የ”ችጋር” አጀንዳ በትግራይ ያሉ እርድታ ሰጪዎች “ቁማር” ተካሯል

በትግራይ “በሰብአዊነት” የምግብ ድጋፍ ለማድረግ የተሰማሩ እርዳታ ድርጅቶች ሰራተኞቻቸው በመቶኛ ሲሰላ ከዘተና በመቶ በላይ የገር ውስጥ ዜጎች ናቸው። ከዚያ ውስጥ ደግሞ ዘጠና ስምንት በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ሾፌሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የትግራይ ተወላጆች እንደሆኑ ዘርፉን የሚከታተሉት ይናገራሉ።

ቀውስና ችጋር ደግሞ ከትህነግ ጋር እጅግ የተቆራኙ የህልውና ጉዳዮች እንደሆኑ የ1971 ድርቅና የህል ንግድ፣ እንዲሁም የሃውዜኑ ጭፍጨፋ ቅንብር በዋናናት የሚጠቀሱ ምሳሌዎች ናቸው። የ1971 ረሃብ ለትህነግ የህልውና ሲሳይ መሆኑ፣ ሃውዜን የተፈጸመው ድብደባ ደግሞ የድርጅቱ የፕሮፓጋንዳ ምንጭ እንደሆነ የተነገረው በራሱ ነባር አባላት ዛሬ ሳይሆን አራት ኪሎ ጉብ ብሎ በነበረበት ወቅት ለውጥ ሳይታሰብና ሳይጸነስ ነበር።

ታሪክ ራሱን ደገመ እንደሚባለው ዛሬ ላይ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይህን ያለፈውን የትህነግ ታሪክ እያስታወሱ ነው። በትግራይ ከእርዳታ ጋር በተያያዘ በቅርብ የሚሰሩ ለዝግጅት ክፍላችን እንዳስረዱት መንግስት መሮታል።

በትግራይ ዕርዳታ ምን እየሆነ ነው?

በትግራይ እርዳታ የሚያሰራጩ የውጭ ድርጅቶችና በትግራይ እርዳታ ሰጪነት የተመዘገበ ድርጅት የሚሸፍኑት የራሳቸው ክልል አላቸው። በዚህ ክልላቸው እህል ያከፋፍላሉ። መረጃ ያሰባስባሉ። ስለሰሩትና ስለገጠማቸው ለአለቆቻቸውና ለመንግስት ሪፖርት ያቀርባሉ። ይህ የሚታወቀው ህጋዊ አሰራር ግን ተጋባራዊ አልሆነም። በዚህም የተነሳ መንግስት ተማሯል። ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች መንግስታትና ተቋማት በተደራጀ መልኩ ኢትዮጵያንና መንግስቷን ወደ ሁዋላ ብለው በአንድ ወገን ሪፖርት በመጠመዳቸው መንግስት ግራ ተጋብቷል። ሲመረው እንደመንግስት ” የለም” ብሎ አቋም ሲወስድ ” አሰናከለ” እየተባለ ትን እስኪለው በሪፖርትና በዜና ያጣድፉታል። ምላሹን አይሰሙትም። እንደውም በቸዋ መልክ አነጋገረውት ሲያበቁ በሚሰጡት ሪፖርትና መግለጫ ከዲፕሎማት፣ ከአገር መሪና ከሃላፊነታቸው ጋር በማይመጣጠን መልኩ ወርደው ዘመቻ ሲከፍቱበት ነው የሚሰማው።

ለስራው ቅርብ የሆኑት ሲነገሩ እነዚህ እርዳታ እንሰጣለን የሚሉ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስንዴ፣ አልሚ የህጻናት ምግብ፣ ዱቄትና ዘይት እየጫኑ ወስደው ያድላሉ። ለማን፣ መቼ፣ የትና ምን ያህል መተን እንዳከፋፈሉ ሲጠየቁ መረጃ አጠናክረው መስጠት አይፈልጉም ወይም እሺ አይሉም።

See also  «በወልቃይት ጠገዴ ያልተነገረ ካልሆነ በስተቀር ያልተፈጸመ የግፍ አይነት የለም›› ኮ. ደመቀ

እንደ ሃላፊው ገለጻ ድርጅቶቹ ተረክበው ለማከፋፈል የውሰዱት እርድታ በየዓይነቱ ከሁለት ዙር በላይ የሚዳረስ ለአራት ጊዜ የሚሆን ነው። ግን በሚወጣው ሪፖርት እጥረት እንዳለና ለዚህም መንግስት ተጠያቂ እንደሆነ፣ ረሃብን ሆን ብሎ ለፖለቲካ ጭና እንደመሳሪያ የሚጠቀም አድርገው ይስሉታል። በዚህም አውቀው የሚያሳድሙትን ጨምሮ ጉዳዩ ያለግባቸው አገሮች ኢትዮጵያን ጥፋተኛ ያደርጋሉ።

በተደጋጋሚ በተደረገ ውይይት ” ጥርት ብያለ ሪፖርት አቅርቡ” ሲባሉ ” አትጠይቁን” የሚል መልስ ይሰጣሉ። ” ወንበዴ እየቀለባችሁና ዳግም እንዲያንሰራራ እየሰራችሁ ነው። ለተጎዳው ህዝብ አልጠቀማችሁም” በሚል ሲገሰጹ የተንሻፈፈ ሪፖርትና መረጃ እየሰጡ መንግስትን ያስደበድባሉ።

“ዱቄትና እህል፣ በተለይም አልሚ ምግብ ከህጻናት ጉሮሮ እየተነጠቀ ለወንበዴው ቡድን እለት ቀለብ ይሰጣል። ሾፌሮቹ መኪና አስረክበው ‘ነጠቁን’ ብለው ባዶ እጃቸውን ይመለሳሉ። ህግ ከማስከበሩ በላይ እንዲህ ያለውን የተቀነባበረ ዘመቻ ነው እየታገልን ያለነው። የትግራይ ተወላጆችም ሆኑ የትህነግ ደጋፊዎች ያልገባቸው ይህ ነው” የሚሉት መረጃውን ያካፈሉን ” መኪናና የእርዳታ ዕህል እንዳይዘረፍ መከላከያ ያጅብ ሲባል፤ በፍጹም አይሆንም፤ አታጅቡን” የሚል ምላሽ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። በዚህ መልኩ እንደማይቀጥልም ጠቁመዋል።

One of the TPLF founders, Dr. Aregawi Berhe told the BBC that of the $100 million that went through TPLF hands to mitigate famine in Tigray, $95 million was diverted for weapons purchases and other purposes not related to famine relief.

In 2005, the U.S. created its Africa welfare-on-the-dole program, a/k/a Productive Safety Net Program (PSNP), keeping millions of people especially in Tigray in a state of permanent poverty and dependency.

የቀረበው እርዳታ በጊዜና በተረጂ ቁጥር ሲሰላ ከሚፈለገው ወይም መቅረብ ከሚገባው በላይ ሆኖ ሳለ፣ እጥረት የሚወራውና እንዲወራ የሚደረገው በሌላ ምክንያት መሆኑንን ያመለከቱት ሃላፊው ” መንግስት በሱዳን በኩል ለትህነግ ቁንጮዎች መውጪያ ነጻ በር ይክፈት፣ አሜሪካና ኢትዮጵያ አብረው ይስሩ፣ የንጹሃን ስቃይ ይቁም” የሚለው የኸርማንክሆን ጥሪ የዚሁ ዕርዳታ ስር የሚፈለፈለው ሴራ ማሳያ ነው” ብለዋል።

See also  በአማራ ክልል ዝርፊያ መፈጸሙና ንብረት መውደሙ ከመረጋጋት በሁዋላ የሕዝብ አጀንዳ ሆነ

የዕርዳታ ድርጅቶች ሆነው ከተሰማሩት ውስጥ መድሃኒት፣ የሬዲዮና ስልክ እንዲሁም ኤሊክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ ለጄነረተር መጠቀሚያ ነዳጅ፣ ሲጃራ፣ ጫማ፣ የውስጥ ሱሪ … ለማቅረብ ሲሞክሩ መያዝቸውን፣ መሳሪያ ጭነው በፍተሻ የተያዙ እንዳሉም ሃላፊው አመልክተዋል። ቀደም ሲል መከላከያ በሃላፊዎቹ አማካይነት ይህንን ሪፖርት ማደረጉን አመልክተዋል። ይህን ሁሉ እውነት የሚያውቁት የእርዳታ ድርጅቶቹ ሃላፊዎች በሪፖርታቸው አያካትቱም።

ሽፍቶቹ ሰላማዊ የቀበሌ አመራሮችን ሲገሉ ዝም እንደሚሉ፣ እንዳሽቸው ለሚነዷቸው ሚዲያዎችም እንደማያሳውቁ ያስረዱት የመረጃችን ባለቤት ” እህል ተዘረፍን፣ መኪና ተነጠቅን” ብለው ሁሉንም ለወንበዴዎቹ አስረክበው ባዶ እጃቸውን ለሚመለሱት ደሞዝ ተከፋይ ሰራተኞች ድርጅቶቹ ምንም እንደማይሉዋቸው አስታውቀዋል። ይህን ሁሉ እርዳታ እንሰታለን የሚሉት አገሮች ጠንቅቀው እንደሚያውቁ፣ በተለያዩ ውይይቶች ለዓለቆቻቸው ቢነገርም ለውጥ ያልተገኘበት ችግር እንደሆነ አመልክተዋል።

ስለ መፍትሄው ተጠይቀው ” በቅርቡ ወደዱም ጠሉም አዲስ አሰራር ተጋባራዊ ይሆናል። ምርጫው ጥሩ መልዕክት ስላስተላለፈ በሁሉም ወገን መላዘብ ይኖራል” የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል። ይህ የማይሆን ከሆነ አንድ አገራዊ መፍትሄ ሊበጅ እንደሚገባ አመልክተዋል። ሲያጠናቀቁም ” ትህነግ የችጋር አጀንዳን እንዴት እንደሚጠቀም ተክኖበታል። ዓለምን ባሰማራቸው ተከፋይ ወገኖቹ አማካይነት እያሳተና እያታለለ ዛሬም እየሰራበት ነው። በግሌ ሃቅ ቢኖር ችጋርን ለፖለቲካ ፍጆታ እያዋለ ያለው እሱና ደጋፊዎቹ ናቸው” ብለዋል።

በትግራይ አሳሳቢ ረሃብ እንዳለና በአስቸኳይ ወደ ስምምነት ካልተኬደ አደጋው የከፋ እንደሚሆን በምዕራብ አገራት፣ በተባበሩት መንግስታትና በአሜሪካ በኩል በቅንጅት መገለጹ አይዘነጋም። ረሃቡን የኢትዮጵያ መንግስት ለጦር መሳሪያነት እየተገለገለበት ነው በሚል እየተከሰሰ ነው። መንግስት በገሃድ ክሱን ያጋደለና እውነታውን ያልተንተራሰ መሆኑንን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በተደጋጋሚ ማስተባበሉ አይዘነጋም።

ገለልተኛ የሆኑ እንደሚሉት ግን የትግራይ ሕዝብ ትናንትም በሴፍቲ ኔት ስንዴ ሲሰፈርለት ነበር። ዛሬ ልዩነቱ ዕርዳታው ላይ መፈናቀል መታከሉ ነው። ትግራይ ሰላማዊ ክልል በምትባልበት ወቅትም ሁለት ሚሊዮን ልጆቿ ተረጂ ነበሩ። ዛሬም ጦርነትና ቀውስ የታጀበበት ተረጂ ናቸው። የትህጋር ልሂቃን ሊያስቡና ትክክለናውን አቋም ሊይዙ የሜጋባቸውም ለዚህ ህይዝብ ሲሉ ነው።

Leave a Reply