በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩ ጨፌው ወሰነ። ኢዜአ እንዳለው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩና ማንኛውንም አገልግሎት ሲፈልጉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) የወሰነው ዛሬ ነው።
ዛሬ በተጀመረው የጨፌው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እውቅና መስጠት የሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ፀድቋል።
አፈ ጉባኤዋ በማብራሪያቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ መሆኑን ገልጸዋል።በሰሜን ኢትዮጵያ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን የአገር ሉዓላዊነት የመድፈር ወንጀል ሰራዊቱ በከፍተኛ ጀግንነትና መስዋእትነት ጭምር መቀልበሱን ጠቅሰዋል። “በዚህም ለአገር መከላከያ ሰራዊት እውቅና መስጠት አስፈልጓል” ብለዋል።
በውሳኔ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላ ከላቸው ማንኛውም ማዕርግ በተጨማሪ ” ጅግና” የሚል የክብርና ተጋድሏቸውን የሚያደነቅ የክብር ስያሜ ይኖራቸዋል። ምክር ቤቱ ይህን ውሳኔ መወሰኑ ለሁሉም ምሳሌ እንደሚያደርገው ይገመታል።
ኦሮሚያ ክልል አሸባሪውን ሃይል “ለህልውናችን ያሰጋናል” ሲል ወደ ግዳጅ ቀጠናው ሰራዊት ማሰማራቱ ይታወሳል።
- የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”“የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም!” በሚል ርዕስ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባሰራጨው መግለጫ ትህነግን አስጠንቅቆ ” የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ… Read more: የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ለትግራይ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ፤ “አማራ ልዩነትህን ወደጎን አድርግ፤ዳግም በጅምላ አንቀበርም”
- በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!More stories በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!April 19, 2024 ” አልፎ እንዳይቆጨን … እድል እንዳያመልጥ ” ቁ. 1April 10, 2024 አዲሱ ሚኒስትር “የሰላም እጦት”February 23, 2024… Read more: በዝቋላ ገዳም የሆነው ይህ ነው!!
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared three days of national… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning
- U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membershipCGTN – The United States on Thursday stopped the UN from recognizing a Palestinian state by casting a veto in the Security Council to deny Palestinians… Read more: U.S. stops UN from recognizing a Palestinian state through membership
- Israel launches missile attacks on Iran: reportCGTN – Israeli missiles have hit a site in Iran, ABC News reported late on Thursday, citing a U.S. official, while Iranian state media reported explosions,… Read more: Israel launches missile attacks on Iran: report