የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ዕርዳታን ለጦርነት እንዴት እንደተጠቀመበት የሚያውቁ ዜጎች ዛሬም መንግስት ከደረግ ስህተት በመማር ለአፍታም ቸል እንዳይል ጥሪ እያሰሙ ነው። በእርዳታ ስም የገቡ ድርጅቶቻቸው አቋማቸውና አካሄዳቸው የማይምር መሆኑንን የሚያሳዩ ምልክት በመታየታቸው አንዳንዶች ስጋት እንዳላቸውም እየጠቀሱ ነው።
በማህበራዊ ሚዲያ፣ በተለያዩ አውዶችና በጎንዮሽ ሕዝብ ” የእርዳታ ቁሳቁስ ሊፈተሽ ይገባል። መፈተሽ ከደህንነታችን አንጻር ለነገ የሚባል አይደለም። ለጋሾችም ቢሆኑ ፍተሻን የሚቃወሙበት አንዳች ህጋዊ መሰረት የላቸውም” ብለዋል። ኢዜአ ያነፋገራቸው ባለሙያ የሚከተለውን ብለዋል።
የተራድኦ ድርጅቶች ከተፈቀደላቸው ተግባር ውጭ እንዳይንቀሳቀሱ መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንዳለበት የህግና የታሪክ ምሁር ዶክተር አልማው ክፍሌ ተናገሩ።የተራድኦ ድርጅቶች ከአድሎ በጸዳ መልኩ ሰብዓዊነት፣ ገለልተኝነትና ነጻነታቸውን ጠብቀው በችግር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለመርዳት የተቋቋሙ ናቸው።
ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ ድርጅቶች ደግሞ በየትኛውም የዓለም ጥግ ያሉ አገሮች ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግሮች ወይም ግጭት ሲገጥማቸው ድጋፍ ለማድረግ ይገባሉ።በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ የህግና የታሪክ ምሁር ዶክተር አልማው ክፍሌ፤ አገሮች ቀውስ በሚገጥማቸው ጊዜ የተራድኦ ድርጅቶች የሚያደርጓቸው ሰብዓዊ ድጋፎች ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ያስረዳሉ።ነገር ግን እነዚህ ድርጅቶች በአንድ አገር ውስጥ ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲንቀሳቀሱ መከተል የሚጠበቅባቸው መብቶችና ግዴታዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
የተራድኦ ድርጅቶቹ ሥራቸውን ሲያከናውኑ የአገር ሉዓላዊነትን ባከበረ መልኩ መሆን እንዳለበት አመልክተው፤ በውስጣዊ ፖለቲካ እንዲሁም ህዝብንና አገርን ከሚጎዱ እንቅስቃሴዎች መታቀብ እንዳለባቸውም አንስተዋል።መንግስት በትግራይ የወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ ተከትሎ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ወደ አካባቢው መግባታቸውን ጠቅሰው፤ የድርጅቶቹ ሰራተኞች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ተገቢ ባለሆነ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እየታዩ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የተራድኦ ድርጅት አባላቶች ተገቢ ባልሆነ መልኩ በህዝብና መንግስት ላይ የሽብር እንቅስቃሴን አንግበው ለሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የመወገን አዝማሚያ እንደሚታይም ጠቅሰዋል።በአሸባሪነት የተፈረጀው ድርጅት አባላት በተራድኦ ድርጅቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱንም ለአብነት አንስተዋል።
አሸባሪው “ህወሃት ደርግን ለመጣል ባደረገው የትጥቅ ትግል የተራድኦ ድርጅቶች የጦር መሳሪያ በማቀበል ሲያግዙ ነበር” ያሉት የህግና ታሪክ ምሁሩ፤ መንግስት ከደርግ ዘመን ሂደቶች ትምህርት በመውሰድ የተራድኦ ድርጅቶች የሚያደርጉትን ያልተገባ እንቅስቃሴ መከታተል እንዳለበት ገልጸዋል።በእርዳታ ስም ሌሎች የአገሪቱን ህግ የሚጥሱ ተግባራት እንዳይከናወኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው፤መንግስት አስፈላጊውን ፍተሻ የማድረግና እርዳታው ለተገቢው አካል መድረሱን ማረጋጋጥ እንዳለበትም ተናግረዋል።መንግስት ግብረ ሃይል በማቋቋም የቁጥጥር ስራውን ማከናወን እንደሚችልም ዶክተር አልማው ተናግረዋል።
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን አስጠንቅቆ ” የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories ” አልፎ እንዳይቆጨን … እድል እንዳያመልጥ ” ቁ. 1April 10, 2024 አዲሱ ሚኒስትር “የሰላም እጦት”February 23, 2024 የባህር በር ህልውናችን!! አብይ አህመድ… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared three days… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in the Security Council to… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official, while Iranian state media… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report