አዲስ አበባን በፓርላማ ለመወከል የተመረጡት እነማን ናቸው?

በፎቶው ላይ የሚታዩት የውሃ፣ መስኖ እና ኢንርጂ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ፣ዛዲግ አብርሀ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ ፕ/ር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የአገር አቀፍ ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ ናቸው።

በዘንድሮው ምርጫ ብልፅግና ፓርቲ ከ436 መቀመጫዎች ውስጥ 410 ያሸነፈ ሲሆን ለቀጣዩ አምስት አመታትም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ወንበር አግኝቷል።

ለዘመናት የአገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ማዕከል ሆና በቆየችው አዲስ አበባ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከተማዋ ላይ ባተኮረ መልኩ ፖሊሲዎችን ሲቀርፁና ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ።

በዘንድሮው ምርጫ ብዙ ትኩረት በነበረባት አዲስ አበባ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 1,819,343 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 99ኛው በመቶ ድምፅ ሰጥቷል።

አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 መቀመጫዎች ያሏት ሲሆን ገዢው ፓርቲ ብልፅግና 22 መቀመጫዎችን ሲያሸንፍ በግል የተወዳደሩትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መቀመጫ አግኝተዋል።

ለመሆኑ በቀጣዮቹ አምስት አመታት አዲስ አበባን በፓርላማ የሚወክሏት እነማን ናቸው?

 • ምርጫ ክልል 1- ፕ/ር ኢያሱ ኤልያስ
 • ምርጫ ክልል 2 ብርሃነ መስቀል ጠና
 • ምርጫ ክልል 3 የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ
 • ምርጫ ክልል 4 ሙሉ ይርጋ
 • ምርጫ ክልል 5 ያስሚ ወህቢ
 • ምርጫ ክልል 6 ዶክተር ወንድሙ ተክሌ
 • ምርጫ ክልል 7 በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያ አቋም ለአረቡ ዓለም በማንጸባረቅ የሚታወቁት መሐመድ ከማል አሊ አል-አሩሲ
 • ምርጫ ክልል 8 የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ
 • ምርጫ ክልል 10 ዶ/ር ቤተልሄም ላቀው
 • ምርጫ ክልል 11 ፕ/ር ሂሩት ወ/ማርያም፣
 • ምርጫ ክልል 12 እና 13 ዕጩ ሲሆኑ ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል
 • ምርጫ ክልል 15 ህይወት ሞሲሳ
 • ምርጫ ክልል 16 ሰሃርላ አብዱላሂ
 • ምርጫ ክልል 17 የውሃ፣ መስኖ እና ኢንርጂ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር)፣
 • ምርጫ ክልል 18 ዛዲግ አብርሀ
 • ምርጫ ክልል 19 ዶ/ር ትዕግስት ውሂብ
 • ምርጫ ክልል 20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
 • ምርጫ ክልል 21 እና 22 የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ
 • ምርጫ ክልል 23 የአገር አቀፍ ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ
 • ምርጫ ክልል 24 ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ
 • ምርጫ ክልል 25 ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ
 • ምርጫ ክልል 26 እንዳልካቸው ሌሊሳ
 • ምርጫ ክልል 28 በግል ተወዳዳሪነት የቀረቡትና የጠቅላይ ሚኒሰትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ናቸው።

የክልል ምክር ቤቶችን በምንመለከትበት ወቅት ብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባን ምክር ቤት ሁሉንም 138 መቀመጫዎችን አሸንፏል።

መስመር

ምርጫ 2013 በጨረፍታ

 • 37,408,600 መራጮች ተመዝግበዋል ከዚህ ውስጥ 20,317,472 ወንዶችና 17, 091, 128 ሴቶች ናቸው
 • 47 ፓርቲዎች 8,209 እጩዎችን አቅርበዋል 125 የግል ተወዳዳሪዎችም
 • 634 የምርጫ ክልሎችና 49, 407 የምርጫ ጣቢያዎች
 • 52,700 የምርጫ አስፈጻሚዎች፤ በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ 5 አስፈጻሚና 1 የኮቪድ-19 ቁጥጥር ባለሙያ
 • ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ለ445 የፓርላማ መቀመጫዎች ድምጽ ተሰጥቷል
 • ጳጉሜ 01/2013 ደግሞ ለቀሪዎቹ 64 ወንበሮች ድምጽ ይሰጣል

ምስጋና ፎቶና ዘገባ ቢቢሲ


 • ጌታቸው ረዳ የማያውቃቸው የጄ. ይልማ መርዳሳ ንሥሮች
  …. SU-27 ሆዬ 100KM ላይ ኢላማውን አረጋግጦ ሚሳይልና ቦምቦቹን አራግፎለት ተመልሷል። በዚህ ቅፅበት የጌቾ ሰዎች ፍንዳታ እና እሳትን እንጂ SU-27 መምጣቱንም ማወቅ አይችሉም። ጌቾ ፍንዳታውን በተመለከተ መረጃ ሳይደርሰው/ በማይሰማበት ቅፅበት ጄቱ ሚሳይሉን ካስወነጨፈበት የ 100KM ርቀት አፍንጫውን ወደ ደብረ ዘይት መልሶ ከድምፅ ሁለት እጥፍ በላይ ተወንጭፎ ወደ ጦር ሰፈሩ ለማረፍContinue Reading
 • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
  የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
 • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
  “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
 • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
  አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading
 • የሽብርተኛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሠራዊታችንን የድል ግስጋሴ አይገታውም !
  ሽብርተኛው ከሚታወቅባቸው ስልቶቹ መሀል አንዱ ቅጥፈቱ ነው ፡፡ ጉልበት ሲያንሰው ምላሱ ይረዝማል ፤ ያልሆነውን ሆንኩ ፣ ያላደረገውንም አደረኩ…ይላል ፡፡ ይህ ደግሞ ጥርሱን የነቀለበት እና ተወልዶ ያረጀበት ባህሪው ነው ፡፡ አንድም ቀን ከአፉ እውነት ተገኝታ የማታውቀው ይህ ሽብርተኛ ፣ ሽንፈቱን የሚሸፍነው የሠራዊታችንን ስም በማጠልሸት ነው ፡፡ ደጋፊዎቹ ኪሳራውን እንዳያወቁ ፣ ሰላማዊውContinue Reading

Leave a Reply