“ትህነግ ድል ቀናው፤ ትህነግ በጀት ተደበደበ”ቢቢሲ፤

ቢቢሲ እንግሊዘኛው የትህነግ ተዋጊዎች በርካታ ከተሞች ላይ ድል ቀንቷቸው እንደከረሙ ” ትህነግ ድል አገኘ” ሲል ዘግቧል። የቢቢሲ አማርኛም ትርጉሙን ደግሞታል። የመከላከያ ሃላፊ ውጊያ መኖሩን አምነው፣ ወጊያው ግን ዋናዎቹን የትህነግ አመራሮች ላይ እርማጃ ለመውሰድ የተከፈተ በመሆኑ ለለመጥፋት የሚደረግ ጩኸት እንደሆነ ይገልጻል። ትህነግ በበኩሉ ድል እንዳገኘ ጠቅሶ፣ በጀት ሲቪሎች መመታታቸውን አስታውቋል።

የቢቢሲን ዜና መሰረት በማድርገ ከአዲግራት ባደረግነው ማጣራት ” ትህነግ ሲዋጋ ጀግና ተዋጊ፣ ሲመታ ሲቪል ተተቃ የሚል ድርጅት ነው” የሚል አስተያየት አግኝተናል። ውጊያ መኖሩን ያልካዱት ምስክሮች እንዳሉት አዲግራት ላይ የመንግስት ሃይል እነሱ ባላወቁት ምክንያት ቦታውን ሲለቅ የተወሰኑ የህንገ ሃይሎች ታይተው ነበር። ሆኖም ግን መከላከያ ወዲያው እርምጃ ወስዶ ከተማዋ የቀድሞ መልኳን ይዛለች።

ዛሬ ጌታቸው ረዳ ትዊት ባደረጉት መሰረት በሺህ የሚቆጠሩ የኢርትራ ወታደሮች መገደላቸውን መማረካቸውን አመልክቷል። ሲ- 130 የመጓጓዣ አውሮፕላን መጣላቸውን ከተቀረጸ ፊልም ተወሰደ ያለውን ምስል በማሳየት አስፍሯል። ይህን አስመልክቶ ከመንግስት ወገን የተባለ ነገር የለም። በተመሳሳይ ምስላቸው የሚታዩ ምርኮኛ የተባሉ የተዳከሙ ወታደሮችም አስመልክቶ ቃል በቃል የተባለ ነገር የለም።

ድምጸ ወያኔ በሰበር ዜና “… በዘመቻ አሉላ አባ ነጋ ጥቃት ከአስር ሺህ በላይ የምንግስት ወታደሮች ሙት አድርገናል ፤ ቁጥራቸው ከ3356 የሚበልጡ ተዋጊዎችን፣ እንዲሁም የጦር አዛዦችን ማርከናል። ከመቶ አርባ አራት የሚልቁ ተሽከርካሪዎች ተረክበናል። በቁጥር የማይገለጽ የጠላት ክፍለ ጦሮችን አስወግደናል” ሲል በድምጸ ወያኔ ትግርኛ አሳውጇል።

ዜናው “ምርጫው በሚካሄድበት ቀን ልዩ ድል እናስመዘግባለን” በሚል አስቀድሞ ለተገባው ቃል ይውል ዘንድ የተሰራ ድራማ መሆኑንን የሚገልጹ ” ትህነግ ድል በድል ቢሆን ኖሮ ኸርማን ኮሆን በሱዳን ነጻ መውጫ በር እንዲከፈትና መሳሪያ እንዲያወርዱ አይማጸኑም ነበር” ሲሉ መከራከሪያ ያቀርባሉ።

በሌላ ወገን ምርኮኛ ተብሎ የቀረበው ቪዲዮ የመከላከያ ሰራዊት በተኛበት ሲመታና ትጥቅ አልባ እንዲሆን ባልደረቦቹ ጭምር ክህደት በፈጸሙበት ወቅት የተቀረጸ እንደሆነ በመረጃ እየገለጹ ነው።

ያም ሆኖ አሁን መነጋገሪያ የሆነው ትህነግ ድል እንዳገኘ የዘገበው ቢቢሲና ማርቲን ፕላውት የመንግስት ሃይል በሲቪል ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሷል በሚል ሌላ የዓለም ዓቀፍ ተቃውሞና ድጋፍ ጥሪ ማሰማታቸው ነው።

የኈት ዓመት ልጅ ሳትቀር በጥቃት መጎዳቷን የህክምና ሰዎች እንደነገሩዋቸው ጠቅስው የዘገቡት ሚዲያዎች፣ በተለይም ቢቢሲ ሲቪል ያላቸው አካላት እነማን እንደሆኑ ግልጽ አይደለም። ቢቢሲ በዜናው ያካተታቸው የመከላከያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ” አየር ሃይል መምታት ያለበትን ቦታ የሚያውቅና የጠላትን አድራሻ አይቶ አጥቅቷል” ብለዋል።

ቢቢሲ የአካባቢ ነዋሪዎች እንደነገሩት ጠቅሶ ሲቪል ሰዎች መጎዳታቸውን እንደገለጸው ሁሉ፣ በሌላ በኩል የአካባቢ ነዋሪዎች በስልክ ለቤተሰቦቻቸው እንዳሉት መከላከያ ጠንካራ ጥቃት ሲሰነዝር የትህነግ ሃይሎች ሸሽተዋል። ሶሸሽም ከተድመሰሱት ውጪ ከቆሰሉት ላይ መሳሪያ እየነጠቀ ነበር። መከላከያ የቆሰሉትንና የወታደር መለያ የሌላቸውን ቁስለኞች ሰብስቦ ህክምና አስገብቷል። እንደ እማኞቹ “የአየር ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ደረሰ” ተብሎ የተሰራጨው ዜና ይህ ነው።

ከስፍራው በሚገኝ መረጃ ቀድሞ በማድረስ የሚታወቀው ግዕዝ ሚዲያ “ጁንታው የራሱ ታጣቂም ሲቆስሉ ጥሏቸው ነው የሚሄደው” ብሎ ዘግቧል። በዘገባው ሲያብራራ “… ትላንት በተጎጋ በነበረው ውግያ ብዙ ሲቭልያን አሰልፎ የተዋጋ ሲሆን በውግያው የቆሰሉትን ብረታቸውን ብቻ በመንጠቅ የራሱ ቁስለኛ ጥሎ ሽቷል” አያይዞም “ጁንታው ቆስለው ጥሏቸው የሄደው ታጣቂዎች መንግስት ህክምና እያደረገላቸው ይገኛል” ሲል አስፍሯል። ቁስለኞች ወደ ሃኪም ቤት በቀይ መስቀል ተሽከርካሪ ሲገቡ ምስል አሳይቷል።

” ከአሸነፍን ዜና” ጎን ለጎን ” ተደበደብን” የሚለው ዜና የኢትዮጵያ ሕዝብ ካደረገው ምርጫ ዜና በላይ ገኖ ወጥቷል። ምርጫው ከመደረጉ በፊት ሲባሉ የነበሩ ስጋቶች በሙሉ ሳይከሰቱ ካሉት ተወዳዳሪዎች ሕዝብ ያሻውን መምረጡ ለውጮቹ መገናኛዎች ዜና አለመሆኑ የሚዲያዎቹን ሰፈር ያመላከተ መሆኑ ተመልክቷል። ምርጫ ጣቢያ ገብተው ጠቅላይ ሚንስትሩን የቅድሚያ ጥያቄ ” ስለ ረሃብ በትግራይ” ማድረጋቸውና፣ የምርጫውን ዜና በሌሎች ጉዳዮች ለመለውሰ የተኬደበትን አካሄድ ” አንድ ሙሽራን መድረክ ላይ ወጥቶ ‘ስራ እንዴት ነው ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው” ሲሉ በቢቢሲ ሙያዊ ቁመና የተሳለቁ ታይተዋል።

መንግስት በይፋ ባይናገረውም የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታና ህግን የማስከበር ስራ አስመክቶ ነገ መግለጫእንደሚሰጡ ተሰምቷል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: