“ሠራዊታችን በስነ ልቦና ፣ በትጥቅ ፣ በሎጀስቲክስ ፣ በሰው ሀይል የተሟላ ዝግጁነት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ፣ ትዕዛዝ ሲሰጠው አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ በሚያስችል ተጠንቀቅ ላይ ሆኖ እየተጠባበቀ ይገኛል” የሚለው መግለጫ ማለዳ ተሰጠ። አስከትለው አጅግ በተለሳለሰ ቋንቋ “ሁሉ ከግምት በማስገባት መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ነገር በተገቢው መንገድ ያደርጋል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ። ተከትሎም አማራ ክልል በይፋ ማጥቃት መጀመሩን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት የጸጥታ ኃይል ህወሓትን የከፈተውን ወረራ ለመመከት እግዳጅ ማዕከል መሰማራቱ የተሰማው ከክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።የቢሮ ኃላፊው አቶ ጌታቸው ባልቻ “የክልሉ ጸጥታ ኃይል በትግራይ ክልል ሕግ የማስከበር ዘመቻውን ተቀልቅሏል” ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሲዳማ ክልል በሃሰት የተሰራጨውን ዜና ለማጋለጥ በሚመስል ሃይሉን መላኩ ተሰምቷል።
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ፥ ዛሬ ምሽት የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ይሸኛሉ ሲሉ በይፋ ተናግረዋል። በመንግስት መገናኛ እንደታየው የሲዳማ ክልል ልዩ ሃይል ግንባሩን ሊቀልቀል ያቀናል። ይህ ከተባለ በሁውላ ነው። አሁንም በሰከነ መንገድ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ፣ የመከላከያ ሠራዊት በየት ቦታ እና መቼ ማጥቃት እንዳለበት ወስኖ እየሰራ ነው” ሲሉ መግለጫ የሰጡት።
ከመከላከያ ሕዝብ ግንኙነት፣ ከጄራሉና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጡት መግለጫዎች ወይም መረጃዎች ፉከራ አልታዩባቸውም። ነገር ግን የአማራ ክልል መንግስት፣ ኦሮሚያን ጨምሮ ክልሎች እንዲሁም መከላከያ ድጋፍ እንደሚያደርግ በይፋ መናገራቸውን ተከትሎ አንድ ይፋ ሊሆን ያልተፈለገ ነገር ግን መንግስት አድብቶ የሚፈጽመው አንድ ጉዳይ ስለመኖሩ አመልካች መሆኑ እየተነገረ ነው።
ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ህዝቡ መረዳት ያለበት ወታደራዊ ስራ በወታደሮች እንጂ በአክቲቪስቶች የሚከናወን አይደለም፤ ሠራዊቱ ደግሞ በየት ቦታ፣ መቼ ማጥቃት እንዳለበት ወስኖ እየሰራ መሆኑን መናገራቸው የዚሁ ማሳያ ሆኖ ታይቷል።
መንግስት በወሰነው የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት ሠራዊቱ ከትግራይ ክልል መውጣቱን ያስታወሱት ሌተናል ጀነራል ባጫ በመንግስት ውሳኔ መሰረት ሠራዊቱ እንቅስቃሴ ማድረጉን ገልፀዋል።የመከላከያ እና የአካባቢ የፀጥታ አካላት አነስተኛ ኃይል በማስቀመጥ ጥበቃ ይደረግ እንደነበር እና አሸባሪው ቡድን በተለያየ አጋጣሚ ይህንን ኃይል ለማጥቃት በመሞከር በተለያዩ አካባቢዎች ትንኮሳ ማድረጉን ሌተናል ጀነራል ባጫ ገልፀዋል።
የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነቱን አሸባሪው ኃይል ለመቀበል ባህሪው አይፈቅድለትም ያሉት ሌተናል ጀነራል ባጫ የተኩስ አቁም ስምምነቱን መቀበል ያልቻለው ጁንታው ከትግራይ ህዝብ የሚቀርብለትን የሰላም ጥያቄ ለመመለስ ስለማይችል እና ከህዝብ የሚነጥለው ጉዳይ ስለሆነም ጭምር ነው ብለዋል።የሚደረገው ጦርነት ኢትዮጵያን እንደሀገር የማስቀጠልን ጉዳይ ለማረጋገጥ እና ጁንታው የያዘውን ሀገር የመበታተን እቅድ እንደማይሳካ እና እንደማይቻል ለማሳየት ነው ብለዋል።
ሠራዊቱ እየተዋጋ ያለው ለኢትዮጵያ ድንበር ነው፤ ድንበሩ ደግሞ መረብ ነው ያሉት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ ሠራዊቱ የተቀመጠበትን ቦታ እና የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማንም ግልፅ አለመደረጉንም ገልፀዋል።መከላከያ ሠራዊቱ የአገሪቱን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን የገለፁት ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዲቆም እና ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
- “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደትሰሞኑንን ለይቶለት ይፋ ሆነ እንጂ ውስጥ ውስጡን የጦርነት እንቅስቃሴ ሲደረግ እንደነበር መረጃዎች ከበቂ በላይ ነበሩ። ለዚህም ይመስላል ጠቅላይ… Read more: “ንገሩዋቸው፣ ምከሩዋቸው” ሌላ ጦርነት እብደት
- የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይየ34 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ከአውሮፕላኑ ሲወርድ እግሮቹ ቆስለው መራመድም ሆነ መቆም አቅተውታል። ብርክ ይዞት ይንገዳገዳል፡፡ ይህ ሰው የተሻለ ህይወት… Read more: የባህር ወንበዴ ሲሳዮች – በገሃነም የሚመሰለው ስቃይ
- ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል“ህወሓትና የግብረ አበሮቹ ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀቡ ይገባል” ሲል አማራ ክልል አሳሰበ። ስም… Read more: ትህነግ ለአራተኛ ጊዜ የአማራ ህዝብ ላይ ወረራ በመፈጸሙ አማራ ክልል ህዝቡን ለመከላከል እንደሚገደድ አስታወቀ፤ ፌደራል መንግስት ጥያቄ ቀርቦለታል
- የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው መገደላቸውን እና ሌሎች የወረዳው እና የከተማዋ ኃላፊዎች አካባቢውን ለቅቀው ወደ… Read more: የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሲገደሉ ሌሎች ሃላፊዎች ሸሽተዋል፣ ግድያውን ማን ፈጸመው?
- ታደሰ ወረደ ” የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም” ሲሉ አዲሱን ግጭት የሚጠበቅ እንደሆነ አመላከቱየትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በራያ አላማጣ ዳግም ወረራ እየተካሄደ መሆኑ ይፋ መደረጉን ተከትሎ… Read more: ታደሰ ወረደ ” የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም” ሲሉ አዲሱን ግጭት የሚጠበቅ እንደሆነ አመላከቱ