አሸባሪ የህወሃት ቡድን በራያና አዘቦ ”የለውጥ ደጋፊዎች ናችሁ” በሚል ንጹሃን ዜጎችን እየገደለ መሆኑን የራያ ራዩማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤትና የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ጌታቸው ከበደ ገለጹ፡፡
ባላቸው ስጋት ምክንያት ከአስር ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንም ገልጸዋል።
ኢዜአ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል መልቀቅ ተከትሎ በራያ አካባቢ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ከአቶ ጌታቸው ከበደ ቆይታ አድርጓል፡፡
የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል የተናጠል የተኩስ ማቆም ውሴ መወሰኑን ተከትሎ አሸባሪ የህወሃት ቡድን ”የለውጥ ደጋፊ ናችሁ” በሚል ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱን አቶ ጌታቸው ከበደ ተናግረዋል፡፡
ቡድኑ ንጹሃንን እየገደለ፣ ቤትና ንብረቶችን በማውደም ራያ አዘቦ ተብሎ በሚታወቀው መሆኒ፣ መቻሬ፣ ጨርጨር እና ሓደ አልጋ በታባሉ አካባቢዎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡
ሽብርተኛ ቡድኑ ቀደም ሲል መከላከያ ወደ አካባቢው በገባበት ወቅት አቀባበል ያደረጉ፣ ስንቅ ያቀረቡ፣ ለሰራዊቱም የባህል ልብስ ያለበሱ ናቸው በሚል በሻይ መሸጥ የሚተዳደሩ፣ የባህል ልብስ የሚሰሩ፣ በጫማ ማጽዳት ስራ የተሰማሩ ደሃ ሰዎችን በግፍ በመግደል የጥፋት ስራዎችን መስራቱን አመላክተዋል፡፡
በዚህም በአካባቢው እየተፈጠረ ባለው ችግር ስጋት ምክንያት ከአስር ሺህ በላይ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መከላከያ ባለባቸው የራያ የገጠር እና የከተማ አካባቢዎች በርታህላ፣ ታኦ፣ ዳዩ፣ አላማጣ፣ እንዲሁም ራያ ቆቦ ከተማ ጭምር ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል፡፡
አሸባሪው የህወሃት ቡድን ”እናስተምራችዋለን” በሚል ሰበብ በርካታ ወጣቶችን በሲኖ ትራክ መኪና ጭነው በመውሰድ ኢ ሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸሙባቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
የለውጥ ደጋፊዎች ናችሁ በሚል የጊዜያዊ አስተዳደር አባላት እና የነዋሪዎች መኖሪያ የሆኑ ከአራት መቶ በላይ ቤቶችን መቃጠላቸውን ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል መቀሌ እና በሌሎች ከተሞች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና መከላከያን ተባብራችኋል ያላቸውን ንጹሐን ላይ ግድያ እየፈጸመ እንደሚገኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል።
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል
- የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ… Read more: የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?
- ታደሰ ወረደ ” የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም” ሲሉ አዲሱን ግጭት የሚጠበቅ እንደሆነ አመላከቱየትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በራያ አላማጣ ዳግም ወረራ እየተካሄደ መሆኑ ይፋ መደረጉን ተከትሎ… Read more: ታደሰ ወረደ ” የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም” ሲሉ አዲሱን ግጭት የሚጠበቅ እንደሆነ አመላከቱ