በአርሲ በመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት በመታየቱ ነዋሪዎች አከባቢያቸውን ለቀቁ

በአርሲ ዞን ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ የመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት በመታየቱ 2 ሺህ 303 ነዋሪዎች አከባቢያቸውን ለቀው ወጡ።

ምልክቱ በታየበት በወረዳው ቢቴ ቀበሌ ቅኝት ያደረገው የፋና ባልደረባ ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቷል።

በኦሮሚያ ውሃና ኢንርጂ ቢሮ የመሬት ምህዳርና የውሃ ባለሙያ አቶ አብዱለጢፍ ሙሀመድ ምልክቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው ብለዋል።

የለካነው ማግኒቲውድ ውጤቱ ተመልሶ ለህብረተሰቡ እስኪነገር ድረስ ባሉበት መቆየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በዚህ በመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት ከአከባቢው ራቅ ብለው የሚኖሩ ሰዎች የምግብና የውሃ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

በአብደላ አማን FBC

Leave a Reply