በኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር የህዳሴው ግድብ ዛሬ ለሌት ሲሞላ ” ኢትዮጵያ ኒኩሌር ታጠቀች” ማለት እንደሆነ ባለሙያዎች አስታወቁ። ሲያብራሩም የህዳሴውን ግድብ መሙላት ማለት ግድቡን ከማንኛውም ክፉ ሙከራ መታደግ እንደማለት ነው።
“በኢትዮጵያዊያን ደም፣ አጥንትና ላብ የተሰራ ነው” ሲሉ ድየውሃና መስኖ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ የገለጹት የህዳሴው ግድብ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ተገባዷል። ወይም እንደተገባደደ ይታመናል። በዚሁ ሂሳብ መሰረት ከፍታው ከባህር ወለል በላይ 574 ሜትር ሆኗል። ዶክተር ስለሺ በተደጋጋሚ እንደተናገሩት የውሃው ሙሌት ሲጠናቀቅ በሁለት ተርባይን የኤሌክትሪክ ሃይል ለማምረት የተያዘው ዕቅድ የሚሳካ ነው።
የሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት አስመለክቶ ግብግብ ፈጥራ የነበረችው ግብጽ የውሃው ሙሌት ጫፍ መድረሱንና ምንም ማድርተግ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን ስትረዳ አልሲሲ “ኢትዮጵያን በልማት ማገዝ እንፈልጋለን” ማለታቸውን ያስታወሱ ባለሙያዎች እንዳሉት ካሁን በሁዋላ የህዳሴው ግድብ ጥበቃ አያስፈልገውም።
ግብጽ ግድቡን ብትመታ ሽቅብ ወደላይ ሳይሆን ወደታች ሲወርድ ሱዳንና ግብጽን ተረት እንደሚያደርጋቸው በሂሳብ የሚያስረዱ እንዳሉት፣ ግብጽ ካሁን በሁዋላ ማተረማመሷን ታስቀጥል ካልሆነ በቀር ህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ አንዳችም ክፋት ማሰብ አትችልም።
ነገ የወሃው ሙሌቱ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያዊያን በይፋ ” ኒኩሌር ታጠቁ እንደማለት ነው” ሲሉ የተናገሩትም በዚሁ መነሻ መሆኑንን አመልክተዋል። “ምርጫ ካካሄደች ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” ሲባል የተሳካ ምርጫ ማካሄዷን፣ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ሙሌት መሳካቱን አንድ ላይ አዳምረው ለኢትዮጵያዊያን ይህ ታላቅ የድል ዜና እንደሆነ እየተገለጸ ነው።
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል የዕዳ… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት ታምኖበት ፖሊሲ ሲዘጋጅ መቆየቱ… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ የሚሊሻ ሃይሉ ጸጥታ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ የተለመደው አይነት የፈንጠዝያ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን