“የትህነግ ሰራዊት ወደ መቀለ እንዲገባ ታዟል” ሼትል

በኖርዌይ የትህነግ ቃል አቀባይ ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮል የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ሰራዊት ወደ መቀለ እንዲገባ መታዘዙንና ዛሬ ይኸውም ዛሬ ማታ ተግባራዊ እንደሚደረግ አመልክተዋል። በተመሳሳይ የአገር መከላከያ ሃይል ማተናከሩና ለመጨረሻ ውጊያ ዝግጅት ላይ መሆኑ እየተሰማና ይህንን የሚያሳይ ምስል እየወጣ ይገኛል። አብዛኞችን የሚያሰጋው ግን ከፍተኛ እልቂት እንዳይኖር ነው።

ሼትል አቶ ጌታቸው በሳተላይት ሊንክ እንደነገሯቸው ጠቅሰው እንዳስታወቁት የአገር መከላከያ ሃይል እያፈገፈገ ነው። ኢትዮ 13 ትናንት የትህነግ ሃይል ሲቪል መስሎ መቀለ ገብቶ መመሪያ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ጠሰን ጽፈን ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ማቆሙ፣ አሁን ደግሞ የትግራይ ቲቪ መዘጋቱ የነገሮችን መልክ መቀየር የሚያመላክቱ በመሆናቸው በመቀለ ዙሪያ ችግሩ መካረሩን አመላካች ነው። ሼትል በቲውተር ገጻቸው እንዳሉት ዛሬ ማታ የትህነግ ሃይል መቀለን ይቆጣጠራል።

ይህ ዜና ከመሰማቱ ቀድሞ በርካታ ዜጎች የኢትዮጵያ መከላከያ ከትግራይ ክልል ለቆ መውጣት እንዳለበት እየጠቆሙ ነበር። ምክንያታቸውም ጦርነቱ በጦርነት ህግ የሚከናወን ሳይሆን የዓለም አቀፍ ጫና ያለበት፣ በውስጥ ሲቪል መስለው ጥቃት የሚፈጽሙበት ከዚያም በላይ የአገር መከላከያ በግፍ የታረደበትና ክህደት የተፈጸመበት ምድር በመሆኑ ነው።

ቀደም አስተያየት ሰጪዎችን ጠቅሰን እንደጻፍነው የአገር መከላከያ የወልቃይትንና የራያን ህዝብ ከጥቃት የሚታደግበትን አግባብ አመቻችቶ ከትግራይ የሚለበት አግባብ ሊፈለግ እንደሚገባ አስታውቀን ነበር።

ሼትል አቶ ጌታቸውን ተክተው ባሰራጩት የህዝብ ግንኙነት ዜናቸው መሰረት ይፈጸም አይፈጸም ባይታወቅም ከመንግስት ወገን በይፋ የተባለ ነገር የለም። ታማኝ ምንጮች እንዳሉት ከሆነ ግን መከላከያ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ የዓለም አቀፍ ጫናው ትልቁን ሚና እንድተጫወተ፣ የትህነግ ታጋዮች ሲቪል እየሆኑና ሲቪል መሃል እየገቡ ስለሚሸሸጉ ለማጥቃት አለመቻሉ ትግራይን ለመልቀቅ ገፊ ምክንያት ሆኗል። በሌላ በኩል መንግስት ” ድርቅን ለፖለቲካ አዋለው” የሚለው ዘመቻ ሌላ መዘዝ ይዞ መምጣቱና ዓለም በትግራይ ጉዳይ ስለታወረ መንግስት ትግራይን ከመልቀቅና የሚያባክነውን ሃብት መቆተብ እንደሚሻለው እንደታመነ ተሰምቷል።

Image
ተጨማሪ ሃይል መቀለ እይገባ ነው

ሁሉም ዓይነት መረጃዎች ቢወጡም ትክክለናውን ጉዳይ መንግስት አላስታወቀም። ይህ እስከታተመ ድረስ ምንም የተባለ ነገር ባለመኖሩ የመንግስትን አቋም ማካተት አልቻልንም።

ይሁን እንጂ ከስፍራው ፈጣን መረጃ የሚያቀርበው ግዕዝ ሚዲያ እንዳለው ትህነግ በቆላ ተምቤን ተከቦ እየተጠቃ ነው። “አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለስድስት ወራት በተንቤን ገጠራማ ቦታዎች ሲሽሎኮሎክ ነበር፤ጀግናው የሃገር መከላከያ በተንቤን በሰራው ትልቅ ኦፕሬሽን አሸባሪው የህወሓት ቡድን አከርካሪው ተሰብሯል። አሸባሪው ቡድን በተንቤን ቀብሮት የነበረው የጦር መሰሳርያ ቆፍሮ እያወጣ ባለበት ሰአት ጀግናው የሃገር መከላከያ በወሰደው መብረቃዊ እርምጃ የቀበረው መሳርያ ሳይወስደው ጥሎት ፈርጥጧል። ውግያው በተለያዩ የትግራይ ቦታዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል። መከላከያ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። አሁን እየተካሄደ ያለው ውግያ ጠንከር ያለ ውግያ ነው የትግራይ ወጣት ለመከላከያ ሰራዊት እጅ በመስጠት ሂወቱን ማዳን ይገባዋል” ሲል ግዕዝ ሚዲያ ሃሳቡን አስፍሯል።

በኖርዌይ የሚኖሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር ግሩም / በፌስ ቡክ ገጻቸው ልጅ ግሩም ” እንደሚመስለኝ ዛሬ እና ነገ አብይ አሕመድ ጦርነቱ እንዲቋረጥ ይወስናል። ምርጫውን በማሸነፍ የበላይነት መያዙ የጦርነቱን ፍትሐዊነት ይቀንሰዋል። ትግራይ እስከ ተከዜ በነበራት አቀማመጥ ተቀይራ ሰላም ይወርዳል የሚል ግምት አለኝ። የትግራይ ውድመት ከሌላው ክልል ሲነጻጸር ቢያንስ በ200 አመት ወደ ኋላ ተመልሷል። “ነፃ አውጪ” የሚባሉ ፍጥረቶችን ማመን የሚያመጣው ውጤት ይኼው ነው። መቀሌ ውስጥ ብዙ እልቂት እንዳይኖር ድርድር ይሻላል። ” ሲሉ ” የለሊት ህልሜ” ያሉትን ጽፈዋል። የጻፉት ይህ ከመታተሙ ሰባት ሰዓት በፊት ነውልል

Leave a Reply