የራያ አዘቦ ህዝብ በአሸባሪው ሕወሃት ዋጋ እየከፈለ መሆኑን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።የአገር መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ ከወጣ ጀምሮ የራያ አዘቦ ተወላጆች የሆኑ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንም ፓርቲው አስታውቋል።
በተጨማሪም ከ30 ሺህ በላይ ከአካባቢያቸው ተሰደዋል።የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የወጣቶች ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጥጋቡ ጎበና እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የራያ አዘቦ መኾኒ ከንቲባ አቶ አለ በርዎ ከኢዜአ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።የራያ አዘቦ ህዝብ ባለፉት ሶስት ዓመታት አገራዊ ለውጡን ተቀብሎ የህዝቡን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።
ህዝቡ በአሸባሪው ሕወሃት ከማንም በላይ ጭቆና ሲደረስበት እንደነበር አስታውሰው፤ ክልሉን መከላከያ ከያዘው ጀምሮ በተለይ አርሶ አደሩ ተረጋግቶ ወደ እርሻው መግባቱን ተናግረዋል።ሆኖም በአሁኑ ወቅት መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደውን የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ተከትሎ ህዝቡ በአሸባሪው ሕወሃት ዋጋ እየከፈለ መሆኑን ገልጸዋል።
የትግራይ አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውንና ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ መንግስት ያደረገው መልካም ተግባር የራያ አዘቦ ህዝብ በአሸባሪው ሕወሃት ግድያና ሰቆቃ እየደረሰበት መሆኑን ጠቁመዋል።
ክልሉ በመከላከያ ቁጥጥር ስር እያለ የራያ አዘቦ አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው፤ “አሁን ከአካባቢው መልቀቁን ተከትሎ ችግር ውስጥ በመግባቱ መፍትሄ ያስፈልገዋል” ብለዋል። የራያ አዞቦ ህዝብ ከዚህ የከፋ ጉዳት ከማስተናገዱ በፊት መንግስትና መከላከያ እንዲደርስለትም መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው መግለቻቸው… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories ትግራይ – ችግር ፈጣሪው ትህነግ መፍትሄ ሆነ፤ መንግስት “ራሳችሁ ጨርሱ” ብሏልMarch 6, 2023 ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ