አዲስ ዲፕሎማሲ አሁኑኑ!! ” 115 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አገር ባልተገባ ጫና ለማፍረስ መሞከር ቅድሚያ የሚጎዳው ጫና ፈጣሪዎቹን ነው”

ስምንት የህዝብ ግንኙነት የሚሰሩላቸው ድርጅቶ ቀጥረዋል። ከለውጡ በፊት በወር አርባ ሺህ ዶላር ይከፍሏቸው ። ከልወጡ በሁዋላ ከ100 እስከ 140 ሺህ ዶላር እንደሚከፍሏቸው መረጃ አለኝ። ይህን ሁሉ ሃብት እያፈሰሱ ነው ኢትዮጵያ ስሟ እንዳየሳ፣ ጉዳይዋ እንዳይሰማ ሁሉንም በሮች የተቆጣጠሩት። ስልጣን ላይ እየሉ ባከማቹት የዘርፊያ ሃብት የህዝብ ግንኙነቱን ስራ በገንዘብ ቆላልፈው ይዘውታል። እኛ ደግሞ ዲፖሎማቶቻችን ብር ከመሰብሰብ ያልፈ ስራ አይሰሩም። በዚህ አካሄድ መቀጠል አይቻልም። ጊዜው የአዲስ አሳብ፣ አሰራርና ትገበራ ነው…

ዶ/ር ሃይማኖት አሰፋ ናደው በትምህርታቸው የፋርማሲ ሳይንስ ባለሙያ ቢሆኑም ፍልስፍና፣ ታሪከ፣ ሳይንስ፣ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ ወዘተ ጉዳዮች ላይ ማንበብ፣ ማጥናት እና መመራመር እንደሚወዱ ግል ታሪካቸው ያስረዳል። ከጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ አስተዳደር ጀምሮ በዩኒቨርሲቲ በማስተማር፣ በዓለምአቀፍ ልማት፣ በምርምር፣ በማማከር፣ በትርፍ አልባ ድርጅቶች እና በመንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች እስከ አመራር የዘለቀ የሥራ ልምድ ያካበቱ ናቸው።

ዶ/ር ሃይማኖት

ጋሙጎፋ ሳውላ ከተማ ተወልደው ያደጉት ዶክተር ሃይማኖት ለሰው ማሰብ፣ ለሰው መኖር፣ የሰዎችን ስቃይና ችግር መካፈል ካስተዳደጋቸውና ከአካባቢያቸው ማኅበረሰብ እንድተማሩ ይናገራሉ።ምንም እንኳን ኑሯቸው ከአገር ቤት፣ ከሚወዱት ማህበረሰብ ርቆ ቢኖርም በየዕለቱ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ከማሰብ ወደኋላ አላልሁም። ይህንኑ ያደጉበትን እሴት በመጠበቀ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ የሚሰጠው አመለካከታቸውን እያራመዱ ነው።

የሁለት ሴት ልጆች አባት የሆነው ሃይማኖት፤ እናታቸው ወ/ሮ ታየች ዘውዴ ወልደሚካኤል የመኖር ምክንያታቸው እንደሆኑ ግለታሪካቸው ላይ በጉልህ አኑረዋል። ኢትዮ 12 አሁን ላይ ” አዲስ አሰራር፣ አዲስ አሳብና አዲስ ዲፖሎማሲ” በሚል በጀመሩት ስራ ዙሪያ እንግዳ አድርገናቸዋል። ዶክተር ሃይማኖት ዜጎች ሁሉ አቅም ያላቸው የአገራቸው አምባሳደር ይሆኑ ዘንዳ የሚያተባበርና የሚመራ Ethiopian Americans Voting Bloc EAPAC Global የሚባል ድረጅት መስረተዋል። ወደ ቃለ ምልልሱ


ኢትዮ 12 – እንደ መነሻ ከዋናው ትኩረት ለመነሳት፣ አሜሪካኖች ሊረዱት የሚገባቸውና የሳቱት፣ እርስዎና ድርጅትዎ አጥበቀው ለማሳወቅ የምትጥሩበት ቁልፍና ከባዱ ጉዳይ ምንድን ነው

ዶ/ር ሃይማኖት – ኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና እየተደረገ ነው። ይህ አላስፈላጊ ጫና ኢትዮጵያ ላይ አደጋ ካመጣ የመጀመሪያዋ ጥቅሟን የምታጣ አገር አሜሪካ ናት።፡ኢትዮጵያ 115 ሚሊዮን ህዝብ አላት። ጫናው በዚህ መልኩ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ወደ አላስፈለጊ መበትን ልታመራ ትችላለች። ይህ ከሆነ ምስራቅ አፍሪቃ የአክራሪ መናኸሪያ ይሆናል። ሰፊ ቁጥር ያለው ሕዝብ ለስደትና ለሰብአዊ ቀውስ ይዳረጋል። ወደ አውሮፓ የሚሰደደው ስፍር ቁጥር የለውም። በጥቅሉ ማህበራዊ ቀውሱ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ቀጠናው እንዳለ ይናወጣል። በዚህ ቀውስ ውስጥ አሜሪካንም ሆነች አውሮፓ አንዳች አያተርፉም። ፍላጎታቸም አይሟላም። በተቃራኒው 115 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ ሰላሟ የተረጋገጠና አንድነቷ የተጠበቀ ሲሆን ጥቅማቸው እንደሚከበር ቢያውቁም በቂ መረጃ እንዲሰጣቸው አልተደረገም። ከዚህ አንጻር መሰራት እንዳለበት እናምናለን።

ኢትዮ12 – አሜሪካኖች ኢትዮጵያን መስማት አቁመዋል ይባላል? ለመሆኑ ትገናኛላችሁ? በምን ደረጃ?

ዶ/ር ሃይማኖት – እንገናኛለን። ጉዳዩ መስማት የመፈለግና ያለመፈለግ ሳይሆን ችግሩ ያለው ቀድሞ መረጃ ማድረሱ ላይ ነበር። ያገኘናቸው የአሜሪካ ህግ አውጪዎች የመረጃ ችግር እንዳለባቸው ነግረውናል።

ኢትዮ12ያስደነግጣል ምን ማለት ነው?

ዶ/ር ሃይማኖት- አያስገርምም ለዓመታት አገራችን የዲፕሎማሲ አቅጣጫዋ ድርጅት ላይ የተቸከለና በመርህ ደረጃ የተቃኘ አልነበረም። ስለዚህ ለውጡ ሲመጣ ለድርጅት ጥቅም የተሰመሰረተው መስመር በተቋቋመለት መስመር ቀጠለ። እንደ አገር ግን ያው እንደታየው ውጤቱ ሽንፈት ሆነ። የመረጃ እጥረቱና ክፍተቱ መነሻው ይህ ነው። ቀደሞ ያልተሰራ ስራ …

ኢትዮ12- የሚቃና ይመስልዎታል?

ዶ/ር ሃይማኖት– በሚገባ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ስንለው የነበረውን ሰምተዋል። መንግስት ሰማ ማለት ነው። ተወደደም ተጠላም ዲፕሎማሲው በህዝብ መሰራት አለበት። ፑብሊክ ዲፕሎማሲ እጅግ ወሳኝ ነው። ከአሁን በሁዋላ የዲፕሎማሲው ስራ የሚሰራው እንደ እኛ ባሉ ድርጅቶችና በጎ ፈቃደኞች ነው። አሁን የሚቀረው ለሃላፊነቱ መዘጋጀት ነው። በቀናነት፣ በታማኝነትና በፍጹም ፈቃደኛነት ከሰራን እንቀይረዋለን። ዋና ጉዳይ አዲስ አሳብ፣ አዲስ አሰራርና አዲስ የትግበራ መንገድ መከተሉ ላይ ነው። በቀድሞው የስህተት መንገድ መጓዝ ለሌላ ስህተት ይዳርጋል እንጂ ወደ ከፍታ አይወስድም። ያለፈው ሽንፈታችን ጥሩ አስተምሮናል።

ኢትዮ12- አሁን ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ዘመቻ የተደራጀና ማዘዣ ጣቢያ ያለው እንደሆነ እየተነገረ ነው። ታላላቅ የሚባሉ መንግስታት፣ መገናኛዎችና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ እየተሳተፉበት ነው። እርስዎ በትክክል ምን ተፈልጎ እንዲህ ያለ ዘመቻ እንደተከፈተ ያውቃሉ? ወይም መረጃ አለዎት?

ዶ/ር ሃይማኖት- መቶ በመቶ የሚያውቁት ዘመቻውን የሚያካሂዱት የጠቀስካቸው ክፍሎች ናቸው። ግን የተጠጋጋ መልስ መስጠት ይቻላል።

ኢትዮ12- መፍትሄ ለመፈለግ ዋናውን ጉዳይ ማወቅ አስፈላጊ እንደሆነ ስለሚታመን ነው ጥያቄውን ያነሳሁት፤

ዶ/ር ሃይማኖት- ትክክል ነው እንዳልኩት እጅግ በተቀራረበ ደረጃ ከዚህ ሁሉ ዘመቻ ያለውን ፍላጎት እንረዳለን።

ኢትዮ12- ይቀጥሉ ዶክተር

ዶ/ር ሃይማኖት– ትህነግ ስምንት የህዝብ ግንኙነት የሚሰሩላቸው ድርጅቶች ቀጥሯል። ከለውጡ በፊት በወር አርባ ሺህ ዶላር ይከፍሏቸው ነበር። ከልወጡ በሁዋላ ከ100 እስከ 140 ሺህ ዶላር እንደሚከፍሏቸው መረጃ አለኝ። ይህን ሁሉ ሃብት እያፈሰሱ ነው ኢትዮጵያ ስሟ እንዳየሳ፣ ጉዳይዋ እንዳይሰማ ሁሉንም በሮች የተቆጣጠሩት። ስልጣን ላይ እየሉ ባከማቹት የዝርፊያ ሃብት የህዝብ ግንኙነቱን ስራ በገንዘብ ቆላልፈው ይዘውታል። እኛ ደግሞ ዲፖሎማቶቻችን ብር ከመሰብሰብ ያለፈ ስራ አይሰሩም። በዚህ አካሄድ መቀጠል አይቻልም። ጊዜው የአዲስ አሳብ፣ አሰራርና ትገበራ ነው የምለው ለዚህ ነው።

ኢትዮ12- አልመለሱልኝም? ደግሞስ በምን እንመን?

ዶ/ር ሃይማኖት- ሲጀመር አሜሪካን አገር በተባለው ስራ ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማት ጉዳይ ሚስጢር አይደለም ዳታ አለ። በዚህ ላይ በበቂ መረጃ የተደገፈ ጣናት አድርገን የደረስንበት በርካታ ጉዳዮች አሉ። ይህንን ጉዳይ እንደም ሃይል ሊያስተባብል አይቻለውም። እነዚህ ስምንቱ ተቀጣሪ የህዝብ ግንኙነት ስራ የሚሰሩት ድርጅቶች ከሎቢስት/ ወስዋሾች ከፍ ያሉ ናቸው። በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ መዋቅ፣ ተቋማትና አስፈለጊ ሰፍራዎች ውስጥ ዘልቀው በመግባት የትህነግን ስራ ይሰራሉ።

ኢትዮ12- ምንድን ነው የሚሰሩላቸው?

ዶ/ር ሃይማኖት- ለአሜሪካ ጥቅም መከበር ትክክለኛ አማራጭ እነሱ መሆናቸውን፣ በተቃራኒ ኢትዮጵያ የአሜሪካንን ጥቅም ማስተበቅ እንደማትችል አድርገው ያሳያሉ። በዚህ መልኩ ፖሊሲ አውጪዎቹም ሆኑ አስፈሳሚዎቹ ከአሜሪካ ጥቅም አንሳር ትህነግን እንዲመርጡ እንዲገደዱ ይሆናል። በዚህ ላይ መሃል ያለው አገር ሰላም ማጣቱ እንኳ የአሜሪካንን የራሱንም ሕዝብ ሰላም ማስከበር የማይችል ደካማ መንግስት ሆኖ እንዲታይ ያደርጋሉ። ጨዋታው መንታ ነው።

ኢትዮ12- ስምንት የህዝብ ግንኙነት የሚሰራ ድርጅት መቅጠር አይበዛም? ወይስ ስምንት የሆኑበት ልዩ ምክንያት አለ?

ዶ/ር ሃይማኖት- ታስቦበት ነው። ልዘርዝርልህ። ለዲሞክራቶች፣ ለሪፐብሊካኖች፣ ለሃይማኖቶች ጥምረት፣ለጥቁር አፍሪካ አሜሪካኖች ጥምረት፣ ለዋይት ሃውስ፣ ለኮንግረንስ፣ Lesbian, Gay, Bisexual and Transgender. q ለሚባሉት ጥምረቶችና ለተቀረው የህብረተሰብ ክፍል በህዝብ ግንኙነት የሚሰሩ የታሰበባቸውና የተመረጡ አቅጣጫዎች ናቸው። እነዚህ ሁሉ በየቀኑ ስለ ትግራይ እንጂ ስለ ኢትዮጵያ አይሰሙም። ዘመቻውም ጠንካራ የሆነው በዚሁ መነሻ ነው። እነዚህ አካላት ሚዲያውን ጨምሮ ሁሉም ፕሮፓጋንዳ በጃቸው ነው። ቀደም ብዬ እንዳልኩት ቀደም ብሎ አገራችን በመርህ ላይ የተመሰረተ የዲፕሎማሲ አግባብ ስላልነበራት ወይም እንዲኖራት ስላልተደረገ ዛሬ ልንፈተን ችለናል። ትህነግ የተመረጠው በዚህ አግባብ ነው። ከሰራንበት ግን በአጭር ጊዜ ይቀየራል።

ኢትዮ12- “አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ አሰራርና፣ አተገባበር” ያልሉ ምን ድን ነው?

ዶ/ር ሃይማኖት– ያለፈው አካሄድ እንዳከሰረ ታይቷል። ክርክር የለውም። ስለዚህ አዲስ አስተሳሰብ ግድ ነው። ትህነግ እያልን መሟገት ማቆም አለብን። 115 ሚሊዮን ሕዝብ ያላትን አገር አሜሪካ ከከሰረች ምን እንደምታጣ ማሳየትና በምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና ምን ሊከሰት እንደሚችል እንዲረዱ ማድረግ ግድ ነው። ትህነግ መረጃ እያምታታና በሚዲያ የበላይነት ራሱን ኢትዮጵያ ከምታክል አገር ይልቅ ለአሜሪካ ፍላጎት የተሻለ አድርጎ የሚያቀርበበትን አግባብ የእኛን ጉዳይ በማጉላት ብቻ ማሳየትና አሁን የሰፈነውን አመለካከት መገልበጥ ይቻላል። ስለዚህ አዲስ አሳብ ስል ዲፕሎማሲውን ከተራ ገንዘብ ሰብሳቢነት አላቆ ወደ ህዝብ ተሳትፎ ከፍ ማድረግ፣ እንደ እኛ ያሉ ድርጅቶችና ቀና አሳቢ ዜጎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አምባሳደሮች እንዲሆኑ ማስተባበር። አዲስ የትግበራ መንገድ መከተል ለማለት ነው። ( ዝርዝሩን ከቪዲዮው ያድምጡ)

ኢትዮ12- ስለዚህ አዲሱ አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ማጉላት ነው እያሉ ነው?

ዶ/ር ሃይማኖት- በሚገባ። ፖሊሲ አውጭዎቹ እኮ በገሃድ የመረጃ ችግር እንዳለባቸው ነግረውናል። ራሳችንን ከትህነግ ጋር ማወዳደርና ትህነግን በመክሰስ ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ ውጤቱ ታይቷል። ያን መድገም አያዋጣም። አዲሱ እሳቤ ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ጥቅም መከበር የማይተካ ሚና እንዳላት ማሳየትና ማረጋገጥ ነው። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ጥቅም ብቸናዋ የማትተካ አገር ብቻ ሳትሆን ሰብአዊ ቀውስ በመቀነስ ረገድ በቀጣናው እጅግ ታላቅ ሚና እንዳላት መረጃ መስጠትና ማሳመን ይጠይቃል። 115 ሚሊዮን ሕዝብ እንዲበተን መስራት፣ ስድስት ሚሊዮን ሕዝብ መደገፍ የመረጃ ክፍተት ካለሆነ በስተቀር ለማንም ግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው …

ኢትዮ 12- ትህነግ የኢትዮጵያን መንግስት ደካማ አድርጎ በየጊዜው የሚስለውና ይህንኑም የትህነግን ፍላጎት ሚዲያዎች የሚያራግቡት የተሻለ መሆኑንን ለመምስከርና ጫና ለመፍጠር ነው?

ዶ/ር ሃይማኖት – ምን ጥያቄ አለው? በሶማሊያ፣ በሱዳን የአሜሪካንን ፍላጎት ለማስጠበቅ ጥሩ ቅጥረኞች እኛ ነን በሚል ለአሜሪካ የደህንነት ጥያቄ መልስ ሰጪ ሆነው ኖረዋል። ዛሬም ” እኛ ካልሆንን ” እያሉ ነው በህዝብ ግንኙነታቸው በኩል የሚሰሩት። የሰላም ማስከበሩ ትህነግ ከወረደ በሁዋላ ያለ ችግር ቀጥሏል። ስለዚህ ኢትዮጵያ ይህን ተግባር በተሻለ ደረጃ እንደምትሰራ አሳይታለች። ወደፊትም ይህንኑ ታደርጋለች በሚል የተዛውን ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጵያን በማጉላት መቀየር ይገባል።

ኢትዮ 12- ምን አልባት የሰሜን ዕዝ እንዲጠቃ የተደረገው ለዚህ ይሆን?

ዶ/ር ሃይማኖት- “የተረጋጋች ኢትዮጵያን መምራት የምችለው ብቸኛ ድርጅት እኔ ነኝ” የሚለው ትህነግ ፣ ሰሜን ዕዝን ሲያጠቃ ሰማኒያ በመቶ የኢትዮጵያ ጦር እንደወደመ፣ መሳሪያውን እንደተቆጣጠረ፣ በማወጅ የአሜሪካን ጥቅም በማስከበር ደረጃ ብቸኛ ድረጅት መሆኑንን ለማሳየት ነበር እቅዱ። በገሃድም ተናግረዋል። በዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሩት እንደ ቴዎድሮስ አድሃኖም ዓይነት የትህነግ ሰዎች፣ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ በአፍሪካ ጉዳይ አስፈጻሚ ዲፓርትመንት፣ በኮንግረንስ የአፈሪካ ጉዳዮች በተመከተ የሚሰሩ ሃላፊዎች … በግንዘብና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች አስረዋቸዋል። በአሜሪካ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በእጅጉ ከጥቅም ጋር የተሳሰረ ነው። ከለውጡ በፊት ጥቅም ሲያገኙ የነበሩና የቆመባቸው ያንን ጥቅም ለማግኘት በግለሰብ ደረጃ በሚሰጣቸው መጠን ሁሉንም ደጅ ያንኳኳሉ….

ኢትዮ 12- አሁንም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የሚነዛው ፕሮፓጋንዳ የዛው ቀጣይ ነው ማለት ይቻላል?

ዶ/ር ሃይማኖት – አገር መምራትና አረጋግተን ማስቀተል የምንችለው፣ የአሜሪካን ጥቅም ማስተበቀ የምንችለው እና ብቻ ነን የሚለውን ለማሳካታን ያሰቡትን ለመያዝ የማያደርጉት ነገር የለም። ለዚህ ነው ሁሉም ለአገሩ አምብሳደር፣ ዲፕሎማት መሆን አለበት የምንለው። ድርጅታችን እንደራጅ የሚለው ለዚህ ነው። ስንደራጅና መደራጀታችንን በየዕለቱ ስናውጅ ሃይል እንዳለን ያውቃሉ። ሃይላችን ሲሰባሰብ በምርጫ ላይ ያለንን ጉልበት ይረዳሉ። በአሜሪካ ድምጽ ዋጋው ውድ ነው። ድምጻችንን አስተባበረን ለመብታችን መሟገቻና መደራደሪያ ማድረግ አለብን። Ethiopian Americans Voting Bloc – EAPAC Global በግል፣ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በንግድ ድርጅቶቻችን፣ በልጆቻችን፣ በጤናችን … በብዙ መልኩ ተጠቃሚ ለመሆን ኢትዮጵያ አሜሪካንስ እንደራጅ። ዋናው ጉዳይ መመዝገብ ብቻ ነው።


This image has an empty alt attribute; its file name is 217391620_843127696581497_1533589810883676736_n.jpg
EAPAC

EAPAC Global is by all Ethiopian Americans for all Ethiopian Americans. We are all in this together. One Ethiopian American for all and all Ethiopian Americans for one.

ዝግጅት ክፍሉ – እዚህ ቃለ ምልልስ ውስጥ የተጠቀሰው በቃለ ምልልሱ ያልተባለ ነው። ቪዲዮውን ታደምጡ ዘንዳ እናበረታታለን። ዶ/ር ሓይማኖት ሰፊ ራዕይና አሳብ አንግበው በመነሳታቸው ቀና ዜጎች ሁሉ እንዲያግዟቸው ጥሪ እናቀርባለን። ይህን መረጃ የምታነቡ ሁሉ ሼር በማድረግ ይህ ሃሳብ ዜጎች ዘንድ እንዲደርስ ታደርጉ ዘንድ እናሳስባለን። በተከታታይ የድርጅቱን ተግባርና ውጤት እየጠየቅን ለማሳወቅና ይህን ሃሳብ ለማስፋፋት እንደምንሰራ እናረጋግጣለን

ከድርጅቱ ገጽ የተወሰደ አስፈንጣሪውን ተጭነው ዝርዝር ይመልከቱ


1 thought on “አዲስ ዲፕሎማሲ አሁኑኑ!! ” 115 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አገር ባልተገባ ጫና ለማፍረስ መሞከር ቅድሚያ የሚጎዳው ጫና ፈጣሪዎቹን ነው”

 1. መንግስት እንዚህን ይዞ ነው ዲፕሎማሲውን ማሸነፍ የሚያስበው የፌስቡክ ወሬ ለመሰብሰብ ባለ ባይደራጁ ይሻላል ።
  ነጥብ በነጥብ ለማስቀመጥ

  ” …ችግሩ ያለው ቀድሞ መረጃ ማድረሱ ላይ ነበር። ”

  መረጃ ለማን ..? ለኣመሪካ መንግስት..? ስለምን ስለ ጦርነቱ ? የአሜሪካ መንግስት አዲስ ኣበባ ውስጥ ኤምባሲ ያለው ኤምባሲው
  ወደ ስድስት ቅርንጫፎች በተለያዩ ክልል ያሉት
  Satchmo Center ( addis Ababa)
  Mekelle American Corner
  Col. John C. Robinson American Center ( addis Ababa, Mekelle )
  Bahir Dar American Corner
  Dire Dawa American Corner
  Jimma American Corner

  ሌላው የ ኣሜሪካ ድርጅት USAID በ 45 ወረዳዎች ላይ የሚንቅሳቀስ የዜና ወኪሉ አዲስ ኣበባ መቀለ ባህርዳር ጎንደር ዓዲ ግራት ላይ ወኪል ያለው
  ይህ የኣውሮፓውያን ሳይጨምር ነው
  በተለይ ኣሁን በእዚህ ሰዓት በ TPLF በሚቆጣጠራቸው ኣከባቢ እና በመንግስት ይዞታ እንደልብ የሚንቅሳቀሱት ያለ ስጋት የሚዛዋወሩት ፈረንጆቹ እንጂ ኣንድ ትግሬ ወደ ኣማራ ዝር ኣያላትም ኣማራም ወደ ትግራይ ኣይሄድም ። ከኣንዱ ወደ ኣንዱ ወረ እና ደብዳቤ የሚመላለሱት በእነዚህ መካከል ነው ። ከመቀለ ወደ ደሴ ከ ዓዲ ግራት ወደ ባህርዳር ስልክ የሚደወለው በእርዳታ ድርጅቶች የሳተላይት መሳሪያ ነው ። ቀይ መስቀል የመቀለ ዩኒቨርሽቲ ተማሪዎችን ከቤተሰብ እያገናኘ ያለው በWfp በኩል ነው ።
  እና ኣሁን ፈረንጆቹ ስለ TPLF ከዓብይ በላይ ያውቃሉ ከ TPLF በላይ ደግሞ ስለ ዓብይ ያውቃሉ ። ከመቀለ እና ባህርዳር ወጣት በላይ ያውቃሉ ።
  እና ማን ነው ስለማን የሚያስረዳው ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ ከማንም በላይ ስለ ኢትዮጵያ ይመለክትሃል እንጂ ኢትዮጵያ ላይ ስላለው ነገር ታውቃለህ ማለት ኣይደለም ።
  ዲፕሎማሲ ደግሞ መረጃ የማቀበል ወይ ስለ ሁኔታዎች መነጋገር ኣይደለም። በመጭው ላይ መደራደር ነው ።

  ሌላው በወር 1 million usd ያወጣል የተባለው ነው ።ይህ ጄነራል ምግበይ ወይ ጻድቃን የሚሸፍኑት ነው ። ግብጽ ኣይስኬድ ሳውዲ አያመላልስ መቼም የTPLF ሰዎች ይህን ቢሰሙት ያድርግልን እንደሚሉ ነው ። በ 1 ሚልዮን ዶላር በወር የኣሜሪካ ን መንግስት ሚዲያ እና ሴኔት መቀየር ይቻላል ?.
  USAID በ ኣማራ ክልል ላይ በወር ምን ያህል ወጪ ያወጣል..? WFP ትግራይ ላይ በወር ለኣስተዳደር ብቻ ለደሞዝ ምን ያህል ያወጣል …?። የትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት መቀለ ላይ ምን ያህል ግብር ሰበሰበ በወር ..? ይህን የተባለውን ብር ኣዲስ ኣበባ ላይ ኣንድ ክፍለ ከተማ በሳምንት ውስጥ ታክስ ኣንደሚሰብስብ ( በኣማካይ ልደታ ክፍለ ከተማ ወደ ሚልዮን ብር በወር ይሰበስባል ) ኣታውቅም ?
  ይህ ፈጽሞ ፈጽሞ የዲፕሎማት ስራ ኣይደለም ። ዲፕሎማሲ የድርድር ስራ ነው ኣዎ በአሜሪካ እና በ ኢትዮጵያ ጥቅሞች ላይ መደራደር መስጠት መቀበል ምን ይሰጣል ምን ኣይሰጥም ምን ኣንቀበላን ምን ኣንቀበለም መቼ እና የት የሚለየውን መለየት ይህ የራሱ ዓውድ ያለው ሳይንስ ነው ።
  መጀመሪያ ደረጃ public diplomacy የሚባለው ወደ ህዝብ ለመድረስ ነው ። ወደ ኣሜሪካ ህዝብ ። public diplomacy ኢትዮጵያ ከኤርትራ ኢትዮጵያ ከ ሱዳን ኢትዮጵያ ከ ሶማልያ ላይ መሰራት ያለበት ያልተሰራበት ነው ። በኢትዮጵያ እና ኣሜሪካ መካከል የሚያስፈልግበትም የሚሰራበት ሁኔታ ኣሁን የለም ።
  ልምድ ያለው ጋዜጠኛ በእዚህ ጉዳይ ላይ ፋርማሲስት ማናገሩ ውጤቱ ይህ ነው በሃገር ቤትም ተመሳሳይ ችግር ነው ያለው።

Leave a Reply

%d bloggers like this: