“ተልዕኮው ተጠናቋል”የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እየወጡ ነው፤

A damaged Eritrean military tank is seen near the town of Wikro, Ethiopia, March 14, 2021.Picture taken March 14, 2021.REUTERS/Baz Ratner


ኢትዮ12 ዜና – የኤርትራ ፕሬስ ዛሬ እንደዘገበው ” ተልዕኮው ተጠናቋል፤ጀግኖቻቸን ወደ ስፍራቸው እየተመለሱ ነው” ብሏል። አንዳንድ የማህበራዊ መረብ ተሳታፊዎች ” እናመሰግናለን” ሲሉ የኤርትራ ሰራዊት ክህደት ተፈጽሞበት በታረደና በታረዘበት ወቅት የኤርትራ ሰራዊት ያደረገውን ጠቅሰው እየጻፉ ነው። በተመሳሳይ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አዲስ የጫና ምክንያት “ምን ሊሆን ይችላል?” ያሉም አሉ።

ዜናው “የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ጦር አጋሮቻቸው ጋር በህብረት በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ላይ በተሳካ ሁኔታ ከተፋለሙ በኋላ ተልዕኳቸውን ጨርሰው ከሰሜን ትግራይ መውጣት መጀመራቸውን አንድ ምንጭ ለኤርትራ ፕሬስ ገለጸ” ሲል በማለዳ ዜናውን ይፋ አድርጓል።

ከትናት በስቲያ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር አጽቀ ስላሴ ” ከአንዳንድ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ቀርተዋል። የኤርትራ ወታደሮች በቅርብ ይወጣሉ” ሲሉ መደበኛ ባልሆነው የጸጥታው ምክር ቤት ውይይት ላይ መናገራቸውን ተከትሎ ነው ዜናው የተሰማው።

ባለፈው ዓመት አሸባሪው ጁንታ የአስመራን መንግስት ለመጣልና የኤርትራ እና የአማራ ክልሎችን የተወሰኑ ክፍሎችን ያቀፈ ገለልተኛ ‘ታላቋ’ የትግራይ ሀገር ለመመስረት፣ ኢትዮጵያን ኤርትራን ለመበታተን አቅዶ ነድፎ እንደነበር ያወሳው ኤርትራ ፕሬስ ምንጭ ያላቸውን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ ” ትህነግ ሞቱ ለበጎ ሆኗል። በዋሽንግቶን፣ በብራስልስና በሎንዶን የፖለቲኸኞች ኮሪዶር የሚሽከረከረው ስሙ ብቻ ነው” ሲል ትህነግ ላይመልስ መሰናበቱን አመልክቷል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት የድንበር አካባቢዎችን ከትህነግ አሸባሪ ቡድን ሙሉ በሙሉ መከላከለና ማስጠበቅ ስትችል ኤርትራ አካባቢውን ለቃ እንደምትወጣ በመጋቢት ወር ላይ ማስታወቋን ኤርትራ ፕሬስ አስታውሷል።

“TPLF is dead for good, and only its name is reverberating around in the political power corridors of Washington, London and Brussels.”

የኤርትራ ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን የተቃወሙና ድርጊቱን ወረራ እንደሆነ እነ አቶ ልደቱና የሳቸውን ሃሳብ የሚጋሩ ” ተንታኞች” ሲገልጹ ቆይተዋል። ዛሬም ድረስ በዚሁ አቋማቸው የጸኑ ጣልቃ ገብነቱን እየከሰሱ ነው። ” ጣልቃ ገብነት” የሚለውን የሚቃወሙ ደግሞ ” ድንበር ላይ ያለ ወታደር በክህደት ሲታረድና መሳሪያውን ተቀምቶ ሲጭፈጨፍ ማን ድንበር ይጠብቃል” በሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ።

” በወገኑ ከሃዲዎች ከሃያ ሁለት ዓመት በላይ በበረሃ ዋሻ ውስጥ የኖረ የአገር ተገን ሃይልን በክህደት የረሸነው ትህነግ፣ ክህደቱን እንደ ጀግንነት አይቶ ሲያቅራራ ድንበር መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ቁመና እንዳለው አለማወቁና ይህ ሊከተል እንደሚችል አለማሰቡ ድንቁርናውን የሚያሳይ ነው” ሲሉ የሚከራከሩ ሲሉ እንደከረሙት ” ኤርትራ ሮኬት ተተኩሶባት ተጋብዛም ወደ ጦርነቱ እንደገባች ሊታወቅ ይገባል”

የሁሉንም ወገኖች ክርክር የማይቀበሉ ወገኖች ” እናመሰግናለን” ሲሉ እየጻፉ ነው። ” ከሃጂዎች ሲያርዱን ደርሰውልናል፣ ከሃጂዎች እርቃናችንን ሲያስቀሩን አልበሰውናል፣ ከሃጂዎች እንደ ባዕድ ሲያዋርዱን ከጎናችን ቆመዋል። ከሃጂዎች በደቆቃዎች ውስጥ ከጥቅም ውጪ አደርገናቸዋል ብለው ሲዛበቱብን አጽናንተዋናል፣ ከሁሉም በላይ ጉሮሯችንን አርሰው ህይወት ቀጥለውልናል” ሲሉ የሰራዊቱ አባላት በተለያዩ ቀናት የሰጡትን ምስክረነት ያስታውሳሉ።

ትህነግ ትግራይን ለሃያ ሁለት ዓመታት ሲጠብቅና ሲያለማ በኖረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት ፈጽሞ የዘረፈው መሳሪያ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ እጅ መግባቱ፣ የተቀረውም በአየር ሃይል ጥቃት መደምሰሱን መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል።

ከበረሃ በቅርቡ መግለጫ የሰጡት የቀድሞ ኤታማዦር ሹም ጻድቃን ” የኤርትራ ሰራዊት ከወጣ ሌላው ቀላል ነው” ብለው ነበር። በዛው መግለጫቸው እንዳረጋገጡት፤ ጦርነቱ ሲጀመር ለማሰብ ጊዜ የማይሰጥ፣ መልሶ ለመደራጀት ትንፋሽ የሚከለክል፣ በቅጽበት ውስጥ ሜካናይዝድ ሃይላቸውን ወደ ተራ ተዋጊነት የቀየረ፣ እጅግ የተቀናበረ ምት አርፎባቸዋል።

ይህን የሚያስታውሱ፣ የኢትዮጵያ መከለከያ ሰራዊት አሁን ላይ በድንብ መደራጀቱን የሚያውቁ፣ የአማራ ክልል መሪ ጎንደር ላይ ለህዝብ ስም እየጠቀሱ ይፋ እንዳደረጉት የቅማንት አዋጊዎችና ተዋጊዎች መያዝቸውን የሰሙ እንደሚሉት በትግራይ የኤርትራ ወታደሮች መልቀቅ የሚያስከትለው አንዳችም ስጋት የለም። አምባሳደር አጽቀ ” የቲከኒክ ጉዳዮች” ያሉዋቸውን ነጥቦች ዘርዝረው ባያስረዱም፣ የሚለቅ ሲኖር የሚተካ ሃይል የማደራጀት ጉዳይን ለማንሳት እንደሆነ አዋቂዎች ይገልጻሉ።

የኤርትራ ሰራዊት መልቀቁ እንጂ በምን ያህል መጠንና ከድንበር ምን ያህል እርቆ እንደሚሰፍር ይፋ አልሆነም። በህግ የተወሰነለትን የባድመን አካባቢ ትቶ ስለመሄዱም የኤርትራ ፕሬስ በዝርዝር አልተናገረም። ኢትዮ12 ዜናLeave a Reply

%d bloggers like this: