የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እየወሰደ ባለው ማጥቃት የአሸባሪውን ኃይሎች ከአማራ ክልል እያስወጣ እንደሆነ የክልሉ መንግስት አስታወቋል። ክልሉ ወደ ሙሉ ማጥቃት መዛወሩን ይፋ ባደረግ በቀን ውስጥ ነው ይህን ያለው። የአሸባሪ ቡድኑ ወረራ በአማራ ክልል ተወስኖ ስላማይቀር የሌሎች ክልሎች ኃይሎችም የህልውና ዘመቻውን እየተቀላቀሉ መሆኑን ክልሉ ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል በጦርነቱ ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለዉ ቆቦ የሚገኙ ነዋሪዎች ርዳታን እየጠየቁ ነዉ።
የአማራ ክልል እንዳስታወቀው ህዝብ ለቅረበለት ጥሪ ከበቂ በላይ ምላሽ ሰጥቷል። የአሸባሪው ኃይሎች በሰሜናዊ የአማራ አካባቢዎች ወረራ መፈጸማቸውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በተደረገ የክተት ጥሪ ተቀብለው በርካቶች ትግሉን ተቀልቅለዋል። ትግሉን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ሆነው ስምሪት የሚጠብቁም ይልቃሉ።
የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን የመንግስት ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለጀርመን ድምጽ እንድተናገሩት የክልሉ ልዩ ሃይል አሸባሪው ቡድን ይዟቸው የነበረውን አካባቢዎች እያጸዳና እያስልቀቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“የአሸባሪው ጥቃት በአማራ ክልል ተወሰኖ እንደማይቀርና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሚሰራ በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ያረጋገጠው ነው” ያሉት አቶ ግዛቸው ይህን ሴራ ለመበጣጠስ ሌሎች ክልሎችም የፀጥታ ኃይሎቻቸውን ወደ አማራ ክልል እየላኩ እንደሆነ አስረድተዋል፣ እስካሁንም ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃሎቻቸውን ልከዋልም ብለዋል፡፡
አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት ሕወሓት በማይካድራ በቅርቡ ደግሞ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲደርስ አንድም ቃል ሳናገሩ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ፍትሃዊ አለመሆኑንን ሃላፊው አስታውቀዋል።
ሃላፊው አይገለጹት እንጂ አላማጣን ጨምሮ የትህነግ ቡድን ለአንድ ቀን ተቆጣጥሯቸው የነበሩትን ስፋርዎች የአማራ ልዩ ሃይል አስመልሷል። እንደሚሰማው ከሆነ የአማራ ልዩ ሃይል በጦርነቱ የበላይነት ይዟል። ይሁን እንጂ አሁንም ሰላማዊ ውይይት እንደሚሻል በስፋት አስተያየት እየተሰጠ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ የሚገኙ ወገኖች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ አንድ የራያ አማራየወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ተፈናቃዮች በየዘመዱ ቤት ተጠግተው እንደሚገኙና አሁን እርዳታ ለማቅረብ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑንን አመልክተዋል።
- ታደሰ ወረደ ” የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም” ሲሉ አዲሱን ግጭት የሚጠበቅ እንደሆነ አመላከቱየትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በራያ አላማጣ ዳግም ወረራ እየተካሄደ መሆኑ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ለክልሉ መገናኛ መግለጫ… Read more: ታደሰ ወረደ ” የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም” ሲሉ አዲሱን ግጭት የሚጠበቅ እንደሆነ አመላከቱ
- አብን ለአራተኛ ጊዜ በአማራ ላይ ወረራ መፈጸሙን ጠቅሶ፤ ሕዝብ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበየትግራይ ሃይሎች ዳግም ወደ አማራ ክልል ዘልቀው ወረራ መፈጸማቸውን ጠቅሶ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ለህዝብና መንግስት ጥሪ አቀረበ። የቀደሙትን ወራራዎች በማስታወስ ዳግም ስህተት እንዳይሰራ… Read more: አብን ለአራተኛ ጊዜ በአማራ ላይ ወረራ መፈጸሙን ጠቅሶ፤ ሕዝብ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ
- ለትህነግ ምላሽ – ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሠጠ መግለጫየትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ… Read more: ለትህነግ ምላሽ – ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሠጠ መግለጫ
- የትግራይ ክልል አማራ ክልልን አስጠነቀቀ – አማራ ክልል ” ትህነግን ምከሩ” ብሏልየትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ የአማራ ክልል የትግራይን መሬት በካርታው ላይ በማስፈርና በስርዓተ ትምህርቱ ላይ በማካተት እያስተማረበት እንደሚገኝ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ተረድቷል።ክልሉ… Read more: የትግራይ ክልል አማራ ክልልን አስጠነቀቀ – አማራ ክልል ” ትህነግን ምከሩ” ብሏል
- እንደ አደዋ ደል – ድህነትን ለማሸነፍ ምን እንሥራ …. ልጅ ዳንኤል ጆቴላለፉት ስምንት ዓመታት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚደንት ሆነው ያገለገሉት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ ስማቸውም ታሪክ አለው። በውጭው አጠራር ሚድል ወይንም በመካከል… Read more: እንደ አደዋ ደል – ድህነትን ለማሸነፍ ምን እንሥራ …. ልጅ ዳንኤል ጆቴ