የኢቶጵያ መንግስት የኢምባሲዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ፣ ይህም የሚሆነው ኤምባሲዎቹ ወጪ ከማብዛታቸው በላይ የግለሰቦች ምሽግና መጠቀሚያ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ለተወሰኑና ለተመረጡ አምባሳደሮች በደብዳቤ ጥሪ መላኩን አዲስ ስታንዳርድ ” ሰበር” ሲል ዘግቦታል።
ደብዳቤው በገሃድ የተሰራጨና ባለፈው ዓመት የተጠናው ጥናት ውጤት መሆኑን መንግስት በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ በዲፕሎማሲው ረገድ ፋይዳ የሌላቸው ዲፕሎማቶች አገሪቱን ዋጋ እንዳስከፈሏት በተደጋጋሚ ሲተች ነበር። በዚሁ መነሻ “እንደቀድሞው በጅምላ በግዢ ዲግሪ የተመረቁ ” ሳይሆኑ አዳዲስ ዲፕሎማቶች ተመልምለው ሲሰለጥኑ እንደነበር መንግስት አስታውቆ ነበር።
የዚህ አካል እንደሆነ የተነገረለት የማስፈጸም ጅማሮ ሲሰሩበት ለነበረው ሚሲዮን ንብረት አስረክበውወደ አገር ቤት በመመልስ ሪፖርት እንዲያደርጉ የታዘዘበትን ደብዳቤ ደብዳቤው ከተላከለት አንድ አካል በመውሰድ “ሰበር” ዜና በሚል አዲስ ስታንዳርድ አትሟል። በደብዳቤው እንደተጠቀሰው ፣ጥሪ የተደረገላቸው እስከ ነሃሴ 15 ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ተሾመ ቶጋ፣ ኩማ ድሪባ፣ አይነት ዲፕሎማቶች ያሏት አገር መሆኗ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ለዲፕሎማሲው ቅረበት ያላቸው በተደጋጋሚ ሲተቹ እንደነበር።
የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ያነጋገራቸው የብልጽግና ከፍተኛ አመራር ” ሰበር ዜና መሆን ያለበት መንግስት ህዝብን ሰምቶ እርምጃ ወሰደ የሚለው በሆነ ነበር” ሲሉ ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል።
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared three… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in the Security Council… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official, while Iranian state… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report
- ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችምዓለም ባንክና የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ የጠቀችውን ብድር ለመፍቀድ ያቀረቡት ዋና ቅድመ ሁኔታ የብርን የመግዛት አቅም ዝቅ ማድረግ ወይም በነጮቹ አፍ ዲቫሉዌት… Read more: ዓለም ባንክና መንግስት በአሜሪካ እየመከሩ ነው፤ ኢትዮጵያ ” የብርን የምንዛሬ አቅም ቀንሱ” ጥያቄ አልተቀበለችም
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕወሓትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቀ – ቅንጅት “በተጭበረበረ ተግባር”እንዲሰረዝ ተወስኗልJanuary 19, 2021 በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ