ወደ አማራ ክልልና ትግራይ በመግባት ሁለቱም አካላት ለትግራይ ስጋት በማይሆኑበት ደረጃ እስኪደርሱ ጥቃት እንደሚሰነዝር ሲያስፈርራራ የነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ ባስቸኳይና ሙሉ በሙሉ ተኩስ እንዲያቆም ታዘዘ። ግንባሩ ጥቃት ለማድረስ በዛተው መሰረት በማድመ ሽራሮና ኮረም ጥቃት ለመክሰት ሞክሮ የፈለገው እንዳልሆነለት ተገለጸ።
የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ጸጥታው ምክር ቤት “በአስቸኳይ እና ሙሉ በሙሉ” ሲል ትህነግ የተኩስ አቁም እንዲያደርግ ያሳሰበ በይፋ የትግራይን ጉዳይ አንስቶ በተወያየበት ወቅት ነው።
የድርጅቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ሮዝመሪ ዲካርሎ ተጨማሪ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ስጋታቸውን አኑረዋል። አያይዘውም የተካረረ ግጭት ሊነሳ የሚችልበት ሁኔታ አለ።ይህ ደግሞ አሁን ያለውን የጸጥታ አግባ በቅጽበት ወደ ቀውስ ኪቀይረው እንደሚችል አስረድተዋል። ሃላፊዋ ስጋታቸውን ከዘረዘሩ በሁዋላ ነው “የትግራይ መከላከያ ኃይል የተኩስ አቁም ስምምነቱን በአፋጣኝ እና ሙሉ በሙሉ እንዲያጸድቅ እንጠይቃለን” ሲሉ የተደመጡት። ይህን ተከትሎ የትህነግ ሃላፊዎች በይፋ ምን እንደመለሱ አልታወቀም።
ይህን በሚልበት ወቅት አቶ ጌታቸው በተመድ ተሽከርካሪ ሲንቀሳቀሱ የሚያሳዩ ምስሎች በራሱ በተባበሩት መንግስታት የምግብ ድርጅት አስተባባሪ ሲሰራጭ ነበር። ተመድ በቀውስ ቀጠና ውስጥ ገለልተኛ ሆኖ የሚሰራ፣ ያለመነካት መብት ያለው፣ የህግ ከለላው የተጠበቀ ተቋም ሆኖ ሳለ በዚህ መልኩ አንድ ሉዓላዊ አገር ‘ሽብረተኛ” ያለችውን አካል ከላይ በተሰጠው ያለመነካት መብት ጥላ ስር አድርጎ አገልግሎት መስጠት አግባብ እንዳልሆነ፣ ተቋማቱ ገለልተኛ አለመሆናቸውን የሚያሳይ፣ ለወገንተኛነታቸው ገሃድ መውጣት ምስክር እንደሆነ በስፋት በየአቅጣጫው ሲገልጽ ነበር።
ተመድ ከመርሁ በሚጻረር መልኩ እንዲህ ባለ ተራ ተግባር ውስጥ ተነክሮ ከስፍራው የኢትዮጵያን መንግስት የሚደበድብ ሪፖርት ከስፍራው ሲደርሰው የሚያትምና እውነት ነው ብሎ ዓለም እንዲስት የራሱን ሚና የሚጫወት መሆኑ በበርካቶች በቲዊት እየተነቀፈ ነው።
ትህነግ የተኩስ አቁም እንዲያደርግ መታዘዙ ይፋ ከመሆኑ በፊት በኮረም ትንኮሳ አድርጎ እንደነበር አቶ ሬድዋን አስታውቀዋል። የኦቻ ሪፖርት ደግሞ ባድመና ሽራሮ ብሎ ባይጠቅስም ውጊያ እንደነበር ማስታወቁ አይዘነጋም።ኤርትራ ይህን አስመልክቶ ያለችው ነገር የለም። የአማራ ክልል ግን ትንኮሳውን እንዳመከነ ተመልክቷል። ከዚያም በላይ ክልሉ የትህነግ ሃይል በጦርነት ምንም ነገር ለማድረግ ከሞከር አጻፋ ለመመለስ በቂ ዝግትና ቁርጠኛነት እንዳለ አመልክቷል።
በተያያዘ ሌላ ዜና የአማራ ልዩ ሃይል አከባቢ ለቅቆ እንደማይወጣ በተባበሩት የኢትዮጵያ አምባሳደር በይፋ አመልክተዋል። በተባበሩት መንግስታት የፕሬስ ኮንፍራንስ ስለወልቃይት ጉዳይ ” የአማራ ሃይል ከምዕራብ ትግራይ” እንደሚወጣ የተጠየቁት በተባበሩት መንግስታት አምባሳደር ታዬ ስለአካባቢው ከፖለቲካው በላይ በቂ እውቀት እንዳላቸው ለማመላከት እንደ አጋጣሚ በእናታቸው ወገን የወልቃይት አከባቢ ተወላጅ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ደጋግማ ለወተወተቻቸው ጠያቂ “አከባቢው በትግራይ ክልል ስር የተጠቃለለው ህወሓት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነው። ይህም የሆነው ያለ ምንም ህጋዊ መሠረት እና የህዝብ ፍቃድ ነው። በመሆኑም የአከባቢው ነዋሪዎች ያነሱት የማንነት እና የወሰን ጥያቄ በህጋዊ መንገድ መፍትሄ እስከሚሰጠው ድረስ የአማራ ልዩ ሃይል ሆነ የመከላከያ ሰራዊት ከወልቃይት አከባቢ ለቅቆ አይወጣም። ይኸው ነው” ብለዋል። አምባሳደሩ ለጸጥታው ምክር ቤት የተዋጣለት ንግግር ማድረጋቸው በርካቶችን አስደስቷል።
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- የዜናው ሰም፣ ወርቅና “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የትህነግ ዜናውን አጣጣለለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ… Read more: የዜናው ሰም፣ ወርቅና “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የትህነግ ዜናውን አጣጣለ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council