ቱርክ”ድሮኖቼ ኢትዮጵያ የሉም” አለች፤ በቴክኖሎጂና ሽብርን በመዋጋት ከኢትዮጵያ ጋር ይሰራሉ-ተጨማሪ አጫጭር ዜናዎች

ቱርክ ለኢትዮጵያ መንግስት ድሮኖችን ድጋፍ አድርጋለች የሚለዉ ከእዉነት የራቀ መሆኑን የአገሪቱ አምባሳደር አስታወቁበኢትዮጵያ ቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ እንዳስታወቁት፤ በኢንቨስትመንት፣ በማህበራዊ፣ በቴክኖሎጂና ሽብርተናነትን በመዋጋት ረገድ ግን ከኢትዮጵያ ጋር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት የቱርክ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን ወይንም ድሮኖች በኢትዮጵያ የሉም ብለዋል፡፡የቱርክ መንግስት ለኢትዮጵያ ድሮኖችን ድጋፍ እያደረገ ነዉ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰዉ ወሬ ከእዉነት የራቀ ስለመሆኑም አምባሳደሯ አንስተዋል፡፡

ቱርክና ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድም ተቀናጅዉ እንደሚሰሩ የገለፁት ያፕራክ፤በተለይም እንደ ፌቱላህ አይነት ተስፋፊ የሽብር ቡድኖችን በጋራ ማስወገድ ይገባል ብለዋል፡፡ሁለቱ አገራት በፖለቲካና በኢኮኖሚ ያላቸዉን ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚሰሩም በመግለፅ በቀጣይም የንግድ ግንኙነቱን ማጠንከር ይገባል ማለታቸዉን አናዶሉ ኤጀንሲ ነዉ የዘገበዉ፡፡

አሁን ላይ ከ2መቶ 20 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙና ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ማድረጋቸዉን ያስታወቁት አምባሳደር አልፕ ለ25 ሺህ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠሩም ገልፀዋል፡፡ከዚህ ባለፈም በትምህርት ዘርፍ በ የአመቱ ለ75 ኢትጵያዉያን የትምህርት ዕድል እንደምትሰጥም ተጠቁሟል፡፡ባጠቃላይ የቱርክ መንግስት በኢንቨስትመንት፤ በቴክኖሎጂ ልዉዉጥ፤ በሰብአዊ እርዳታ በቱሪዝምና በሌሎችም ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡ ያለው ኢትዮ ኤፍ ኤም ነው

“ነጩ ወይኔ” የሚባለው እንግሊዛዊው ማርቲን ፕላውት በሰበር ዜና ቱርክ ለኢትዮጵያ የድሮን ማምረቻ ማዕከል መገንባቷንና ድሮን እየተመረተ መሆኑንን ማስታወቁ አይዘነጋም። ማቲን ፕላውት በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ሰዓት ጀአሸባሪው ሃይል እየሰራ ነው።

በቡና ኤክስፖርት 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል

የኢትዮጲያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ እንደተናገሩት ከቡና ኤክስፖርት በታሪክ የመጀመሪያ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ገቢ በዘንድሮ በጀት አመት ተገኝቷል፡፡ ኢትዮጵያ በዘንድሮው 2013 በጀት ዓመት ወደ ውጭ አገራት ከላከችው የቡና ምርቷ ታሪካዊና አስደናቂ ሊባል የሚችለውን የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ችላለች፡፡

በአሥራ ሁለት ወራት ውስጥ 248 ሺኅ 311 ነጥብ 66 ቶን ከታቀደው 80 በመቶ በመላክ 907ነጥብ04 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ከዕቅዱ 77 በመቶ ገቢ መገኘቱን ዶ/ር አዱኛ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የውጭ የቡና ኤክስፖርት ማድረግ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በ2009 ዓ.ም አግኝታው የነበረው 882 ሚሊየን ዶላር ከፍተኛ ተብሎ የተመዘገበው ሲሆን ዘንድሮው የተገኘው ገቢ በ25 ሚሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ የተገኘበት ነው፡፡

ይህን ውጤት ማግኘት የተቻለው በዋናነት የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠር በተወሰደው እርምጃ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በአቅራቢ እና ላኪ መካከል የተፈጠረው ቀጥተኛ የገበያ ትስስር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል፡፡በ2014 በጀት አመት በቡና ኤክስፖርት 280 ሺህ ቶን ቡና በመላክ አንድ ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ዶ/ር አዱኛ ተናግረዋል፡፡ – ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

አየር መንገዱ ከሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በጭነት አገልግሎት ያለውን ውል አራዘመ

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቤልጂየሙ ሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በጭነት አገልግሎት ያለውን ውል ለተጨማሪ አመታት አራዘመ፡፡ አየር መንገዱ ከአውሮፕላን ማረፊያው ጋር ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ነው ውሉን ያራዘመው፡፡

በዚህም የሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ እና አውሮፓ መካከል የጭነትና የሎጂስቲክስ አገልግሎት መተላለፊያ ሆኖ እንደሚያገለግል የኤር ካርጎ መረጃ ያመላክታል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 15 አመታት ከሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በመተባበር በአውሮፓ የተሳካ የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ፋና

በጥሬ ጌጣጌጥ ማዕድናት ኤክስፖርት ላይ የተጣለው ገደብ ተነሳ

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር እሴት ባልተጨመረባቸው ጥሬ የጌጣጌጥና ማዕድናት ኤክስፖርት ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ አነሳ፡፡ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በማሰብ እንደ ኦፓል ፤ ሳፋየር እና ኤመራልድ ያሉ የጌጣጌጥ ማዕድናት እሴት ተጨምሮባቸው ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ ላኪዎች 20 በመቶ እሴት የተጨመረባቸው 80 በመቶ ጥሬ ማዕድናት እንዲልኩ ይገደዱ ነበር፡፡

መመሪያው ተሻሽሎ ከቅርብ አመታት ወዲህ እሴት የተጨመረበት 50 በመቶ ጥሬ እሴት ያልተጨመረበት ጥሬ ማዕድን 50 በመቶ እንዲላክ አስገዳጅ መመሪያ ወጥቶ በዚሁ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በሀገር ውስጥ የጌጣጌጥ ማዕድናትን ፕሮሰስ የማድረግ በቂ እውቀትና ልምድ ባለመኖሩ በአገር ውስጥ እሴት የተጨመረባቸውን የጌጣጌጥ ማእድናት በውጭ ገበያ ለመሸጥ ላኪዎች ተቸግረው ከርመዋል፡፡

ይህን ያጤነው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ላኪዎች ለውጭ ገበያ ከሚያቀርቡት ማዕድናት ውስጥ በከፊል እሴት የተጨመረበት ማዕድን እንዲልኩ የሚያስገድደውን አሰራር እንዲቀር መወሰኑን አስታውቋል፡፡ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ አምራቾችና ላኪዎች ያለገደብ በፍላጎታቸው መሰረት እንዲሰሩ መፈቀዱን ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም የጌጣጌጥ ማዕድናት ኤክስፖርት ዝቅተኛ ዋጋ ትመና አሰራር እንዲከለስ መወሰኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ – ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

የማዕድን ግብይት በዘመናዊ የግብይት ስርዓት ሊከናወን ነው

የማዕድናት ግብይት በቅርቡ በዘመናዊ የግብይት ሥርዓት መካሄድ እንደሚጀመር የኢትዮጲያ ምርት ገበያ አስታወቀየማዕድን ምርቶችን ወደ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ለማስገባት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ይታወሳል ፡፡ በተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት በ2014 በጀት ዓመት ኦፓል ፥ ሳፋሪና ኢመራልድ ማዕድናትን ማገበያየት እንደሚጀምር የኢትዮጲያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ ነገራ ተናግረዋል። ባለፉት ወራት ከሁለቱም መ/ቤቶች የተውጣጡ ባለሙያዎች ያሉበት የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ የዝግጅት ሥራ በመከናወን ላይ ሲሆን፤ እስካሁን የቅድመ ዝግጅት ሥራ የኮንትራት ዝግጅትና የግብይት ሞዳሊቲ ተዘጋጅተዋል ተብሏል። በቅርቡ በማዕድን ምርትና ግብይት ላይ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር የኢንዱስትሪ ምክክር እንደሚደረግ አቶ ወንድማገኝ ጠቁመዋል። – ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

Leave a Reply