ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ለ3 ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት ሲጠናቀቅ የተለያዩ ስምምነቶች ማድረጋቸው ይፋ ሆነ። ዝርዝር ጉዳይ አልተገለጸም።
ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ዝግ ምክክር በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን በጥልቀት መርመሯል። አሁን ተደረሰ የተባለው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክርና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።
የአገር መከላከያ ይፋዊ የፊስ ቡክ ገጽ እንዳስታወቀው በውይይቱ ማጠቃለያ ለይ የተገኙት የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሊዊጅ ናቸው የሶስቱን ቀናት ውይይት አስመልክተው የተለያዩ ስምምነቶች ላይ መደረሱን ያመለከቱት።
የሰራዊቱን አቅም በእወቀት ፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በውይይቱም ከሩስያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ኃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ነበሩ።
ዜናው ስለወታደራዊ ስምምነቱ በዝርዝር ይፋ ባያደርገም ታላላቅ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ካለው ቅጥ ያጣ ጫና አንጻር ኢትዮጵያና ሩስያ ከበድ ያለ ወታደራዊ ስምምነት እንደፈጸሙ ግምት አለ።
ሌተናል ባጫ ደበሌ ኸምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሰሞኑንን ሩስያ ለምን እንደሄዱ ተጠይቀው ” መሳሪያ ልገዛ” ማለታቸው አይዘነጋም።
- ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡMore stories “አእምሮዬ አልዳነም!”January 15, 2020 ህወሃት “በዓባይ ወንዝ ጎጃም ከሚለማ የሲና በረሃ ቢለማ ይሻላል”February 25, 2021 “አሸባሪው የህወሃት… Read more: ቀሲስ በላይ ከ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ ሚኒስትር… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት ይኖረናል… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም ጠቅሶ… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል
- የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ ሌሎች… Read more: የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?