ሳኡድ አረቢያ ላይ እየሆነ ያለው ነገር

ይህ ጉዳይ ከመጀመሩ በፊት የሳኡዲ ባለሀብቶች የሚመሩት ሜቢሲ አክባር የሚል ሚዲያ በሳኡዲ አረቢያ ያሉ “ህገወጥ ሰዎችን ብዛትና ጥቅም ጉዳትና ወንጀል” የሚኖሩትን ማህበራዊ ኑሮ ጨምር የሚዳስስ ትልቅ ዶክመንተሪ ፊልም እያሳየ ነበር። ሙሉውን ዶክመንተሪ ሳይለቀቅ እየቅራረጡ በዜና መልክ ያቀርያቀርቡትም ነበር ! ወዲያውኑ ሳይቆይ የባለፈው ጅሙአ መስጊድ ውስጥ የተነገረው ኹጥባ ስለ ህገወጥ ሰዎችና የሚሰሯቸው አፀያፊ ስራዎች የሚያማክል ነበር።

በዶክመንተረው ላይ፣ ኢትዪጵያዊያን

በአደንዛዥ እፅ ንግድ ሲሰሩ የሀገሪቱ ደህነት ሲይዛቸው የሚያሳይ ምስል አለ። ጅዳ ኪሎ 8 የሚባል ቦታ ላይ ብዙ ኢትዩጵያዊያን እንደሚኖሩ በተቀረፀው ቪዲዮ ላይ አይቻለሁ። ከዚህ ባሻገር በስቢከር የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ተከፍተው አካባቢው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሆቴሎችን እንደሚመስሉ ጋዜጠኛው በቀረፀው ምስልላይ አሳይቶናል። አንዲት ሴት ሦስት ወንዶች ሆነው” ሁለቶቹ እጅና እጇን ይዘው ሦስተኛው አንዳዴ ሄድ እያለ እንደማቀፍ እያደረገ መንገድ ላይ ወክ ሲያደርጉ በተቀረፀው ቪዲዮ ላይ ባይኔ አይቼዋለሁ። ይህ ምስል መላውን የሳኡዲ አረቢያ ህዝብ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

በወቅቱ ቀረፃውን የሰራው ጋዜጠኛ እውነት « ጅዳና ኪሎ 6 »ከሳኡዲ መንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆናለች,,? የሀበሾች የግል መኖሪያ ሆናለች ማለት ይቻላል እያለ ይናገራል። ይህ ጅዳ ላይ የተደረገ ቀረፃ

ብቻ ነው።

ሪያድ ላይ፣ መንፉሃ አካባቢ“ አስካሪ «መጠጥና ከኒና» የሚነግዱ ኢትዩጵያዊያን እጅ ከፍጅ ሲያዙ ከየመን እስከ ሪያድ የዘረጉትን የንግድ ኔቶርክ ለሳኡዲ ፖሊሶች ሲናገሩ የሚያሳይ ምስል አይቻለሁ። እዛው ሪያድ « ኢቴጋ» ውስጥ” በአንድ ቤት ኪራው ግቢ ውስጥ ወደመሬት ተቆፍሮ ለአረቂ ማምረቻነት ሲጠቀሙበት የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል በሳኡዲ ፖሊሶች «.ከነ ሴቶቹና ወንጆቹ እጅ ከፈንጅ ሲያዙ አይተናል»..በጎኑ የራቁት ጭፈራ ቤት ከፍተው ራቁታቸውን ከአረብ ወጣቶች ጋር የሚጨፍሩ ኢትዩጵያዊያን ሴቶችም እጅግ ከፍንጅ ተይዘዋል።

.

በተጨማሪ፦ ባንክ ሰብሮ በመዝረፍ

ሴት ኢትዩጵያውያንን ከአረብ ወንዶች ጋር እያገኙ በወሲብ ሻጭና አሻሻጭነት ላይ የተሰማሩ ኢትዩጵያዊያን ተይዘዋል ።

ከዚህ ቀጥሎ ከየመን ወደሳኡዲ መግቢያ ድንበር ላይ ትጥቅ ታጥቀው እፅ በማዘዋወር በሰዎች እገታ፣ ኦሮሞ አማራ ትግሬ እየተባባሉ የገዛ ወገናቸውን እያገቱ 400ሺ 5መቶሺ የሚቀበሉ ኢትዩጵያዊያን እንዳሉ ተካቷል። ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ክልል ላይ የሚፈፀም አይደለም ሳኡዲ አረቢያ ግዛት ውስጥ የሚፈፀም ነው።

እዚህ ላይ ለሁላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ግልፅ ማድረግ የምፈለገው ነገር” በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ ዜጎቻችንን መንግስታችንንና ዜግነታችንን አንገት እያስደፉት ነው። በሳኡዲ ያለ አንድ የኢፌዴሪ አምባሳደር ሳኡዲዎች ዜጎቼን አሰሩ፣ ተጎዱ፣ ብሎ ለማነጋገር ሲሄድ ሳኡዲዎቹ ለመንግሥት የሚያቀርቡት መልስ ከላይ የፃፍኩትን ነው።

እናም የችግሩና የስቃዩ ምንጮች የራሳችን ዜጎች መሆናቸውን መርሳት የለብንም። እዚህ ላይ ግን ትንሽ መቶዎች የሚሰሩትን አፀያፊ ስራ ለመቶሺዎች የስቃይና የመከራ መፈልፈያ ፍብሪካ መሆኑ ነው እጅግ የሚያሳዝነው።አንዲት ሉአላዊነት አገር የራሷ ህግ አላት። ህጓን ጥሶ ዜጎቿንና ህዝቧን ወደ አላስፈላጊ ነገር የሚዶልን እንኳን የውጭ አገር ዜጋ ይቅርና የራሷንም ዜጋ አትምርም። ያማለት ግን በእንደዚህ አይነት የጭምልቅና ስራ ላይ የተሰማሩት“ ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው ማለት አይደለም። እኛ ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገን የወንጀላችን ልክ እንጅ ዜግነታችን ወይም ማንነታችን አይደለም።

በዚህ ነውረኛ ስራችን ላይ የግብፅ ተልዕኮ ተጨምሮበት አሁን ላይ ለአያሌ ጭዋ እህተ

ላቡን አቅልጦ ቤተሰቡን አገሩን ወገኑን ቀና የሚያደርግ ስንት ጀግና ኢትዮጵያዊ እንዳለ ሁሉ፣ ላቧን አቅልጣ ለሀገሯና ለወገኖ ለቤተሰቧና ለወደፊት ኑሮዋ ብረት የምተክል ጀግና ኢትዮጵያዊ ሴት ሰራተኛ እንዳለች ሁሉ በጭምልቅናና በአውሬነት ስራ ላይ የተሰማሩ ከንቱዎችም አሉ። ትንሽ ከንቱዎቹ የሚሰሩት ስራ ለሞቶሽ ጀግኖች የስቃይና የሞት ምንጭ ሆነዋል። ለሀገራችን ክብር ማጣት ለመሪዎቻችን አንገት መድፋትም ምክኒያት ሆነዋል።

እናም ውድ ኢትዮጵያዊያን፣ የሳኡዲ መንግሥትና ህዝብ ላይ ብቻ ክፉነትን በዳይነትን ገፊነትን ጨካኝነትን” መለጠፍ የለብንም። ነውሩና ጉዱ ከኛቤት ይጀምራልና፣

በመጨረሻም፦በሳኡዲ ያሉ ዜጎችን በተመለከተ “የኢትዮጵያ መንግስትና የሳኡዲ መንግስት” ኢትዩጵያውያን ዜጎችን

በሰላም ወደ“ ሀገራቸው እንዲመለሱ” እየሰሩ ነው ። በቅርቡ እስርቤት ያሉትም ከእስር ቤት ውጭ በህገወጥ መንገድ ሀገሪቱ ላይ የሚኖሩ ዜጎችንም ጭምር በምህረት አዋጅ ወደ አገር ቤት ለመመለስ በሰፊው እቅድ ተይዞለት እየተሰራበት ነው። እስከዛው ድረስ እራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ንብረታችሁን በአግባቡ ጠብቁ።

ሱሌማን አብደላ

Leave a Reply