ሱዳን-በታላቁን ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን ልዩነት ከኢትዮጵያ ጋር ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ውይይት ነው

የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን የታላቁን የህዳሴ ግድብ ችግር ከኢትዮጵያ ጋር ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ውይይት መሆኑን ገለጹ፡፡አል-ቡርሃን ሱዳን በአፍሪካ ቀንድ አካባቢያዊ መረጋጋት በተለይም ጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ለመስራት ሀገራቸው ፍላጎት እንዳላት አረብ ኒውስ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል፡፡

ሊቀመንበሩ በቀይ ባህር እና በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበርን ጋር በነበራቸው ወይይት ነው ይህን የተናሩት፡፡ የአውሮፓ ህብረት በሱዳን በተለይም በአለም አቀፍ መድረኮች ዴሞክራሲያዊ ሽግግርን ለመደገፍ ውጤታማ ሚና መጫወቱን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

ሌ/ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን ሱዳን ያለባትን የውስጥ እና የውጭ ተግዳሮቶችን እስክታሸንፍ ድረስ የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበርን ጋር ባደረጉት ውይይት የመንግስት አካላት ነፃነትን የሚፈቅዱ እና የሃይማኖታዊ መቻቻልን ለማስፈን የሚያስችሉ የሕግ ማሻሻያዎችን በማድረግ የግዛት አወቃቀሩን ለማጠናከር ፍጹም በሆነ ስምምነት እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ወታደራዊው አካል ዴሞክራሲያዊ ሽግግሩን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ብለዋል ፡፡የሽግግር መንግስቱ በጎረቤቶቹ ሀገራት ላይ መረጋጋት እንዲሰፍን ፍላጎት እንዳለው በመግለፅ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ሁኔታ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አል-ቡርሃን ተናግረዋል፡፡በጠቅላይ ሚኒስትሩ አብደላ ሀምዶክ የቀረበውን ተነሳሽነት በመጥቀስ የህዳሴ ግድብን ጉዳይ ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ወይይት መሆኑንም አክለዋል፡፡

ዌበር በበኩሏ የሽግግር መንግስቱ ለዴሞክራሲያዊ ሽግግር መሰረት ለመጣል ያደረገውን ጥረት በማድቅ ሱዳን ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮቿን ለመፍታት በምታደርገው ጥረት የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ማድረጓን እንደሚቀጥል ገልጻለች ፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: