ባለፈው ሳምን መጨረሻ ቃል በገባው መሰረት ፍላጎት ያላቸው አካላት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ የበረራ መፍቀዱን መንግስት አስታወቀ። ዜናው ፍቃድ መሰጠቱን እንጂ ስለ ፍተሻና የደህንነት ጉዳይ ያለው ነገር የለም።
የኢትዮጵያ መንግስት ፍላጎት ያላቸው አካላት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ የበረራ ፍቃድ እንደሰጠ ያስታወቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ጽህፈት ቤት ነው።
ፈቃዱ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ክፍት መሆኑንንም አመልክቷል። ለሰብአዊ በሚል ወደ ትግራይ የሚበሩት አዉሮፕላኖች እግረመንገዳቸውን መሳሪያና ሌሎች ትህነግን ለማጠናከር የሚጠቅሙ ቁሶችን ለማጋጋዝ ተግባር ሊወሉ እንደሚችሉ ፍርሃቻ ስላለ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል ከመግባታቸው በፊት አስፈላጊው የጸጥታ ፍተሻ እንደሚደረገ አቶ ሬድዋን ለዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ባልደረቦች መናገራቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።