አዲስ አበባ፦ መላው የአማራ ህዝብ አሁን እያጋጠመው ያለው አደጋ የታሪክና የማህበራዊ ክብር እንዲሁም የማንነት ጉዳይ በመሆኑ አጠቃላይ ጥቃቱን ለመመከት አስቸኳይ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።
አብን ትናንት ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ፣መላው የአማራ ህዝብ አሁን እያጋጠመው ያለው አደጋ የታሪክና የማህበራዊ ክብር እንዲሁም የማንነት ጉዳይ መሆኑን በመረዳት አጠቃላይ ጥቃቱን ለመመከት አስቸኳይ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
የአማራ ወጣቶች በየአካባቢያችሁ በመምከርና በመደራጀት፣ ራሳችሁን በማስታጠቅ ለሁለንተናዊ ዘመቻ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ፣በሁሉም አካባቢዎች ያላችሁ የአማራ ፋኖዎች በአሁኑ ሰዓት ህዝባችን ያጋጠመውን የህልውና ትግል ለመቀልበስ በግንባር ለመንቀሳቀስ ፈጣን ዝግጅት እንድታደርጉ ብሏል።
መላው የአማራ ህዝብ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና በተለይም በመካከላችን ሆነው ሴራና ጥቃት የሚያቀናብሩ፣ በሰርጎ ገብነት መረጃ ለጠላት የሚያቀብሉ አካላትን በንቃት በመከታተል የማክሸፍና የመቆጣጠር ሥራ እንዲያከናውን ጥሪ አቅርቧል።
በተለያየ የአመራር ጥፋትና ጥሰት ያላግባብ ተገፍታችሁ ከፀጥታና ከወታደራዊ አመራ ርነታችሁና ሙያችሁ ውጭ የተደረጋችሁ የአ ማራ ልጆች በሙሉ ህዝባችሁን ለመታደግ የሚደረገውን ታሪካዊ እንቅስቃሴ ለመቀላቀል እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስቧል።
አብን በመግለጫው ፣ሂደቶችን በአስተ ውሎት እየተከታተልንና መረጃ እየሰበሰብን በመቆየት ነገሮች ይሻሻላሉ በማለት ብንጠብቅም ችግሮቹ በፍጥነት ሲወሳሰቡ በማየታችን ለህዝባችን ህልውና ይህንን ጥሪ ለማድረግ ተገደናል ብሏል።
መላው የአማራ ህዝብ የተደቀነበትን የህል ውና አደጋ ለመቀልበስ ለሚደረገው ሁለንተናዊ ዘመቻ በትጥቅና ስንቅ አቅርቦት እንዲሁም በደጀንነት ርብርብ እንዲደረግ የጠየቀው አብን ፣ የህልውና ዘመቻውን በሙሉ እንዲቀላቀሉ እና እንዲያስተባብሩ ለሁሉም የንቅናቄው አባላትና አመራሮች ትዕዛዝ ማስተላለፉንም አስታውቋል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ሐምሌ 7/2013
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of Somaliland in a… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ። ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ
- የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡየቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሲሰጡ እግረመንገዳቸውን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በበጎ ጎኑንና በስጋት ከፍለው መግለቻቸው ላይ አክለዋል። በኢትዮጵያ… Read more: የቡድን ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ የይሁንታና የስጋት ቅልቅል መግለጫ ሰጡ
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring a new dynamism… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀMore stories ባይደን የላኩዋቸው ሴናተር ክሪስ ከውይይቱ በፊት የትህነግን የተደበቀ ግፍና ወንጀሎች በምስል ያያሉMarch 19, 2021 ችግሩን መፍታት የተሳነውና ለአራተኛ ጊዜ የተከፈለው… Read more: መንግስት የፕሪቶሪያው ስምምነት መጣስና የአማራን፣ትግራይና አፋር ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት ተቀባይነት የለውም ሲል አስጠነቀቀ