የዕርዳታ እህል ነው የጫንኩት ያለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከሱዳን በቀጥታ አሰልፎ ወደ ኢትዮጵያ ያስገባቸውን ዘጠኝ ከባድ መኪኖችን ” አላስፈትሽም” በማለቱ ፖሊስ አስቁሟል። ” መንግስት እርዳታ አስተጓጎለ” የሚል መግለጫ ይጠበቃል።
በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ተገቢ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ሲል መኪኖቹን አስቁሞ ፍተሻ ላድረግ ማለቱን ያስታወቁት በስፍራው ያሉ እማኞች ናቸው። የዕርዳታ ቁስ ጭነዋል የተባሉት ሎቤድ ተሳቢዎች ከሱዳን ተነስተው ወደ ትግራይ ለመሄድ፣ በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ፍላቂት ከተማ ከደረሱ በኋላ ፖሊስ የጸጥታና የጥንቃቄ ጥያቄ ያነሳው።
በአስቸኳይ ፍተሻ ተደርጎ እርዳታው ለህዝቡ እንዲደርስ የተጠየቁት ክፍሎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የፍላቂት ከተማ ፓሊስ ዘጠኙንም የ WFP ተሽከርካሪዎች ከሁለት ማርክ 2 አጃቢ መኪኖች ለጊዜው ባሉበት ሳይነቀሳቀሱ እንዲቆዩ አድርጓል።
WFP ከትሀነግ አመራሮች ጋር የድርጅቱ መርህ በማይፈቅድው ደረጃ በገሃድና በድብቅ እየፈጸመ ያለው ተግባር ለጥርጣሬው መነሻ መሆኑን ተመክቷል። በፈተሻ መሳሪያ ከተገኘ የዓለም ምግብ ድርጅት በአደባባይ በማስረጃ ስለሚወገዝ የአካባቢው አስተዳደር ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ መከናወን ያለበትን አከናውኖ ጉዳዩን እልባት እንዲያበጅለት ዜናውን ያሰራጩ ገልጸዋል።
ዜናው በማህበራዊ ገጾች የዓይን ምስክሮች ካሰራጩት ውጭ ከመንግስት ወገንም ሆነ ከዓለም ድርጅት በኩል እስካሁን በገሃድ የተባለ ነገር የለም። ትህነግ እርዳታን ሃይሉን ለማደስ እንደሚጠቀምበት ልምዶች ምስክር መሆናቸው በተደጋጋሚ የተባለ ጉዳይ ነው። ድርድርን አስመልክቶም ቅድሚያ ያስቀመጠው ነጻ በረራና የየብስ ኮሪዶር መሆኑ ይታወሳል።
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው” የሚለው የዋዜማ ዜና ፖለቲካውን ለሚረዱ የዜናው ሰምና… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the Council underscored the… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ የ3 ግለሰቦችን ጊዜ ቀጠሮ መዝገብን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተመልክቷል።… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ