የዕርዳታ እህል ነው የጫንኩት ያለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከሱዳን በቀጥታ አሰልፎ ወደ ኢትዮጵያ ያስገባቸውን ዘጠኝ ከባድ መኪኖችን ” አላስፈትሽም” በማለቱ ፖሊስ አስቁሟል። ” መንግስት እርዳታ አስተጓጎለ” የሚል መግለጫ ይጠበቃል።
በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ተገቢ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ሲል መኪኖቹን አስቁሞ ፍተሻ ላድረግ ማለቱን ያስታወቁት በስፍራው ያሉ እማኞች ናቸው። የዕርዳታ ቁስ ጭነዋል የተባሉት ሎቤድ ተሳቢዎች ከሱዳን ተነስተው ወደ ትግራይ ለመሄድ፣ በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ፍላቂት ከተማ ከደረሱ በኋላ ፖሊስ የጸጥታና የጥንቃቄ ጥያቄ ያነሳው።
በአስቸኳይ ፍተሻ ተደርጎ እርዳታው ለህዝቡ እንዲደርስ የተጠየቁት ክፍሎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የፍላቂት ከተማ ፓሊስ ዘጠኙንም የ WFP ተሽከርካሪዎች ከሁለት ማርክ 2 አጃቢ መኪኖች ለጊዜው ባሉበት ሳይነቀሳቀሱ እንዲቆዩ አድርጓል።
WFP ከትሀነግ አመራሮች ጋር የድርጅቱ መርህ በማይፈቅድው ደረጃ በገሃድና በድብቅ እየፈጸመ ያለው ተግባር ለጥርጣሬው መነሻ መሆኑን ተመክቷል። በፈተሻ መሳሪያ ከተገኘ የዓለም ምግብ ድርጅት በአደባባይ በማስረጃ ስለሚወገዝ የአካባቢው አስተዳደር ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ መከናወን ያለበትን አከናውኖ ጉዳዩን እልባት እንዲያበጅለት ዜናውን ያሰራጩ ገልጸዋል።
ዜናው በማህበራዊ ገጾች የዓይን ምስክሮች ካሰራጩት ውጭ ከመንግስት ወገንም ሆነ ከዓለም ድርጅት በኩል እስካሁን በገሃድ የተባለ ነገር የለም። ትህነግ እርዳታን ሃይሉን ለማደስ እንደሚጠቀምበት ልምዶች ምስክር መሆናቸው በተደጋጋሚ የተባለ ጉዳይ ነው። ድርድርን አስመልክቶም ቅድሚያ ያስቀመጠው ነጻ በረራና የየብስ ኮሪዶር መሆኑ ይታወሳል።
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of Somaliland in a… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው መግለቻቸው ላይ አክለዋል። በኢትዮጵያ… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring a new dynamism… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥብቅ መመሪያ አወጣ – ጥይት መተኮስ ተከለከለ፤ በህግ ያስቀጣልFebruary 19, 2021 “እዚያ ቤት የተመከረ ምክር እኛምይመከራል!?!”March 19,… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ