ሰበር ዜና – የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጀመሩን ኢትዮጵያ ገሃድ አደረገች

የክረምቱን መጠናክረ ተከትሎ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቧን መሙላት መጀመሯን ለግብጽ የመስኖ ሚኒስትር ኦፊሳል ደብዳቤ በመላክ ማሳወቋን አህራም ኦንላይን አስታወቀ። ዜናውን የዓለም ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ነው።

በሰበር ዜና “በስፋት እመለስበታለሁ” ብሎ ዜናውን ያሰራጨው አልሃራም “ሁለተኛው ሙሌት ኢትዮጵያ አስገዳጅ ውል ሳትፈርም ያከናወነችው ነው” ሲል ስጋና ደሙን አክሎበታል። የውሃ ሙሌቱ የተተናከረ ክረምት በመኖሩ ምክንያት ምንም ዓይነትችግር እንደማያስከትልም አላመላከተም።

በተቃራኒው ኢትዮጵያዊያን ዜናውን በደስታ እያሰራጩት ይገኛሉ። ግድቡ ለኢትዮያዊያን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ በሁሉም ዘነዳ ተመሳሳይ አቋም የተያዘበት ጉዳይ ነው። በቅርቡ ከትሀነግ የድብቅ ስብሰባ የተገነው ሰነድ ልግብጽ በመታዘዝ የህዳሴውን ግድብ መምታት አንዱ የፍላጎት ማስፈጸሚያ አጀንዳ ሆኖ መያዙን የመንግስት ስለላ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ይህ ይፋ ከመሆኑ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመከላከያ ሰራዊት ግድቡን አስመልክቶ “እስከ ደም ጠብታ” በሚል ዝግጁነታቸውን ሲገልጹ ነበር። በዛሬው የፓርላማ ውሎ የግድቡ መሞላት ሱዳንንም ሆነ ግብጽን እንደማይጎዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መናገራቸው ያታወሳል።

የህዳሴውን ግድብ መሞላት ለምትናፍቁ ወገኖች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!


Leave a Reply