ብልጽግና አዲስ አበባ አበራ፤ ባልደራስ ተከትሏል

ኢትዮጵያ ባደረገችው የመጀመሪያ ታሪካዊ ምርጫ ከየምርጫ ጣቢያዎች ይፋ እየሆነ አብዛኛ ድምጽ የብልጽግና መብራት ማብራቱ ተሰምቷል። የአዲስ አበባ ተባባሪያችን እንዳለው በዚሁ ጊዜያዊ የየምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ባልደራስ ከኢዜማ የተሻለ ድምጽ አግኝቷል።

“ራሱን ከታሪካዊ የኢትዮጵያ ምርጫ ታሪክ በማጉደል የአሸባሪ አቀንቃኝ መሆንን መርጧል” የተባለው የአውሮፓ ህብረት ያፈረበት ምርጫ በአዲስ አበባ ደረጃ ተቃውሞ አልተሰማበትም። በሁሉም የአገሪቱ ዳር ምርጫው በሰላም ቢጠናቀቅም ተባባሪያችን አዲስ አበባ ላይ አተኩሯል።

ሁሉም ፓርቲዎች የአዲስ አበባን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ታማኝ ስለመሆኑ ተስማምተዋል። ባልደራስ ከኢዜማ የተሻለ ድምጽ እንዳገኘ መረጃዎች አመላክተዋል።

ኢዜማ በተገመተው ልክ ድምጽ እንዳላገኘ ተሰምቷል። በአዲስ አበባ ኢዜማን ወክሎ ለፓርላማ ከተወዳደሩት መካከል የአርክቴክት ባለሙያው የሆኑት አቶ ዮሃንስ ብቻ ማሸነፉ ነው የተነገረው። በአዲስ አበባ ደረጃ ግን የሉበትም ተብሏል። የሽግግር መንግስት እያለ ሲያለቅስ የነበሩት ኢንጂነር ይልቃልና ፓርቲያቸው ሕብር ዋጋ አላገኘም።

አመራሮቹና አባላቱ በማህበራዊ ገጾች ” ነገም ሌላ ቀን ነው” ሲሉ እየተስተዋሉ ነው። ኢዜማ ” ኢትዮጵያ ታሸንፍ” ሲል እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ አመራር የከፈሉት ዋጋ ግን በዚህ ምርጫ በክብር የሚያሰጥ ስለመሆኑ ጎን ለጎን እየተነገረ ነው። ፓርቲውም ይህን አጭር ሃሳብ በገጹ አስቀምጧል።

ለኢዜማ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች

አንዳንዶቻችሁ በበረሀ አንዳንዶቻችሁ ደሞ በሀገር ቤት ለሀገራችሁ ነፃነት ስትታገሉ ፊት ለፊት የነበረውንና እስካሁን ሀገራችን ላይ እንደ አለቅት ተጣብቆ አልነቀል ያላት ጠላት ሳያንስ፤ ከጀርባችና ከጎን እየተወጋችሁ ሊተመን የማይችል መስዋእትነት ከፍላችኋል።

ጓዶቻችሁን በበረሀ አጥታችኋል። በየስር ቤቱ ለአመታት ከፍተኛ ስቃይ ተቀብላችኋል። ሙሉ አካል ይዛችሁ ገብታችሁ ጎዶሎ ሆናችሁ ወጥታችኋል። ገና ፓርውን ስትጠነስሱ ጀምሮ በሁሉም ብሄረተኞች፣ በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በገዢው ፓርቲና በተቀጠሩ ቦዘኔዎች ከአዳራሽ እስከስቴዲየም፣ ከማህበራዊ ሜዲያ እስከ መደበኛ ማዲያ፣ ከስድብ እስከ ዛቻ፣ ከስም ማጥፋት እስከ ድብደባ፣ ከግድያ ሙከራ እስከ ግድያ ሲወርድባችሁ አንገታችሁን ደፍታችሁ፣ ስሜታችሁ ገርታችሁ ለዚች ሀገር ሰላምና ዴሞክራሲ መወለድ ለከፈላችሁት ዋጋ ክብር ስሰጥ ታላቅ ውስጣዊ ደስታ እየተሰማኝ ነው።

ከሁሉም በላይ ለሰላምና መረጋጋት በምታደርጉት የሰከነ አካሄድ እና የትብብር እንቅስቃሴ ማፈሪያ በሌላቸው የዘመናችን ጉዶች አንዴ አድርባይ አንዴ ተለጣፊ ስትባሉ ምን ሊሰማችሁ እንደሚችል ሳስብ አጥንቴ ድረስ የሚዘልቅ ህመም ይሰማኛል። ለመሆኑ ማን ነው ማንን አድርባይ፣ ተለጣፊ ተደጋፊ ባይ? ሁሉንም ጊዜ ይመልሰዋል ማንም አመነ አላመነ የዚህ ምርጫ ሰላማዊነት የናንተ፣ የትግስት የፅናትና የስክነት ውጤት ነው።

ምርጫውን ምርጫ ያደረጋችሁትም እናንተ ናችሁ። የተከበራችሁ ኢዜማውያን እየነደዳችሁ አብርታችኋል። ኢትዮጲያችን ይሄን ክፉ ዘመን ተሻግራ ራሷን ወደ ኋላ ማዬት ስትጀምር ያኔ በታሪክ የሚገባችሁን የክብር ቦታ ታገኛችኋለሁ።

ክብር ለኢዜማውያን!ኢትዮጲያ ታሸንፋለች!

የውጭ ታዛቢዎችን ምስክርነት አስመልክቶ እንዳሻቸው ሲታዘቡ እንደነር ታውቋል። ግን ዘገባቸው በተሰጣቸው ነጻነትና እድል መጠን ሪፖርታቸው አልታየም።

Leave a Reply