ብ/ጀኔራል ዘነበ ክፍሉ ማነው?በአጭር የወጣ የኋላ ታሪክ

ብ/ጀኔራል ዘነበ ክፍሉ በትላንትናው (ሰኔ19/2013) ምሽት እንደተደመሰሰ ዜናው ተሰምቷል። ለመሆኑ ይህ ሰው ማን ነው? የኋላ ታሪኩና በጥቅምት 24ቱ የሀገር ክህደት ወንጀል የነበረው ሚና ምን ነበር?

እነሆ መጠነኛ መረጃ

ተወልዶ ያደገው “ሰለክለካ” ከምትባል የሽሬ የገጠር ከተማ ነው። ሰራዊቱን የተቀላቀለው በ1980ዎቹ መግቢያ አካባቢ ነው።

በተለያዩ የወታደራዊ ኃላፊነት ቦታዎች ሰርቷል። ለ15 ዓመታት ያህል የ23ኛ ክፍለ ጦር አመራር ነበር። በመቀጠል ወደ 31ኛ ክፍለ ጦር ተመደበ። ከጥቂት ቆይታ በኋላ ለሠላም ማስከበር ተልዕኮ ተላከ። ከተልዕኮ ሲመለስ የ23ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆኖ ሲሰራ ከቆየ በኋላ በአዳሱ የዕዝ አደረጃጀት የሰሜን ዕዝ አስተዳደር ሆኖ ተመደበ።

በክህደቱ የነበረው ሚና!

በመከላከያ ሪፎርም መሰረት ዕዞች አራት አባላት ባሉት ዐቢይ ኮሚቴ ይመራሉ።
የኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ የዕዙ ዋና አዛዥ፣ ምክትሉ አዛዡ፣
የሎጀስቲክስ ክፍል ኃላፊው እና
የዕዙ የአስዳደር

ዕዙን የሚመሩ የዐቢይ ኮሚቴው አባላት ናቸው።

በዚህ አደረጃጀት መሰረት የሰሜን ዕዝ አስተዳደር የነበረው ብ/ጀኔራል ዘነበ ክፍሉ የጥቅምት 24ቱን የሀገር ክህደት ወንጀል ከውስጥ ለማደራጀት ቁልፍ ሰው ነበር።

አጠቃላይ ስምሪቱን ከውስጥ ሁኖ የመራው እርሱ ነው። የአስተዳደር ኃላፊነቱን ተጠቅሞ የሰሜን ዕዝ አባል የሆኑ ትግሬዎችን ከውስጥ አደራጅቷል። ከየክፍለጦሩ፣ ከአራቱም ሜካናይዝድ (በነገራችን ላይ እስከ ጥቅምት 24 ድረስ ኢትዮጵያ ከነበሯት ስድስት ሜካናይዝድ ጦሮች አራቱ በሰሜን ዕዝ ስር ነበሩ)፣ ከየ ሻለቃው፣ …አስፈላጊ የተባለውን የሰው ኃይል በራሱ መንገድ የማሰባጠር ስራ ቀድሞ ሰርቷል።

የዕዙ ኮር አመራር አራት ኮሚቴዎች ያሉት ቢሆንም በግሉ የተለያዩ ውሳኔዎችን ይወስን ነበር። አስተዳደራዊ የሆኑ ጉዳዮችን ሆነ ብሎ በማጓተት ሰራዊቱ በአመራሩ ላይ እንዲማረርና ቅሬታ እንዲያሳድር ‘ሳቦታጅ’ ሲፈጽም ቆይቷል።

ከነሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደና ጌታቸው አሰፋ መመሪያ እስከ እየተቀበሉ ከእርሱ ጋር ሲሰሩ የነበሩት (በአጠቃላይ የክህደቱ ፈፃሚዎች) ፦

1) ብ/ጀኔራል ዘነበ ተክሉ
2) ብ/ጀኔራል ከበደ ፍቃዱ (31ኛ
ክፍለ ጦር አዛዥ አሁን አብሮት የተደመሰሰ)
3) ኮሎኔል መሐሪ አሰፋ
(የጌታቸው አሰፋ ወንድም፣ አሁን ላይ
በሕይወት ይኑር አይኑር አይታወቅም)

ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት ወታደራዊ አመራሮች የሰሜን ዕዝን ጥቃት ከውስጥ በማቀነባበር ትልቅ ሚና ነበራቸው።

የ31ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው ብ/ጀኔራል ከበደ ፍቃዱ፣ መቀመጫው ሽሬ ነበር። ሙሉውን ሰራዊት ለዚህ ተልዕኮ አሰልፋለሁ በሚል በክፍለ ጦሩ ላይ ቀላል የማይባል ኪሳራ አድርሷል። ይህ ሰው ጡረታ ሊወጣ አስተዳደራዊ ፕሮሰሶች ተጀምረው እያለ ነበር የጥቅምት 24ቱ ጥቃት የተከፈተው።

ኮሎኔል ሻምበል በየነ [ባለከዘራው] በ31ኛ ክፍለ ጦር የብ/ጀኔራል ከበደ ፍቃዱ ምክትል በመሆን አብረው ሰርተዋል። በዕለቱ ምሽት ላይ ጥቃቱ ሲጀመር ቁጥር አንድ ታርጌት የነበረው ‘ባለከዘራው’፣ ስብሰባ በሚል ከጠሩት በኋላ አዳራሹ ውስጥ ከተደገሰለት የሞት ጽዋ እንዴት ግዳይ ጥሎ እንዳመለጠ ይታወቃል።

ብ/ጀኔራል ዘነበ ከዕዙ በልዩ ሁኔታ የሚመቱ ካምፖችን፣ ዩኒቶችን፣…ፖኬት ኤሪያዎችን በመለየትና ከውስጥ ቀድሞ ያደራጃቸውን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱን አባላት ከልዮ ኃይሉና ዞባ ሚሊሻው ጋር ኃይል የማዋሃድና የማሰማራት ስራዎችን በቅርብ ርቀት ሆኖ መርቷል።

ኮሎኔል መሐሪ አሰፋ ከነ ታደሰ ወረደና ጌታቸው አሰፋ የሚወርዱ መመሪያዎችን በሰራዊቱ/በዕዙ ላይ በማስፈፀም ቀላል የማይባል ሚና ነበረው። ኮሎኔል መሀሪ ቀደም ሲል መከላከያ ዋና መስሪያ ቤት የፋይናንስ ክፍል ውስጥ ነበር የሚሰራው። ለዚህ ዓላማ ነበር ከማዕከል ወደ መቀሌ የወሰዱት። ይህ ሁሉ ኃይል የተቀናጀው የሰሜን ዕዝ አስተዳደር በሆነው ብ/ጀኔራል ዘነበ ክፍሉ የኃላፊነት ቦታውን በመጠቀም ነበር።

ሰውዬው የሰሜን ዕዝ ከጀርባ ለመወጋቱ ቁልፍ ሚና የተጫወተ ከሃዲና ባንዳ ነበር። የዚህ ሰው እና የብ/ጀኔራል ከበደ መደምሰስ ቀላል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። ከተልዕኮ በኋላም ቢሆን ይህ ዘመቻ “የኢትዮጵያ ደመላሽ” ተብሎ መሰየም አለበት። የቀን ብቻ አይደለም የለሊትም ጅቦች ናቸው የተቀበሩት!!

ኢትዮጵያ ትስዕር❗️


ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና ለዐማራ ልዩ ኃይል ሰማዕታት❗️


FDREAL Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የመረጃ ተደራሽነታችሁን በጊዜና ሁኔታዎች ሳይገደቡ መጥናችሁ አሰራጩ። ወታደራዊ ድሉ በመረጃ ተደራሽነት ውድቀት መፈተኑ ሰማዕታቱን ዋጋ ማሳጣት ያስመስለዋል።

Via – ሙሉአለም ገ.መድህን

Leave a Reply

%d bloggers like this: