ለትግራይ ሕዝብ ያለንን ሐሳብ፤ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለንን ቦታ ለመጨረሻ ጊዜ አሳይተናል። ግጭት ላለማባባስ፣ ለሕዝቡ የእርሻ ወቅት ፋታ ለመስጠት እንዲሁም የርዳታ አቅርቦቱ ያለ ሰበብ እንዲከናወን ስንል በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጠል የተኩስ አቁም አድርገናል። ሰላም የተወሰነ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ብናውቅም ይህ ግን የመጨረሻ ሰላማዊ ዕድል ነው።
ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ እንደሚባለው ጁንታው የሰላም መንገድ ሊዋጥለት አልቻለም። አሁን ባለው ቁመናው ያለ ግጭት ውሎ ማደር አይችልም። ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛለ። የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል።
ለሕዝባችን ስንል የከፈልነው ዋጋ ባልገባቸው ደካሞች ምክንያት ውጤት አላመጣም። ጁንታው የኢትዮጵያ ህልውና ቀንደኛ ጠላት መሆኑን ደግሞ እያስመሰከረ ነው። ይሄንንም መላ ሕዝባችንን አስተባብረን እንቀለብሰዋለን። በአንድ በኩል ሰብአዊ ርዳታ እንዲቀላጠፍ እየሠራን በሌላ በኩል የውጭና የውስጥ ጠላቶች ተናበው የከፈቱብንን ጥቃት መክተን እንቀለብሰዋለን።
ጁንታው ዋሻ ውስጥ ገብቶ ሕዝቡ በረሐብ ሊያልቅ ነው እያለ ሲያላዝን ነበር። ለሕዝቡ ሲባል ሰብአዊ የተኩስ አቁም ሲደረግ ደግሞ የረሐቡን አጀንዳ ትቶ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ጀመረ።
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለ ርዳታና ስለ ረሐብ ሲናገር መቆየቱን ዘንግቶ ጁንታው ሕጻናትን ሲያሰልፍ እንኳን ዝምታን መርጧል። የርዳታ መግቢያ ኮሪደሮችን የግጭት ቦታዎች ሲያደርጋቸው የርዳታ ድርጅቶች አሁንም መንግሥትን ለመውቀስ ይቃጣቸዋል። እነዚህን ሁሉ ከግምት በማስገባት መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ነገር በተገቢው መንገድ ያደርጋል።
ሕዝባችን ከሐሰተኛ መረጃዎች እና ከጠላት ፕሮፓጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ አሁንም ለማሳሰብ እንወዳለን። ጁንታውና አጋሮቹ ያላቸው ዐቅም ውሸትን መፈብረክ ብቻ ነውና። የውስጥና የውጭ ኃይሎች ፕሮፓጋንዳቸውን አቀናጅተው ሕዝብን ለመከፋፈል እየሠሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ሕዝባችን እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ እንደ አንድ ሠራዊት ሆኖ ለሀገሩ ህልውና በመቆም፣ የመከላከያ ሠራዊቱን በሁሉም ነገር በመደገፍ፣ የውጪውን ጫና እና የውስጡን ትንኮሳ እንዲመክትና እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሀምሌ 7, 2013 ዓ.ም
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር መተብተቧ እየተጠቆመ ነው። በተጀመረው የአብይ ጾም ማቅ ለብሰውና አመድ ነስንሰው ችግራቸውን ሊፈቱ እንደሚገባ ምክር እየተሰጠ ነው። መንግስት በዋናነት ብቻ ባለው አስራ አንድ ጊዜ ስብሰባ የተቀመጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳለ የተጠቆመው አሁን ከቀናት… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ ሊያውል መሆኑ ተሰምቷል፡፡ More stories ቻይና በኢትዮጵያ ያላት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸFebruary 26, 2023 “መጀመሪያ ሁሉም ነገር አስቸጋሪ ቢመስልም በስኬት እንደሚጠናቀቅ ጽኑ እምነት ነበረኝ”April 23, 2023 “መለኮታዊ አገዛዝ” የተባለው የትህነግ ዘመን የውስጥ ቀውስJanuary 19, 2022… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም ነው፡፡ ከገንዘቡ ባሻገር ብዙ እውቀቶች ፈሰውበታል፤ አዳዲስ ነገሮች ተዋውቀውበታል፡፡ ዓለምን እጅ በአፍ አስጭኗል…. “ኒዮም ሲቲ” (Neom City) በሳውዲው ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ይፋ የሆነው ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረ ሲሆን በውስጡ አራት ሥራዎች ይገኙበታል፡፡ እነሱም ዘ ላየን፣ ኦክሳገን፣ ትሮጄና እና ሲንዳላህ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has even raised questions about the stability of the Horn of Africa and resulted in a similar deal struck between Somalia and Türkiye recently. However, arguments that the region might fall into turmoil due to Ethiopia’s move are overstated. Addis Ababa, with the deal,… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ” ባላቸው አካባቢዎች ለዓመታት የቆየ ውዝግብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ህገመንግስቱ በሚያዘው መሰረት በህዝበ ውሳኔ እንዲቋጭ በይፋ ስምምነት ላይ መደረሱ ተረጋገጠ። ተፈናቃዮች ወደቀያቸው መመለስ ይጀምራሉ። በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ወልቃይት ጠገዴን ጨምሮ ” ነጻ ወጡ” የተባሉት አካባቢዎች ለትግራይ እንዲመለሱ ካልተደረገ ጦርነት እንደሚቀሰቅሱ ሲገልጹ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ