ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ለ3 ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት ሲጠናቀቅ የተለያዩ ስምምነቶች ማድረጋቸው ይፋ ሆነ። ዝርዝር ጉዳይ አልተገለጸም።
ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ዝግ ምክክር በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን በጥልቀት መርመሯል። አሁን ተደረሰ የተባለው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክርና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።
የአገር መከላከያ ይፋዊ የፊስ ቡክ ገጽ እንዳስታወቀው በውይይቱ ማጠቃለያ ለይ የተገኙት የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሊዊጅ ናቸው የሶስቱን ቀናት ውይይት አስመልክተው የተለያዩ ስምምነቶች ላይ መደረሱን ያመለከቱት።
የሰራዊቱን አቅም በእወቀት ፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በውይይቱም ከሩስያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ኃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ነበሩ።
ዜናው ስለወታደራዊ ስምምነቱ በዝርዝር ይፋ ባያደርገም ታላላቅ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ካለው ቅጥ ያጣ ጫና አንጻር ኢትዮጵያና ሩስያ ከበድ ያለ ወታደራዊ ስምምነት እንደፈጸሙ ግምት አለ።
ሌተናል ባጫ ደበሌ ኸምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሰሞኑንን ሩስያ ለምን እንደሄዱ ተጠይቀው ” መሳሪያ ልገዛ” ማለታቸው አይዘነጋም።
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን አስጠንቅቆ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!April 19, 2024 ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ህዝብ ተወካዮች ጋርApril 1, 2024 የባህር በር… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S.… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report