በመቀሌ በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ከወጣ በኋላ በመቀሌ ከተማ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመ ስለመሆኑ ተገልፆአል።

በዋነኛነት የኢሮም ሕዝብን ይወክላል የሚባለው ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በገፁ “የከዳን የእንደርታ ሕዝብ ነው።” በሚል በማንነት ነጥሎ ማጥቃት እንደተፈፀመ ገልፆአል። ይህ አካሄድ አደገኛ እና የእርስ በርስ ግጭት ሊያስከትል የሚችል ነው ብሏል።

የትህነግ ታጣቂዎች ከ36 በላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮችንና ሲቪል ሰራተኞችን መግደላቸው መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን በተለይም የእንድርታ አካባቢ ተወላጆች የጥቃት ሰለባ ሆነዋል ተብሏል።

Leave a Reply