ሙቀት ሰዎችን ጨረሰ

ካለፈው ሳምንት ዓርብ ጀምሮ ባሉት ቀናት በምዕራብ የባሕር ዳርቻ በሆነችው የካናዳዋ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛት በሙቀት ምክንያት ከ230 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተሰማ። የግዛቷ አስተዳዳሪ እንደተናገሩት ካለፈው ዓርብ ጀምሮ እስከ ሰኞ ዕለት ድረስ 130 ሰዎች የመሞታቸው ዜና የተሰማ ሲሆን እስከ ትናንት ማክሰኞ ድረስም ቁጥሩ 233 ደርሷል። የሞት ምክንያት የሆነውን ለማጣራት በተደረገው ጥረትም የሰሜኑን ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት መግቢያ የተከሰተው ከፍተኛ የሆነው ሞቃት የአየር ጠባይ መሆኑ እንደተደረሰበት ነው የተገለጸው። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የከባቢ አየር ከፍተኛ ሙቀት በተለይ ዕድሜያቸው የገፋ ሰዎችን፤ ጨቅላ ሕጻናት እና ልጆችን በአብዛኛው ለከፋ የጤና እክል አልፎ ተርፎም ለሞት ያደርሳል። ዘገባዎች እንደሚያሳዩት በምዕራብ ካናዳ የሙቀት መጠኑ 49,9 ዲግሪ ሴልሺየስ ደርሷል። DW

ካናዳ አዎንታዊ ምላሽ ሰጠች- እድሉን ተጠቀሙበት

ካናዳ የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎቹን ፍላጎት ለማሟላት የሚያደርገውን ሁለገብ ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎቹን ፍላጎት ለማሟላት የሚያካሄደውን ሁለገብ ጥረት እንደምትደግፍ ነው ካናዳ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ያስታወቀችው። የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኒው እና የአገሪቱ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ካርማ ጎልድ በጋራ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የወሰደውን የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ ካናዳ እንደምትቀበለው አስታውቀዋል። ከየትኛውም ወገን ይሁን በትግራይ ክልል በነበረው ቀውስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ ወሳኝ መሆኑንም አሳስባለች።ሁሉም ወገኞች ይህንን የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ እድል በመጠቀም ለግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄ ለመሻት እንዲጠቀሙበትና በቀጠናው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን አበርክቶ እንዲያደርጉም ነው ጥሪ ያቀረበችው።

አምነስቲ በትግራይ የበቀል ጥቃቶች አሳሰቡኝ አለ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቀሌ ከተማን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሉ ሲቪሎች አስቸኳይ ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው አመለከተ። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድ እና የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ ምክትል ዳይሬክተር ሣራ ጃክሰን ባወጡት መግለጫ፤ ድርጅታቸው ትግራይ ውስጥ የሲቪሎች ደህንነት በብርቱ እንዳሳሰበው አመልክተዋል።

ሲቪሉ ኅብረተሰብ ለወራት ጦርነቱን እና የመብት ጥሰቶችን እንዲሁም የጦር ወንጀልን ተቋቁሞ መቆየቱን በመጥቀስም የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች አካባቢውን ለቅቀው ሲወጡ እና የክልሉ ኃይል በስፍራው ሲተካ ለሲቪሎች ተገቢውን ከለላ ማረጋገጥ መሠረታዊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በመሆኑም «ቀጣይ ግድያ እና የጦር ወንጀል ከመፈጸም ሁሉም ወገኖች እንዲታቀቡ፤ በተለይም የበቀል ጥቃቶች በወታደሮቻቸውም ሆኑከእነሱ በወገኑሚሊሺያዎቻቸው እንዳይፈጸም ጥሪ እናቀርባለን።» ብለዋል። በተጨማሪም ሁሉም ወገኖች ለሲቪሎች ያለምንም መሰናክል ሰብዓዊ ርዳታ እንዲቀርብ እንዲሁም የመገናኛ ስልቶች ባለመኖራቸው ዳግም የኢንተርኔት፣ የሕትመትም ሆነ የራዲዮ እና ቴሌቪዥን አገልግሎት እንዲሠራ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

አስቀድሞ “ጁንታ ነበሩ” የተባሉ የትግራይ አስተዳደር አባላት የበረሃውን ሃይል ተቀላቀሉ

ዶ/ር ፋሲካ፣አቶ ካሕሳይ ፣ወ/ሮ ኢቴኔሽ እና አቶ ቴድሮስ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር አመራር የነበሩ ሲሆን ጁንታዎች ናቸው በሚል ከመጀመርያውንም ጀምሮ ለማጋለጥ ቢሞከርም የሚሰማ አካል አልነበረም።

መንግስት ትላንት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ካቢኔ ጥቃት እንዳይደርሳቸው ከመቐለ እንዲወጡ ያደረገ ሲሆን አራቱ ጁንታዎች ግን አደጋ እንዳይደርሳቹህ ከመቐለ ውጡ ቢባሉም አንወጣም እዚህ ነው የምንፈልገው ብለው የቀሩ ናቸው። በመጨረሻ ሰአት ላይ ጁንታነታቸው በግልፅ ያረጋገጡ ሰዎች ናቸው።

ጁንታ እንዴት ጁንታን ይፈራል። ዶ/ር ፋሲካ የክልሉ የጤና ቢሮ ሃላፊ ፣ ኢቴኔሽ የክልሉ የኮምኒኬሽን ሃላፊ ነበረች ፣ ቴድሮስ የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ በረ ከዛም ወደ ሴቶች ቢሮ ሃላፊ ነበረች እንዲሁም ካሕሳይ የክልሉ የፋይናንስ ሃላፊ ነበር። ለአራቱ ጁንታዎች ሹመት የሰጣቸው ዶ/ር ሙሉ ነጋ ነበር ዶ/ር ሙሉም መፈተሽ ያለበት ሰው ነው። ግዕዝ ሚዲያ እንደዘገበው

ክትባትና ውጤቱ

 በቻይናው ሲኖቫክ ባዮ ቴክ የተመረተው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት በህፃናት እና ወጣቶች ላይ ውጤታማ መሆኑን ዘ ላንሴንት የተሰኘው የሜዲካል ጆርናል ጥናት አመላከተ፡፡ ከክትባቱ ውጤታማነት ባሻገርም የጎንዮሽ ችግር እንደማያስከትልም ነው ጥናቱ ያመላከተው፡፡ ጥናቱ እድሜያቸው ከ3 እስከ 17 ዓመት የእድሜ ክልል በሚገኙ ህፃናትና ታዳጊዎች ላይ የተሞከረ ነው፡፡ ህጻናቱና ታዳጊዎቹ ክትባቱን በ28 ቀናት ልዩነት ሁለት ጊዜ እንዲወስዱ ተደርጓልም ነው የተባለው፡፡ በጥናቱ ከ500 በላይ ጤናማ ህፃናትና ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ከ96 በመቶ በላይ የሚሆኑት ቫይረሱን የመከላከል አቅም አጎልብተው ታይተዋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን መልቀቁ አገሪቱን ያፈራርሳል

የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን ለቆ መውጣት በሃገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል ሲሉ ከፍተኛ የአሜሪካ ወታደራዊ አዛዥ አስጠነቀቁ፡፡ በአፍጋኒስታን የአሜሪካ መራሹ ጦር አዛዥ ጀኔራል ስኮት ሚለር፥ የአሜሪካ ጦር ከሃገሪቱ እየለቀቀ መውጣቱን ተከትሎ “አፍጋኒስታን እጅግ አስቸጋሪ ጊዜን ልትጋፈጥ ትችላለች” ብለዋል፡፡

አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ወታደሮቿን ማስወጣት ከጀመረችበት ካለፈው ወር መጨረሻ ጀምሮም የታሊባን ታጣቂዎች በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠር መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታና ደህንነት ስጋቶች እንዳሉና የእርስ በእርስ ጦርነትም በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

በሃገሪቱ ለሚስተዋለው የፀጥታና የደህንነት ስጋት ታሊባን ከአሜሪካ ጋር የደረሰውን ስምምነት አለማክበሩ እና ወደ ሽምቅ ውጊያ መመለሱ ምክንያት መሆኑን በርካቶች ይናገራሉ፡፡ የታሊባን ታጣቂዎች አሁን ላይ 100 አካባቢዎችን እያስተዳድረን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአንጻሩ ከግንቦት ወር ጀምሮ ባለው ጊዜ ታጣቂዎቹ በሃገሪቱ ከሚገኙ 370 አስተዳደራዊ አካባቢዎች 50ዎቹን መቆጣጠራቸውን የሃገሪቱን ባለስልጣናት ዋቢ ያደረገው የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡ በርካታ አካባቢዎችን ከማስተዳደር ባለፈም መዲናዋ ካቡልን መክበባቸውም ነው እየተነገ ያለው፡፡

በሌላ በኩል የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽረፍ ጋኒ የሀገራቸው የፀጥታ አካላት በሙሉ አቅሙ የሰርጎ ገቦችን ጥቃት መመከት በሚችልበት ደረጃ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ ጦር እስከ ፈረንጆቹ መስከረም 11 ቀን ድረስ አፍጋኒስታንን ሙሉ በሙሉ ለቆ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡ ኤፍቢሲ እንደዘገበው

የጉበት ሀመም ምልክት

የጉበት ህመም (ሄፐታይተስ) አምስት ዋና ዋና ምልክቶች አሉት፡፡ ከጉበት ህመም አንዱ ምልከት ተደርጎ የሚወሰደው ድካም ሲሆን፥ የጉልበት ማጣት ፣ ከስራ ወይም ከእንቅስቃሴ በኋላ የሚመጣ ድካም ነው፡፡

ብዙ ጊዜ ምልክቱ ከጠዋት ይልቅ በማታ ያጋጥማል ፣ በጉበት በሽታ ምክንያት የሚመጣ ድካም አልፎ አልፎ የሚመጣና በተለያየ ጊዜ የድካሙ ክብደት የሚለያይ ነው፡፡

የማቅለሽለሽ ስሜት ደግሞ ሌላኛው የህመሙ ምልክት ሲሆን፥ ከፍተኛ የሆነ የጉበት ህመም ላይ የሚከሰት እና ከድካም የህመም ስሜት ጋርም አብሮ ሊኖር የሚችል ነው፡፡ ይህ የህመም ስሜት ሽታ ባላቸው ምግቦች እና ቅባት የበዛባቸው ምግቦች በመመገብ ይባባሳል፡፡ የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም ደግሞ በብዙ አይነት የጉበት በሽታዎች የሚከሰት ሲሆን፥ የሰውነት ቆዳ ማሳከክ ሌላው ህመሙ ምልክት ነው፡፡

Leave a Reply