“አደንዛዥ ዕጽ የሚሰጧቸው በበርሜል ሻይ አፍልተው ነው”

አሸባሪው ትህነግ (የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ዜጎችን ወደ ውትድርና ተመልምለው ለውጊያ የሚያደርሰው በሁለት መንገድ ነው፤ አንዱ ምንም የጦር ዕውቀትና ልምምድ ሳይኖራቸው በግድ ከሽፍታው ቡድን ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አደንዛዠ ዕፅ አፍልተው ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ትህነግ ህጻናት ልጆችን ለጦርነት እየመለመለ እንደሚሰማራ በማስረጃ ተረጋግጦበታል። ልጆቹ በተለይ ለዚህ ግዳጅ እንዲሰማሩ የሚደረግበትን አካሄድ በየኔታ ትዩብ ላይ የተናገረው በቅርቡ በምርጫ የተወዳደረው ማኅበራዊ አንቂ ብሩክ አበጋዝ ነው።

ብሩክ እንደሚለው ትህነግ ልጆቹን ከሰበሰበ በኋላ የጠጡት ምን እንደሆነ በማያውቁበት ሁኔታ እንደ መደበኛ የሚጠጣ ነገር ሻይ ይሰጣቸዋል። ልጆቹ የሚያውቁት ወይም የሚነገራቸው ሻዩ የሚሰጣቸው ለብርታት ተብሎ እንደሆነ ብቻ ነው።https://www.youtube.com/embed/V77OTfMU4TY?feature=oembed

በሌላ በኩል የኢትዮፕያ ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው አሸባሪው ትህነግ ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ ነው፤ ሚዛን አልባው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወንጀሉን ከማጋለጥ ይልቅ የጁንታው “የህዝብ ድጋፍ” ማሳያ አድርጎታል።

በዓለም አቀፍ ህግ ህጻናትን ለጦርነት መጠቀም ወንጀል መሆኑ እየታወቀ ራስ ወዳዱ ጁንታ እድሜያቸው ለትምህርት እንጂ ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናትን በሀሽሽ አደንዝዞ ጦርነት ውስጥ እያሰለፈ ነው።

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀንም ጉዳዩን በራሳቸው ዘገባ ጭምር ይዘው ቢወጡም ጉዳዩን ከማውገዝና አጥፊዎችን ከመኮንን ይልቅ በተቀራኒ ተሰልፈው የጁንታው ወንጀል አስተባባዮች ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል። የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል” ሲሉ የጉዳዩን አደገኛነት አስታውቀዋል።

የጁንታው አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ የህግ ማስከበር ዘመቻው ሲፋፋምባቸው የትግራይ ህጻናት ድንጋይም ቆንጨራም በመያዝ እንዲታገሉ ጥሪ ማድረጉ አይረሳም። አሁንም በተጨባጭ እየሆነ ያለው ይሄው ነው።

ዓለም፤ “… ስለ ርዳታና ስለ ረሐብ ሲናገር መቆየቱን ዘንግቶ ጁንታው ሕጻናትን ሲያሰልፍ እንኳን ዝምታን መርጧል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን የገለጹት፤ አሁን ለጁንታው የተሰጠው እድል የመጨረሻ የሰላም አማራጭ መሆኑን በመጥቀስ ነው። (ኢፕድ)

ጎልጉል ከተለያዩ ማህበራዊ ገጾች እና ከራሱ ከጁንታው ደጋፊዎች ገጾች የሰበሰባቸውን የህጻናት “ወታደሮች” ምስሎችን እንዲህ አቅርቧቸዋል።

በተቃራኒው ጄኔቭ ሆኖ “ግፋ በለው” እያለ ህጻናቱን የሚማግደው የአሸባሪው ትህነግ አባል ቴድሮስ አድሃኖም ለራሱና ለልጆቹ በአውሮጳ የተደንደላቀቀና የቅምጥል ኑሮ የኖረ ነው። በጦር ወንጀለኝነት ሊጠየቅ ይገባዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Leave a Reply