አየር መንገድ ለመንገደኞች ጥንቃቄ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው አቋረጠ፤ መከላከያ ሰፊ ጥቃት ሊሰነዝር ነው

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተሳፋሪዎች ጥንቃቄ በሚል ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡ ተሰማ። የኢትዮጵያ መከላከያ በሁሉም አቅጣጫ ” ያዋጣኛል” የሚለውን ጥቃት ሊሰነዝር እንደሆነ ተሰማ። በጥቃቱ መከላከያ ሁሉንም ዓይነት ዘዴ ይጠቀማል ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስም ያለተጠቀሱ ሃላፊን ገልጾ ኢትዮኢንሳይደር ማረጋገጫ ማግኘቱን ነው የጠቆመው። እንደዘገባው በረራ ከቆመ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ድርጅት እንደመሆኑ ለጸጥታ ችግር ባለባቸው አካብቢዎች ሌሎች እንደሚያደርጉት በረራውን ማገዱ አግባብ እንደሆነ ተመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መከለከያ አሰላለፉን አስተካክሎና የአቋም ለውጥ አድርጎ ዘመቻው ሲካሄድ እንደሆነው አይነት ጥቃት ሊሰነዝር መሆኑ ተሰምቷል። ትናንት መግለጫ የሰጡት ኮሎኔል ጌትነት በቀጥታም ባይሆን ” ታውቁታላችሁ ክንዳችንን እናሳያቹሃለን” ብለው ነበር።

የዝግጅት ክፍላችን እንደሰማው አሁን በተለያዩ ቦታዎች አሉ የሚባሉት ጦርነቶች እንዳሉ ሆኖ፣ የሚጀመረው አዲስ ኦፕሬሽን ከቀድሞ የጠነከረ፣ አመቺ ነው የተባለ እርምጃ የሚወሰድበት ነው። ሲጠቁ ወደ ቤተሰቦቻቸው በማምራት ሰላማዊ የሚመስሉትን የትህነግ ሰራዊት አባላት እንዴት ለይቶ ማትቃት እንደሚቻል ግን የታወቀ ነገር የለም። በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች ፍጹም ሰላም እንደሆነ የጠቆሙት ክፍሎች፣ ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ ወልቃይትና ራያ ላይ ህዝቡ ራሱ ወታደር በመሆኑ ስጋት እንደሌለ ይናገራሉ።

በተጠቀሱት ቦታዎች የትህነግ ሰራዊት ተመሳስሎ መኖር ስለማይችል ሊሳካለት እንደማይችል ያክላሉ። ወልቃይት ጠገዴ ህዝቡ በወጉ ተደራጅቶ፣ ታጥቆና ነቅቶ እንደሚጠብቅ ያስታወቁት ክፍሎች አሁን የሚጀመረው ጥቃት ከፍተኛ ጩኸት ሊያስነሳ እንደሚችል ከወዲሁ ግምታቸውን ገልጸዋል።

Leave a Reply

%d bloggers like this: