የኢቶጵያ መንግስት የኢምባሲዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ፣ ይህም የሚሆነው ኤምባሲዎቹ ወጪ ከማብዛታቸው በላይ የግለሰቦች ምሽግና መጠቀሚያ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ለተወሰኑና ለተመረጡ አምባሳደሮች በደብዳቤ ጥሪ መላኩን አዲስ ስታንዳርድ ” ሰበር” ሲል ዘግቦታል።
ደብዳቤው በገሃድ የተሰራጨና ባለፈው ዓመት የተጠናው ጥናት ውጤት መሆኑን መንግስት በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ በዲፕሎማሲው ረገድ ፋይዳ የሌላቸው ዲፕሎማቶች አገሪቱን ዋጋ እንዳስከፈሏት በተደጋጋሚ ሲተች ነበር። በዚሁ መነሻ “እንደቀድሞው በጅምላ በግዢ ዲግሪ የተመረቁ ” ሳይሆኑ አዳዲስ ዲፕሎማቶች ተመልምለው ሲሰለጥኑ እንደነበር መንግስት አስታውቆ ነበር።
የዚህ አካል እንደሆነ የተነገረለት የማስፈጸም ጅማሮ ሲሰሩበት ለነበረው ሚሲዮን ንብረት አስረክበውወደ አገር ቤት በመመልስ ሪፖርት እንዲያደርጉ የታዘዘበትን ደብዳቤ ደብዳቤው ከተላከለት አንድ አካል በመውሰድ “ሰበር” ዜና በሚል አዲስ ስታንዳርድ አትሟል። በደብዳቤው እንደተጠቀሰው ፣ጥሪ የተደረገላቸው እስከ ነሃሴ 15 ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ተሾመ ቶጋ፣ ኩማ ድሪባ፣ አይነት ዲፕሎማቶች ያሏት አገር መሆኗ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ለዲፕሎማሲው ቅረበት ያላቸው በተደጋጋሚ ሲተቹ እንደነበር።
የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ያነጋገራቸው የብልጽግና ከፍተኛ አመራር ” ሰበር ዜና መሆን ያለበት መንግስት ህዝብን ሰምቶ እርምጃ ወሰደ የሚለው በሆነ ነበር” ሲሉ ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል።
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ የሚሊሻ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ የተለመደው… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና ፖለቲካውን ለሚረዱ የዜናው ሰምና ወርቅ… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the Council underscored the need… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን ጊዜ ቀጠሮ መዝገብን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል። ቀሲስ… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ