የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እየወሰደ ባለው ማጥቃት የአሸባሪውን ኃይሎች ከአማራ ክልል እያስወጣ እንደሆነ የክልሉ መንግስት አስታወቋል። ክልሉ ወደ ሙሉ ማጥቃት መዛወሩን ይፋ ባደረግ በቀን ውስጥ ነው ይህን ያለው። የአሸባሪ ቡድኑ ወረራ በአማራ ክልል ተወስኖ ስላማይቀር የሌሎች ክልሎች ኃይሎችም የህልውና ዘመቻውን እየተቀላቀሉ መሆኑን ክልሉ ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል በጦርነቱ ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለዉ ቆቦ የሚገኙ ነዋሪዎች ርዳታን እየጠየቁ ነዉ።
የአማራ ክልል እንዳስታወቀው ህዝብ ለቅረበለት ጥሪ ከበቂ በላይ ምላሽ ሰጥቷል። የአሸባሪው ኃይሎች በሰሜናዊ የአማራ አካባቢዎች ወረራ መፈጸማቸውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በተደረገ የክተት ጥሪ ተቀብለው በርካቶች ትግሉን ተቀልቅለዋል። ትግሉን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ሆነው ስምሪት የሚጠብቁም ይልቃሉ።
የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን የመንግስት ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለጀርመን ድምጽ እንድተናገሩት የክልሉ ልዩ ሃይል አሸባሪው ቡድን ይዟቸው የነበረውን አካባቢዎች እያጸዳና እያስልቀቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“የአሸባሪው ጥቃት በአማራ ክልል ተወሰኖ እንደማይቀርና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሚሰራ በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ያረጋገጠው ነው” ያሉት አቶ ግዛቸው ይህን ሴራ ለመበጣጠስ ሌሎች ክልሎችም የፀጥታ ኃይሎቻቸውን ወደ አማራ ክልል እየላኩ እንደሆነ አስረድተዋል፣ እስካሁንም ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃሎቻቸውን ልከዋልም ብለዋል፡፡
አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት ሕወሓት በማይካድራ በቅርቡ ደግሞ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲደርስ አንድም ቃል ሳናገሩ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ፍትሃዊ አለመሆኑንን ሃላፊው አስታውቀዋል።
ሃላፊው አይገለጹት እንጂ አላማጣን ጨምሮ የትህነግ ቡድን ለአንድ ቀን ተቆጣጥሯቸው የነበሩትን ስፋርዎች የአማራ ልዩ ሃይል አስመልሷል። እንደሚሰማው ከሆነ የአማራ ልዩ ሃይል በጦርነቱ የበላይነት ይዟል። ይሁን እንጂ አሁንም ሰላማዊ ውይይት እንደሚሻል በስፋት አስተያየት እየተሰጠ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ የሚገኙ ወገኖች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ አንድ የራያ አማራየወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ተፈናቃዮች በየዘመዱ ቤት ተጠግተው እንደሚገኙና አሁን እርዳታ ለማቅረብ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑንን አመልክተዋል።
- እንደ አደዋ ደል – ድህነትን ለማሸነፍ ምን እንሥራ …. ልጅ ዳንኤል ጆቴላለፉት ስምንት ዓመታት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚደንት ሆነው ያገለገሉት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ ስማቸውም ታሪክ አለው። በውጭው አጠራር ሚድል ወይንም በመካከል… Read more: እንደ አደዋ ደል – ድህነትን ለማሸነፍ ምን እንሥራ …. ልጅ ዳንኤል ጆቴ
- ” ዐድዋ የኢትዮጵያ ልክም መልክም ነው” ተመስገን ጥሩነህ – ስለ አደዋ – የክልል መሪዎችዐድዋ የኢትዮጵያ ልክም መልክም ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል… Read more: ” ዐድዋ የኢትዮጵያ ልክም መልክም ነው” ተመስገን ጥሩነህ – ስለ አደዋ – የክልል መሪዎች
- በደብረ ብርሃን ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ኦሮሚያ ክልል መመለስ ጀመሩተመላሾች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው የተመለሱት “በፈቃደኝነት” መሆኑን ተናግረዋል።
- ስንዴ በገፍ – ለምን ገበያው አይረጋጋም?ኢትዮጵያን ከጠብመንጃ ባልተናነሰ የንግድ አሻጥርና የአመራር ዥጉርጉርነት ፈተናዋ እንደሆነ በርካታ አመላካች ጉዳዮች አሉ። በዚሁ የንግድ አሻጥር የተነሳ ህዝብ ክፉኛ መከራውን እንዲያይ ተፈርዶበታል። ስግብግብነትና… Read more: ስንዴ በገፍ – ለምን ገበያው አይረጋጋም?
- የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚያም ምን ተካቶበታል?ኢትዮጵያ ነጻነቷን ጠብቃ እንድትኖር ያደረጓት አባቶቻችንን የሚዘክር የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ ፒያሳ ተገንብቶ ዛሬ ይመረቃል፡፡ መታሰቢያው የተገነባው ጀግኖች ወደ ጦርነቱ ሲተሙ በአንድነት… Read more: የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚያም ምን ተካቶበታል?