመቷል። ስለዚህም አስቀድሞ መጮህና ማስጮኽ መመረጡን አመልክተዋል። ለሁሉም ግን በፊልም የተደገፈ መረጃ ሰሞኑ ሕዝብ እንደሚያይ አረጋግጠናል።

በሃሽ ታግ የትግራይ መከላከያ ሃይል ያሉት አቶ ጌታቸው በስልክ እንደነገራቸው ወዲያውኑ ያሰራጩት የቲውተር መረጃ አሉላ ኦፕሬሽን የማጥቃት ዘመቻ ረፋዱ ላይ በኢትዮጵያ ተጀምሯል። የተጀመረው በአራተኛውና ሶስተኛው ተዋጊ ሃይል በመታገዝ በአግበ እና ሃገረ ሰለማ ዙሪያ ገባውን ነው። በዚህም እየተፋለሙ ያሉት ከኈለይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሃይል ጋር እንደሆነ ነው ሼትል የገለጹት።

በሰበር ዜና የቀረበው የዘመቻ አሉላ የማጥቃት ውጊያ የዝናቡ ወቅት ሳይገባ አስፈላጊ ቦታዎችን ለመያዝ ያቀደና በሙሉ እምነት ውጤት እንደሚያመጣ ሼትል ጽፈዋል።

ይህ ዜና ከመሰራጨቱ በፊት ከተራ የፌስ ቡክ እክቲቪስትነት ደረጃ የወረደ ነው በተባለ አቀራረብ የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአውሮፓ ፓርላማ ” የኢትዮጵያ መንግስት መሪዎች የግራይ ህዝብን እንጨርሳለን ብለው ነግረውኛል” የሚለው ዜና ተሰራጭቶ ነበር።

ቀደም ባሉት ቀናቶች ደግሞ መንግስት የኬሚካል መሳሪያ ለመጠቀም ወደ መቀለ 42 ቶን መሳሪያ በአውሮፕላን ጭኖ ማራገፉ ሲገለጽ እንደነነር ይታወሳል። ከዙሁ ዜና ጋር በተያያዘ ማርቲን ፕላውት የሚባለው የትህነግ አፈ ቀላጤ የተጭበረበረ የኬሚካል ተቀታታይ ቦንብ ሲገነዳ የሚያሳይ ምስል በመለጠፍ ዓለም ሊደርስ እንደሚገባ ሲወተውት እነደሰነበተም የሚዘነጋ አይደለም።

እሱ ብቻ ሳይሆን በመናበብ ኢትዮጵያ ላይ የዘመቱት ክፍሎች በሙሉ በአንድነት እየተቀባበሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ኬሚካል መሳሪዎችን ሊጠቀም በዝግጅት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ሲወነጅሉ ነበር።

ኢትዮ 12 አስቀድማ እንደዘገበችው ሰሞኑንን በተካሄደ አሰሳ ትህነግ ክፉና ጉዳት እንደደረሰበት ለማረጋገጥ ተችሏል። ለጊዜው ስማቸውን እንዳይገለጽ አስገንዝበው መረጃውን የሰጡን እንዳሉት፣ ውስን ቦታ እንዲከበቡ በተደረጉት የትህነግ ሃይሎች ላይ በተወሰደ እርምጃ በርካታ ተደምስሰዋል። በግድ እንዲዋዱ የተያዙ ናቸው የተባሉ እጃቸውን ሰጥተዋል። አብዛኞቹ ህጻናት ናቸው።

“ትህነግ ሲመታ አንድ ሰው ወደፊት አምጥቶ መጮህ ልማዱ ነው” ያሉት የመረጃው ሰው ” ለመተማመን እንዲያመች ምና አልባት እሁድ በትህንግ ሃይል ላይ ምን እንደደረሰ በፊልም የተደገፈ መረጃ ለህዝብ ይቀርባል። እንግዲህ ጩኸቱ እሱንም አይታችሁ አትመኑ” የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ በታላቁ ጀግና ስም የተሰየመው ዘመቻ አሉላ የተባለው ጥቃት እንደሚጀመር የተገለጸበትን ምክንያት ገልጸዋል።

“በሴራና ሃሰተኛ መረጃ በማምረት ወደር የሌለው ትህነግ ዛሬም ይህንኑ ያደገበትን ፈጠራውን ቀጥሏል ” ሲሉ መረጃ አቀባያችን አስታውቀዋል። ለሰራዊቱ በተሰጠ መመሪያ መሰረት የትህነግን ርዝራዥ የገባበት በመግባት እየመቱ እንደሆነ ወታደራዊ መኮንኖችም በይፋ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው በይፋ አይናገሩ እንጂ ትህነግ ክፉኛ መመመታቱን አረጋግጠዋል። ማሳደዱ እንደቀተለም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ እያሳደደ መሆኑንን ባስታወቀበት ማግስት ነው በኖርዌይ የትህነግን አንድ አመራር ጊታቸውን ማናገራቸውን በሰበር ዜና ጠቅሰው ሼትል ትህነግ የማጥቃት እርምጃ በሶስት አቅጣጫ እንደሚከፍት የገለጹት።

የመከላከያ መኮንኖቹ ህዝብ ሽፍቶቹ የሚበሉት ስለሌላቸው ከህዝብ ጉሮሮ እርዳታ እየቀሙ፣ በቤቱ እየመጡ ምግብ ስለሚያስቸግሩትና ሰላሙን ስለነሱት በመማረሩን እየጠቆመ እያሳዛቸውና በብዛት ” በቃን ” እያሉ እጅ እንደሚሰጡ በይፋ ተናግረዋል። ኢትዮ12 ዜና

Leave a Reply