የጸጥታው ምክር ቤት በሕዳሴው “ተወያዩ ከማለት ውጪ ሌላ መፍትሄ የለኝም” አለ

የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ወይይት አድርጓል። የወሩ የምክር ቤቱ ጠርናፊ የፈረንሳይ አምባሳደር ኖኮላስ ደ ሪቪዬር ከስብሰባው በሁዋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ምክር ቤት በሚቀጥለው ሳምንት በግድቡ ዙሪያ ሊወያይ እንደሚችል ጠቁመው ሶስቱ አገራት ከስምምነት ሊያደርሳቸው ወደሚችሉበት ድርድር እንዲመለሱ ከማበረታታት ውጪ ሌላ መፍትሄ ማፈላለግ እንደማይቻል ተናግረዋል።

ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴ ግድቡ ላይ የገጠማቸውን አለመግባባት በንግግር እንዲያስወግዱ ከማበረታታት የዘለለ ምንም ማድረግ እንደምይችል የገለጹትን ሰብሳቢ ጠቅሶ ሮይተርስ እንዳለው ምክር ቤቱ የተሰበሰበው ሱዳን ፣ ግብጽ እና የአረብ ሊግ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ጣልቃ እንዲገባ በጠየቁት መሰረት ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ እንደነበር አመልክቷል። ይሁን እንጂ ቀኑ በይፋ አልተገለጸም። ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሶስቱ አገራት ዘንድ ያለው ልዩነት አፍሪካ ህብረት መሪ አደራዳሪነት ብቻ እንደሚፈታ ማስታወቋ አይዘነጋም።

ግብፅ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ አሁን ያለበት ሁኔታ ለዓለም አቀፍ ሰላም አደገኛ ስጋት በመሆኑ የፀጥታው ም / ቤት አፋጣኝ ትኩረት ይስጥበት ስትል ለምክር ቤቱ ደብዳቤ መላኳን፣ የረብ ሊግ አገራትም በተመሳሳይ ይህን ማድረጋቸውና ለወገኖቻቸው ይበጃል የሚሉትን እንደምያደርጉ ማስታወቃቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply